የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የለውጥ ስራዎች መደገፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (TW) በቤልጂየም ብራሰልስ በሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ፅህፈት ቤት ፊት ለፊት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በትናንትናው እለት ተደርጓል፡፡

በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ዓለም አቀፍ ትብብር የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዳይሬክቶሬትም የድጋፍ ሰልፉን በተመለከተ ደብዳቤ ጽፏል፡፡
በደብዳቤውያውም ህብረቱ የተደረገውን የድጋፍ ሰልፍ እንደተመለከተው ጠቅሶ፥ ህብረቱ ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ እንደቁልፍ አጋር እንደሚቆጥራት አስታውቋል፡፡

በሃገሪቱ የሚካሄዱ የለውጥ ስራዎችን መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀው ህብረቱ፥ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ስትራቴጂክ ግንኙነት ካላቸው ጥቂት ሃገሮች መካከል አንዷ መሆኗንም ጠቅሷል፡፡
ህብረቱ የኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ጠንቅቆ ይረዳል እንደሚረዳ በማውሳትም የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል።
አያይዞም ህብረቱ በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ ቀውስ እንደሚያሳስበው በመግለጽም፥ በክልሉ ዓለም ዓቀፍ የስደተኞች እና የሰብአዊ መብት ሕግጋቶች እንዲከበሩ ጥሪ አቅርቧል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman