ልጥፎች

ከጁላይ, 2017 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አፋን ኦሮሞ ሁለተኛው የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዳይሆን ምን ያግደዋል?

ምስል
በቶለዋቅ ዋሪ ከ25 ዓመታት በላይ እንደ ፈንጂ ሲፈራ የነበረው የኦሮሚያ ክልል ከፊንፊኔ ማግኘት ያለበት ህገ መንግስታዊ የልዩ ጥቅም ጉዳይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፀሃይ የሞቀው አገር ያወቀው ጉዳይ ሆኖ አነጋጋሪና አወያይ   በመሆን ቀጥሏል መልካም ነው ጉዳዩ እንዲህ ግልጥልጥ ብሎ   ለሰፊው ሕዝብ መቅረብ ሲችል ለአመታት ተደፋፍኖ ለፀረ ሰላምና ፀረ ሕዝብ ኃይሎች የተቃውሞ አጀንዳ ሆኖ መቆየት አልነበረበትም፤ይሁንና አሁን ሁሉም ነገር ትክክለኛውን መስመር በመያዝ ላይ ስለሚገኝ ቢዘገይም ለበጎ ነው ማለት ይቻላል በቅርቡ በኢፌዴሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ   ወደ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራው የልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት አባላትም ውይይት ተካሂዶበት ጉዳዩ ወደ ሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ በይደር እንዲቆይ መወሰኑ ይታወቃል “የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ” እንዲሉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ውጤት አልባ እንዳይሆንና ሁሉንም የሚያነጋግር በመሆኑ በውይይት እንዲብላላና የኦሮሞ ሕዝብ ፍላጎት ተሳክቶ የሌሎች ወገኖች መብትም ሳይነካ አዋጁ ብሰለት እንዲኖረው እንወያይበት መባሉ ትክክለኛና በአመራሮቻችን ብስለት የመጣ አመርቂ ውሳኔ እንደሆነ መረዳት አያዳግትም በረቂቅ አዋጁ ውስጥ በተጠቀሱት ልዩ ጥቅም በተባሉ ጉዳዮች ላይ በሌላ ፅሁፌ እይታዬን የማንፀባርቅ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ፅሁፍ በረቂቅ አዋጁ ላይ ስለተጠቀሰው የአፋን ኦሮሞ በፊንፊኔ የስራ ቋንቋ መሆን ፍላጎትን መሰረት በማድረግ እንዲህ ቢሆንስ የሚል ሌላውን እይታዬን ላንፀባርቅ የኦሮምኛ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ የቀድሞዎቹ ጨቋኝ ስርዓቶች በሰፊው የኦሮሞ ሕዝብና በሌሎች ብሄር ብሄራሰቦችና ሕዝቦች ላይ ባደረጉት ገደብ የለሽ ተፅዕኖ ምክንያት የስነ ፅሁፍና የስራ ቋንቋ