የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ የሕዝቡን ንቁ ተሳትፎ ግድ ይላል
የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በአንድ ወቅት የሚጠናቀቅ ሳይሆን በሂደት የሚከናወን ነው፡፡ የስርዓት ግንባታውን ከዳር ለማድረስ በሂደቱ ከውስጥና ከውጭ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ማለፍ ያስፈልጋል፡፡ በሀገራችን እየተካሄደ የሚገኘው የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በእስከአሁኑ ሂደት ውጣ ውረዶች ሳይበግሩት በርካታ ድሎችን አስመዝግቧል፡፡ በሂደቱ ያጋጠሙ በርካታ ተግዳሮቶችን ታግሎ በማስተካከል ሂደቱን ለማሳለጥ ተሞክሯል፡፡ የስርዓት ግንባታውን እየተፈታተኑት ከሚገኙ ችግሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ሲሆን በዚህ ላይ ትግል ከተጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ በመሆኑም ባለፉት 15 ዓመታት ከየትኛውም መሰል ሀገር የተሻለ እድገት ማስመዝገብ ችለናል፡፡ በየሴክተሩ በተደረገው ርብርብ መጥፎ ገጽታችን በለውጥ ተምሳሌትነት ተቀይሯል፡፡ ሆኖም ግን አሁንም ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን ከኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ባለመላቀቁ ትግሉ ሊቀጥል ግድ ነው። ኪራይ ሰብሰቢነት ከገበያ ውድድር ውጪ ለስልጣን ባለ ቀረቤታ አማካኝነት ያልተገባ ጥቅም የሚግበሰብስበት የዜሮ ድምር ስልት ነው፡፡ ይህ ተግባርና አመለካከት ለኢኮኖሚው ባበረከቱት አስተዋጾ ልክ ከሚገኝ ፍትሃዊ ጥቅም ጋር ፍጹም ተቃራኒ የሆነ አካሄድ ሲሆን፤ ስር እየሰደደ በሄደ ቁጥር በሀገር ውስጥ የሚገኘው ኃብት በጥቂቶች ቁጥጥር ስር እንዲውል መንገድ የሚከፍትና ብዙኃኑን የሚያገልል ሁኔታ እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው፡፡ በተከታታይ አመታት በግብርና ገጠር ልማት ዘርፍ ባደረግነው ርብርብና በተመዘገበው ስኬት የተነሳ መላው አርሶ አደራችን የብልፅግናው ምንጭ የራሱንና የቤተሰቡን ጉልበት አስተባብሮ በማሳው ላይ የሚያደርገው ጥረት ብቻ መሆኑን መረዳት ከጀመረ ውሎ አድሯል። በዚህ የተ...