ልጥፎች

ከሴፕቴምበር, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አዲሱን ዓመት አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕት

ምስል
ክብርት የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ለአንድ እራት አምስት ሚሊዮን ብር የከፈላችሁ እውነተኛ የኢትዮጵያ ባለሃብቶች ዛሬ የዚህ በአል እውነተኛ ታዳሚ በመሆናችሁ ለእናንተም የሚገባችሁን ክብር ሰጥቼ መጀመር እፈልጋለሁ። ብዙ ተስፋ አስቆራጭ ነገር ባለበት ሀገር ውስጥ 16 ሰዓት እየሰራችሁ የቤተመንግስቱን ፕሮጀክት በስድስት ወር ጊዜ ማጠናቀቅ ለቻላችሁ የፕሮጀክት ኃላፊዎች እንደምንችል ለሕዝብ ልምድ ያሣዩና ለእኛም ተስፋ የሆኑ ሙያተኞች በእኛ መካከል አላችሁ። የሚገባችሁን ክብር ሰጥቼ ማለፍ እፈልጋለሁ። በለውጥ እርምጃዎቻችሁ ታጅቦ ላይመለስ በማለፍ ላይ ያለው አመት ከእድሜው ቁጥር በላይ ታላቅ ፈተና የደቀነብን ግን ደግሞ ኢትዮጵያ በፈተና የማትወድቅ መሆኗን ዳግም ያስመሰከረ ዘመን ነበር 2011 ዓ.ም። ያሳለፍነው አንድ አመት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ እንደሀገርና ሕዝብ ለዘመናት ተጭኖ የነበረው ድህነት፣ጉስቁልና የመብት ረገጣና አፈና ጦርነት የመበታተን አደጋ በዘላቂነት እንዲወገድ እንዲሁም የዘመናት ጸረ-ዴሞክራሲያዊ የቁልቁለት ጉዟችን እንዲገታ የጦርነት ታሪካችን ጦርነት ሆኖ እንዳይቀጥል ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከራሳቸው ጋር እንዲታረቁ ፤የዜጎች ክብርና ሀገራዊ አንድነት እንዲረጋገጥ የአንድ አመት ሳይሆን የአስር አመቱን ውዝፍ እዳ የተጋፈጥንበትም አመት ነበር። ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ከለውጥ በፊት የነበሩባቸው አያሌ ጭነቶቻቸው በለውጡ ከጭንቅላታቸው ላይ የተራገፈላቸው ቢሆንም በምትኩ ካረፉባቸው አዳዲስ ጭነቶች ገና አልተገላገሉም። በሕዝብ ትግል ከመጣው ለውጥ በፊት እንደነበሩት በርካታ አመታት በውስጥና በውጭ ግልጽ የሆነ ጦርነት በሀገር ደረጃ ባይኖርም ሰላሙ እረፍት ከሚሰጥበት ዴሞክራሲው ሙሉ በሙሉ ከአፈና የተላቀ...

ለሃይማኖታዊ ግጭት ጅማ የተመረጠችበት ምክንያት!

ምስል
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ያነበብኩት አንድ መረጃ በጅማ ከተማ በሃይማኖት ስም ብጥብጥ ለመፍጠር የተደረገው ጥረት በህዝብና የፀጥታ አካላት ጥረት ከሽፏል ይላል መክሸፉ ጥሩ ነው እንኳን ከሸፈ! የነገሩን ስረ መሰረት ግን ለወደፊት ጥንቃቄ ማድረግ በሚያስችል መልኩ ማየትና መረዳት ያስፈልጋል የሚል እምነት አለኝ በራሴ ግምት ብጥብጡ እንዲነሳ የተፈለገው “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር ሆነን በኦሮሚያ ክልል የራሳችን መዋወቅር ይኑረን” ብለው የጠየቁ አባቶችን በማሸማቀቅ የህዝብ ፍላጎትም ተዳፍኖ እንዲቀር ለማድረግ ነው በዚህ ጉዳይ ወስጥ የብዙ አካላት እጅ ሊኖር ይችላል ከውጭ እስከ አገር ውስጥ በገንዘብና በመሳሰሉት ጉዳዮች ድጋፍ እንደሚደረግ መገመት አይከብድም ከአመታት በፊት ጅማ ከተማና አካባቢዋ ላይ የሆነውን አረመኔያዊ ድርጊት እናስታውስ፤አሁን ጅማ የተመረጠችበትን ተጨባጭ ምክንያት ልንገራችሁ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ቤተክርስቲያን አቃጥለዋል ጉዳት አድርሰዋል በሚል ምክንያት ዘግኛኝ ድርጊት ተፈፅሞ አልፏል እንዲያውም በወቅቱ የደረሰው ጉዳት በምስል ተወስዶ በሲዲ አባዝተው በማሰራጨት ቸብችበው የተጠቀሙ ኃይሎች አሉ አሁንም “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ደርሷል” በሚል ሽፋን በመላ አገሪቱ ህዝቦች እንዲጋጩና አስከፊ ጉዳት እንዲደርስ ፅኑ ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች አሉ እነዚህ ኃይሎች ገንዘባቸውን መድበው በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አትጠራጠሩ!በዚህ ምክንያት ያጡትን ለማግኘት የሚጥሩ የሚፍጨረጨሩ ደፋ ቀና የሚሉ አሉና ልብ እንበል የለውጡ አደናቃፊዎችም በዚህ ዘመቻ ተጠቃሚ ሊሆኑ ስለሚችሉ እንደሚቀላቀሉ አትጠራጠሩ!በጅማ የከሸፈው ጥረት ሌሎች አካባቢዎች ላይም ቢሞከር በፍጥነት ...