የ528 ተጠርጣሪዎች ክስ በመጀመሪያ ዙር ተቋረጠ

የ528 ተጠርጣሪዎች ክስ በመጀመሪያ ዙር ተቋረጠ
የፍርድ ሂደታቸው በመታየት ላይ የሚገኙ 528 ተጠርጣሪዎች ክስ በመጀመሪያ ዙር መቋረጡን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ገለፀ።
በአራት መስፈርቶች ተለይተው ክሳቸው ከተቋረጠው ተጠርጣሪዎች መካከል 115ቱ በፌደራል ደረጃ ሲሆኑ፥ ሌሎቹ 413 ደግሞ ከደቡብ ክልል የቀረቡ ናቸው።
ከደቡብ ክልል ክሳቸው የተቋረጠላቸው ተጠርጣሪዎች በክልሉ በጌዲኦ ዞንና በኮንሶ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በመሳተፍ የተጠረጠሩ ናቸው።
በፌደራልና በደቡብ ክልል ቀርበው ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ተጠርጣሪዎች ውጭ ግን ሌሎች ክልሎች ክሳቸው የሚቋረጥላቸውን ተጠርጣሪዎች ገና አለማቅረባቸው ተመልክቷል።
የተጠርጣሪዎቹ ማንነት በቀጣይ ይፋ እንደሚሆን እና ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ እንደሚለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ እየሰጡት ባለው መግለጫ ጠቅሰዋል።
የተፈረደባቸው እና በይቅርታ የሚፈቱትን በተመለከተም በተቀመጡት መስፈርቶች መሰረት እየተለዩ መሆኑን ያነሱት አቶ ጌታቸው፥ መለየቱ ግን ጊዜ እንደሚወስድ ነው ያስታወቁት።
በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያካሄደውን ግምገማ ተከትሎ አራቱ የግንባሩ አባል ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት በሰጡት መግለጫ ላይ “በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት በፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ወይም ደግሞ ወንጀል በመፈፀም ድርጊት ተጠርጥረው በአቃቤ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በምህረት ህግና ህገመንግሥቱ በሚፈቅደው መልኩ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ እንዲፈቱ ይደረጋል።" መባሉ ይታወሳል
Source:FBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman