ለሃይማኖታዊ ግጭት ጅማ የተመረጠችበት ምክንያት!

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ያነበብኩት አንድ መረጃ በጅማ ከተማ በሃይማኖት ስም ብጥብጥ ለመፍጠር የተደረገው ጥረት በህዝብና የፀጥታ አካላት ጥረት ከሽፏል ይላል መክሸፉ ጥሩ ነው እንኳን ከሸፈ!
የነገሩን ስረ መሰረት ግን ለወደፊት ጥንቃቄ ማድረግ በሚያስችል መልኩ ማየትና መረዳት ያስፈልጋል የሚል እምነት አለኝ
በራሴ ግምት ብጥብጡ እንዲነሳ የተፈለገው “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር ሆነን በኦሮሚያ ክልል የራሳችን መዋወቅር ይኑረን” ብለው የጠየቁ አባቶችን በማሸማቀቅ የህዝብ ፍላጎትም ተዳፍኖ እንዲቀር ለማድረግ ነው
በዚህ ጉዳይ ወስጥ የብዙ አካላት እጅ ሊኖር ይችላል ከውጭ እስከ አገር ውስጥ በገንዘብና በመሳሰሉት ጉዳዮች ድጋፍ እንደሚደረግ መገመት አይከብድም
ከአመታት በፊት ጅማ ከተማና አካባቢዋ ላይ የሆነውን አረመኔያዊ ድርጊት እናስታውስ፤አሁን ጅማ የተመረጠችበትን ተጨባጭ ምክንያት ልንገራችሁ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ቤተክርስቲያን አቃጥለዋል ጉዳት አድርሰዋል በሚል ምክንያት ዘግኛኝ ድርጊት ተፈፅሞ አልፏል እንዲያውም በወቅቱ የደረሰው ጉዳት በምስል ተወስዶ በሲዲ አባዝተው በማሰራጨት ቸብችበው የተጠቀሙ ኃይሎች አሉ
አሁንም “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ደርሷል” በሚል ሽፋን በመላ አገሪቱ ህዝቦች እንዲጋጩና አስከፊ ጉዳት እንዲደርስ ፅኑ ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች አሉ እነዚህ ኃይሎች ገንዘባቸውን መድበው በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አትጠራጠሩ!በዚህ ምክንያት ያጡትን ለማግኘት የሚጥሩ የሚፍጨረጨሩ ደፋ ቀና የሚሉ አሉና ልብ እንበል
የለውጡ አደናቃፊዎችም በዚህ ዘመቻ ተጠቃሚ ሊሆኑ ስለሚችሉ እንደሚቀላቀሉ አትጠራጠሩ!በጅማ የከሸፈው ጥረት ሌሎች አካባቢዎች ላይም ቢሞከር በፍጥነት እንዲከሽፍ በመላ ኦሮሚያ የሚገኙ ሙስሊም ክርስቲያን ወገኖች አሁን ነቃ ብለው አካባቢያቸውን መጠበቅ ይገባቸዋል::
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አትኩረው ዛሬ በሰጡት መግለጫ በጅማ አንድም የተቃጠለ ቤተክርስቲያን የለም ብለዋል
ኮሚሽነሩ በጅማ ብጥብጥ እንዲነሳ ሞክረው የከሸፈባቸው ኃይሎች በቅንጅት ተንቀሳቅሰው በኦሮሚያና በመላ አገሪቱ ሰላም እንዳይኖር ለማድረግ ስለሆነ ህብረተሰቡ እንደከዚህ በፊቱ ተቀናጅቶ በመስራት ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም ጠይቀዋል

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa