ልጥፎች

ከጃንዋሪ, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

Himannaan Dooktar Mararaa addaan cite

ምስል
Dooktar Mararaa Guddinaa fi Dooktar Ruufaa’eel Disaasaa dabalatee himannaan sadarkaa federaa laan namoota 115 irratti banamee ture addaan cite. Faanaa Broodkaastiing Koorporeet odeeffannoon argate akka muul’isutti himannaan shakkamtoota naannoo Kibbaa godina Geede’oo 361 fi aanaa Koonsoo 52 adda citeera. Naannoleen biroos dhimma shakkamtoota himannaan isaanii adda cituuf adda baasaa jiru. Murtee koreen hoji raawwachiistuu ADWUI dabarseen himannaan shakkamtoota 528 marsaa duraatin akka adda cituuf taasifameera. Shakkamtoonni kanneenis har’aa fi booru haaromsa fudhatanii iftaanii kaasee kan gadi lakkifaman ta’uu Abbaan Alangee Federaalaa obbo Geetaachaw Ambaayeen ibsa har’a laataniin beeksisaniiru. Maddi:FBC

የ528 ተጠርጣሪዎች ክስ በመጀመሪያ ዙር ተቋረጠ

የ528 ተጠርጣሪዎች ክስ በመጀመሪያ ዙር ተቋረጠ የፍርድ ሂደታቸው በመታየት ላይ የሚገኙ 528 ተጠርጣሪዎች ክስ በመጀመሪያ ዙር መቋረጡን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ገለፀ። በአራት መስፈርቶች ተለይተው ክሳቸው ከተቋረጠው ተጠርጣሪዎች መካከል 115ቱ በፌደራል ደረጃ ሲሆኑ፥ ሌሎቹ 413 ደግሞ ከደቡብ ክልል የቀረቡ ናቸው። ከደቡብ ክልል ክሳቸው የተቋረጠላቸው ተጠርጣሪዎች በክልሉ በጌዲኦ ዞንና በኮንሶ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በመሳተፍ የተጠረጠሩ ናቸው። በፌደራልና በደቡብ ክልል ቀርበው ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ተጠርጣሪዎች ውጭ ግን ሌሎች ክልሎች ክሳቸው የሚቋረጥላቸውን ተጠርጣሪዎች ገና አለማቅረባቸው ተመልክቷል። የተጠርጣሪዎቹ ማንነት በቀጣይ ይፋ እንደሚሆን እና ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ እንደሚለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ እየሰጡት ባለው መግለጫ ጠቅሰዋል። የተፈረደባቸው እና በይቅርታ የሚፈቱትን በተመለከተም በተቀመጡት መስፈርቶች መሰረት እየተለዩ መሆኑን ያነሱት አቶ ጌታቸው፥ መለየቱ ግን ጊዜ እንደሚወስድ ነው ያስታወቁት። በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያካሄደውን ግምገማ ተከትሎ አራቱ የግንባሩ አባል ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት በሰጡት መግለጫ ላይ “በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት በፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ወይም ደግሞ ወንጀል በመፈፀም ድርጊት ተጠርጥረው በአቃቤ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በምህረት ህግና ህገመንግሥቱ በሚፈቅደው መልኩ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ እንዲፈቱ ይደረጋል።" መባሉ ይታወሳል Source:FBC

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያልተለመዱ ግምገማዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊነት በጉጉት እየተጠበቀ ነው

ምስል
የሚፈቱ ፖለቲከኞች ዝርዝር ጉዳይ ከአሁኑ አከራካሪ ሆኗል የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ 17 ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ዝግ ስብሰባ አጠናቆ በመጨረሻ ባወጣው መግለጫና አራቱ የኢሕአዴግ አባል ድርጀቶች ሊቃነ መናብርት ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ . ም . በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችና ሌሎች ግለሰቦች እንደሚፈቱና ‹‹ ማዕከላዊ ›› በመባል የሚታወቀው የምርመራ ማዕከል እንደሚዘጋ ማስታወቃቸውን ጨምሮ ‹‹ ያልተለመዱ ›› የተባሉት ግምገማዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊነት በጉጉት እየተጠበቀ ነው፡፡ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ 17 ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቆ በመጨረሻ ባወጣው መግለጫ፣ የችግሩ ዋነኛ ምንጭ ሥራ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል መሆኑን አሳውቋል፡፡ መግለጫውን ከሰጡት መካከል አንዱ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ‹‹ በዓቃቤ ሕግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር ላይ የሚገኙና የተፈረደባቸው ፖለቲከኞችም ሆኑ የተለያዩ ግለሰቦች ይፈታሉ፡፡ ይህም የሚደረገው የተሻለ አገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዴሞክራሲ ምኅዳሩን ለማስፋት በማሰብ ነው፡፡ ታሳሪዎቹ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ ይለቀቃሉ፤ ›› ብለዋል፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባላት በአገሪቱ ለተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት በጥልቀትና በዝርዝር በመምከር የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ስብሰባውን ‹‹ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ...