“ትናንትና ያዋረደንን፣ አዋርደነዋል፤ ትናንት የሰበረንን ሰብረነዋል” -ጠ/ሚ አቢይ አህመድ
“ የተከበራችሁ የባሌ ሽማግሌዎች፣ የኦሮሞ ወጣቶች፦ የነገ ተስፋዎች፤ እኔ በየቀኑ የባሌን ሶፍ ኡመር ዋሻን ቀዬ ውስጥ ስለማየው፣ ውሎዬም፣ አዳሬም ሶፍ ኡመር ውስጥ፣ ባሌ ውስጥ ስለሆነ፤ ባሌ የኦሮሞ ታሪክ የተጀመረበት፣ ባሌ የኦሮሞ ታጋዮች ቁጭ ብለው፣ ተረጋግተው ጠላቶቻቸው እንዴት መፍረስ እንዳለባቸው አጥንተው፣ አዲስ ፍልስፍና ፈጥረው፣ ከዚህ ጀምረው ኦሮሞንና ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣትና ለመግዛት ስለሚችሉ፣ ሶፍ ኡመር . . . የሶፍ ኡመርን ዋሻ ቀዬያችን ውስጥ ስንሰራ ታሪክ እንዲያስታውሰውና ለማስታወስ፣ ለማሳወቅ፣ ዓለም ይሄ ምንድን ነው ቢለን፣ “ የሶፍ ኡመር ዋሻ ይባላል፤ ትግላችን የጀመረበት፣ ማንነታችን የተጀመረበት ነው፤ ” ብለን ልንነግራቸው ነው። የሶፍ ኡመር ዋሻን ቀዬያችን ውስጥ የሚያዩ ሰዎች ምን እንደሆነና ለምን እንደሰራነው መገንዘብ ያዳግታቸዋል፡፡ ባሌ ግን ይህን መገንዘብ እይቸገርም፤ መጥታችሁ እዩት። ኦሮሞነት በስራ ይገለጻል፤ ኦሮሞነት በልማት ይገለጻል፤ ኦሮሞነት በፍቅር ይገለጻል። በልዩ ባህል፣ ወግና ስነምግባር ያደግን ስለሆን፣ ስድብ አናውቅም፤ ፍቅር ግን እናውቃለን። ኦሮሞ ስለሆን እራስን መካብ፣ በአሽሙር መናገር አንችልም፤ ሰርተን ማሳየት፣ ጽፈን፣ ጽፈን ዓለም ሊማርበት የሚችልበትን ሃሳብ ማፍለቅ ብንችልም በአሽሙር መናገርን ግን ኦሮሞነታችን ስላላስተማረን አንችልበትም። ኦሮሞ፦ ትናንት ንቆን፣ ሰብሮን፣ ዘርፎን፣ ኦሮሚያ ውስጥ ያለውን ሁሉ ግጦ የወሰደን፣ ልጆቻችሁ ታግለው፣ ሰባብ...