ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2016 ልጥፎች በማሳየት ላይ

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ አባልነት የተሾሙት እነማን ናቸው?

ምስል
የጨፌ ኦሮሚያ ባካሄደው አምስተኛ የሥራ ዘመን ሁለተኛ ዓመት ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ አቶ ለማ መገርሳን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል። ይህንንም ተከትሎ አዲሱ ርእሰ መስተዳደር የክልሉን መንግስት ካቢኒ አባላት ለጨፌው አቅርበው አስፀድቀዋል። በአቶ ለማ መገርሳ ቀርበው ሹመታቸው በጨፌው ከፀደቀ በኋላ ቃለ መሃላ ከፈፀሙት 21 ተሿሚዎች መካከል 16 ቱ ከዚህ ቀደም በካቢኒ ውስጥ ያልነበሩ አዳዲስ ተሿሚዎች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥም ስምንቱ የኦህዴድ አባል ያልሆኑ እና በጥናት እና ምርምር ላይ ተሰማርተው የነበሩ ምሁራን ናቸው። የካቢኒ አባላቱ ዝርዝር የህይወት፣ የትምህርት እና ስራ ዳራ እንደሚከተለው ቀርቧል። አቶ ኡመር ሁሴን ኡባ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር   የትውልድ ስፍራ፦ አርሲ ዞን የትምህርት ዝግጅት፦ የመጀመሪያ ዲግሪ በኢኮኖሚክስ፣ ሁለተኛ ዲግሪ በኢንተርናሽናል ቢዝነስ። የስራ ልምድ፦ በአርሲ ዞን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ፣ ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ፣ የከተማ ልማት መምሪያ ሃላፊ በመሆን እና በተለያዩ ስፍራዎች በሃላፊነት ሲሰሩ ቆይተዋል። በመቀጠልም የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የኦሮሚያ ክልል የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እና ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ በመሆን አገልግለዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የግብርና ቢሮ ሃላፊ በመሆንም ሲ