ልጥፎች

ከማርች, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የለውጥ ስራዎች መደገፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ

ምስል
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (TW) በቤልጂየም ብራሰልስ በሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ፅህፈት ቤት ፊት ለፊት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በትናንትናው እለት ተደርጓል፡፡ በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ዓለም አቀፍ ትብብር የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዳይሬክቶሬትም የድጋፍ ሰልፉን በተመለከተ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ በደብዳቤውያውም ህብረቱ የተደረገውን የድጋፍ ሰልፍ እንደተመለከተው ጠቅሶ፥ ህብረቱ ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ እንደቁልፍ አጋር እንደሚቆጥራት አስታውቋል፡፡ በሃገሪቱ የሚካሄዱ የለውጥ ስራዎችን መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀው ህብረቱ፥ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ስትራቴጂክ ግንኙነት ካላቸው ጥቂት ሃገሮች መካከል አንዷ መሆኗንም ጠቅሷል፡፡ ህብረቱ የኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ጠንቅቆ ይረዳል እንደሚረዳ በማውሳትም የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል። አያይዞም ህብረቱ በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ ቀውስ እንደሚያሳስበው በመግለጽም፥ በክልሉ ዓለም ዓቀፍ የስደተኞች እና የሰብአዊ መብት ሕግጋቶች እንዲከበሩ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያዊያን አንድነት የኢትዮጵያን ጠላቶች ያርበደብዳል!

ምስል
ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ሲንቀሳቀሱ ድሮም ለጣለታቸው አይበጁም በአገር ለመጣ ነገር ቀልድ የለም!ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊያን አገር ስለመሆኗ ሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች አሁን አይናቸውን ገለጠው በደንብ ይመልከቱ! በውስጥ የፖለቲካ ልዩነት ኢትዮጵያ የተዳከመች መስሏቸው ለቋመጡ ኃይሎች በአሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአደባባይ ወጥተው ያሳዩትን፤ያሰሙትንና በግልፅ ያስተላለፉትን ትልቅ መልዕክት በጥሞና መመልከት ብቻ ለጠላቶች በቂ ነው ልብ ያለው ልብ ይላል! ኢትዮጵያዊያን ታሪክን ደግመው እያሳዩ ነው ከ125 ዓመታት በፊት ጥጋበኛው ሶላቶ ሲመጣ ኢትዮጵያዊያን በውስጥ ልዩነት የነበራቸው ቢሆንም በአገር ጉዳይ ልዩነት አይኖርም ብለው በአንድነት ሆ ብለው ተነስተው ሶላቶውን ዶጋድመድ አደረጉ፤ለሁሉም ጥቁር ህዝቦች አርአያነታቸውን አሳዩ ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚችል በተግባር ያሳዩ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም አንበረከክም ብለው ሆ ብለው ተነስተዋል፤አገር ሻጭ ባንዳ ከህዝብና አገር የዘረፈውን ገንዘብ   ተጠቅሞ ቅጥረኞችን በማሰማራት ወደ ስልጣን መንበሩ የሚመለስበት ሁኔታ የለም!ሲያምረው ይቀራል! የወያኔ ባለስልጣናት ከሞት የተረፉቱ በአጉል ተስፋ ራሳቸውን እየደለሉ ከኢትዮጵያ የዘረፉትን ገንዘብ ለአገር አፍራሽ ቅጥረኞች   መበተናቸው የሚጠቅማቸው መስሏቸዋል ሲያምራቸው ይቀራል! በአሜሪካና ካናዳ የታየው ፍትሃዊ ተቃውሞ በአገር ቤትም ይቀጣጠላል!አሁን ሁሉም ለእናት አገሩ ዘብ ይቆማል! በአገር ቀልድ የለማ!በእናት አገራችን ጉዳይ ወሳኞቹ ህዝቦቿ ብቻ ናቸው ወያኔ በዘረፈውና ግብፅ በምትረጨው ገንዘብ ቀለብተኛ ሆኖ ፕሮፓጋዳውን ሲነፋ የሚውለው ቡደን ሁሉ ኢትዮጵያዊያን በአን ድ ነት ስለቆሙ ይፈር! የኢትዮጵያዊያን አንድነት የኢትዮ...

አሜሪካ ሱማሊያ ልካ እንዳላዋጋችን............

ምስል
ለህልውናዬ ሰጋሁ ያለችው አሜሪካ ሱማሊያ ልካ እንዳላዋጋችን ዛሬ ህግ ለማስከበር በሚደረግ የውስጥ ጉዳይ አንድን ሀገር እንደሁለት ተመለከተች፡፡ ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች፡፡ የተመድ ምክር ቤት ያለ መግባባት ተበተነ፡፡ በኢትዮጵያ ጉዳይ ገና ዓለም ቋንቋው እንደባቢሎን ይደበላለቃል፡፡ አሜሪካን በትግራይ ያለውን ሁኔታ ያየችበት ዓይን የተንሸዋረረ ነው፡፡ እንደ አሜሪካ ያለ የትም እየገባ የሚያምስ መርህ አልባ ሀገር ኤርትራንም ሆነ ኢትዮጵያን አሁን ባሉበት ሁኔታ ለመውቀስ ሞራል የለውም፡፡ የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ገብተው ከሆነ ጉዳዩ መታየት ያለበት ከመሰረቱ ነው፡፡ የኤርትራ መንግስት በትግራይ የመሸገው ወንበዴ የደህንነቴና የብሔራዊ ጥቅሜ ስጋት ነው ብሎ አምኗል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ይህ ወንበዴ የትም አይደርስምና አያሳስብም እኔ ሃላፊነት እወስዳለሁ ያለ መንግስት የለም፡፡ ህወሃት ሃላፊነት የሚወሰድለት መንግስት አይደለም፡፡ ታሪክ አንድ ዜጋ አደረገን እንጂ ኢትዮጵያን ቀብሮ በመቃብሯ ላይ ለመጨፈር ሙዘቃውን ያሳናዳ የታሪክ አራሙቻ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አሜሪካ አፍጋኒስታን ድረስ የወሰዳት የአፍጋን መንግስት አልቃይዳ የተባለውን አሸባሪ ቡድን መጥረግ የማይችል ስለሆነና እሷ ለደህንነቴ ሰጋሁ ስላለች ነው፡፡ አሜሪካ ብዙ አህጉር አቋርጣ አንድን አሸባሪ ቡድን ለማጥፋት ጦር ከሰበቀች፡፡ ኤርትራ ድንበሯ ስር የተሸጎጠውንና የሀገሩ መንግስት ጭምር የተቸገረበትን ቡድን ለማጥፋት ብትሞክር ጥፋቱ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ መንግስት ህዝቡን አስተባብሮ የሀገሩን ጠላትና የብሔራዊ ጥቅሙን እንቅፋት ቢያስወግድ ህግን ለማስከበር ያደረገው ዘመቻ እንጂ እንደ አሜሪካኖቹ ነዳጅ ለመማስ አልያም ቀጠና ለማመስ አይደለም፡፡ ይህ ቡድን የጎረቤት ሀገራትን ጭምር በሮኬት ያጠቃ...