የኢትዮጵያዊያን አንድነት የኢትዮጵያን ጠላቶች ያርበደብዳል!

ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ሲንቀሳቀሱ ድሮም ለጣለታቸው አይበጁም በአገር ለመጣ ነገር ቀልድ የለም!ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊያን አገር ስለመሆኗ ሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች አሁን አይናቸውን ገለጠው በደንብ ይመልከቱ!

በውስጥ የፖለቲካ ልዩነት ኢትዮጵያ የተዳከመች መስሏቸው ለቋመጡ ኃይሎች በአሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአደባባይ ወጥተው ያሳዩትን፤ያሰሙትንና በግልፅ ያስተላለፉትን ትልቅ መልዕክት በጥሞና መመልከት ብቻ ለጠላቶች በቂ ነው ልብ ያለው ልብ ይላል!

ኢትዮጵያዊያን ታሪክን ደግመው እያሳዩ ነው ከ125 ዓመታት በፊት ጥጋበኛው ሶላቶ ሲመጣ ኢትዮጵያዊያን በውስጥ ልዩነት የነበራቸው ቢሆንም በአገር ጉዳይ ልዩነት አይኖርም ብለው በአንድነት ሆ ብለው ተነስተው ሶላቶውን ዶጋድመድ አደረጉ፤ለሁሉም ጥቁር ህዝቦች አርአያነታቸውን አሳዩ

ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚችል በተግባር ያሳዩ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም አንበረከክም ብለው ሆ ብለው ተነስተዋል፤አገር ሻጭ ባንዳ ከህዝብና አገር የዘረፈውን ገንዘብ  ተጠቅሞ ቅጥረኞችን በማሰማራት ወደ ስልጣን መንበሩ የሚመለስበት ሁኔታ የለም!ሲያምረው ይቀራል!


የወያኔ ባለስልጣናት ከሞት የተረፉቱ በአጉል ተስፋ ራሳቸውን እየደለሉ ከኢትዮጵያ የዘረፉትን ገንዘብ ለአገር አፍራሽ ቅጥረኞች  መበተናቸው የሚጠቅማቸው መስሏቸዋል ሲያምራቸው ይቀራል!

በአሜሪካና ካናዳ የታየው ፍትሃዊ ተቃውሞ በአገር ቤትም ይቀጣጠላል!አሁን ሁሉም ለእናት አገሩ ዘብ ይቆማል! በአገር ቀልድ የለማ!በእናት አገራችን ጉዳይ ወሳኞቹ ህዝቦቿ ብቻ ናቸው ወያኔ በዘረፈውና ግብፅ በምትረጨው ገንዘብ ቀለብተኛ ሆኖ ፕሮፓጋዳውን ሲነፋ የሚውለው ቡደን ሁሉ ኢትዮጵያዊያን በአንነት ስለቆሙ ይፈር! የኢትዮጵያዊያን አንድነት የኢትዮጵያን ጠላቶች እንደሚያርበደብድ ይታወቃልⵆ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman