በኦሮሚያ ክልል ሰሞኑን ሁከት ከተከሰተባቸው ወረዳዎች አብዛኞቹ ወደ መረጋጋት እየተመለሱ ነው

በኦሮሚያ ክልል ሰሞኑን ሁከት ከተከሰተባቸው ወረዳዎች አብዛኞቹ ወደ መረጋጋት እየተመለሱ ነው
በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ከ350 በላይ ወረዳዎች መካከል ሰሞኑን ሁከት የተከሰተባቸው 50 ወረዳዎች ናቸው።

የኦሮሚያ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ምክትል ኮሚሽነር ሰለሞን ታደሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ከእነዚህ 50 ወረዳዎች ውስጥ አብዛኞቹ ወደ መረጋጋት እየተመለሱ ነው።
ምክትል ኮሚሽነሩ በምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ከሚገኙ ሁለት ወረዳዎች እና ከነገሌ ቦረና አካባቢዎች በስተቀር ሌላው የኦሮሚያ ክፍል ወደ መረጋጋት መጥቷል።
የኢሬቻ በዓልን ተከትሎ በተወሰኑ የክልሉ ከተሞች የተፈጠሩት ሁከቶች ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማስከተላቸውንም ገልፀዋል።
የክልሉ ፖሊስ ከህዝቡ ጋር በመሆን በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ሁከቶችን መቆጣጠር መቻሉን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ፥ ፖሊስ የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ መጠቀም ያለበትን ሁሉ ሀይል ይጠቀማል ብለዋል።
በዋናነት ግን ህዝቡ ተረጋግቶ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄዎችን እንዲያቀርብ አቅጣጫ ማስያዝ ላይ ትኩረት ያደርጋል ነው ያሉት።
ምክትል ኮሚሽነር ሰለሞን የተፈጠሩት ሁከቶች ከፖሊስ ቁጥጥር ውጭ የሆኑባቸው ቦታዎች እንደነበሩም አንስተዋል።
አብዛኞቹ ሁከቶቹን የተቀላቀሉት አላማውን ያልተገነዘቡ ወጣቶች በመሆናቸው እነዚህን የነገ ሀገር ተስፋዎች በሀይል ማረም ተገቢ ባለመሆኑ ነው ፖሊስ ከፍተኛ ትዕግስት ያሳየው ብለዋል።
ከሰሞኑ ሁከት የተከሰተባቸው አካበቢዎች ከዚህ ቀደም ሰላማዊ የነበሩና ፖሊስ ሰፊ የፀጥታ ሀይል ያላሰማራባቸው በመሆናቸውና ክልሉ ሰፊ የቆዳ ስፋት ያለው መሆኑም በአንዳንድ አካባቢዎች ሁከቶቹ ከቁጥጥር ውጭ ሆነው እንደነበር አብራርተዋል።
በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የመንግስት እና የግል ንብረቶች መውደማቸውንም ነው የገለጹት።
ህዝብ እና ፖሊስ ተባብረው በሰሩባቸው አካባቢዎች ህዝቡ ወደ ተረጋጋ ማህበራዊ ህይወቱ እየገባ መሆኑንም ተናግረዋል።
የፌዴራል ፖሊስም ከክልሉ ፖሊስ ጋር በመጣመር በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ፀጥታ የማስከበር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በአጠቃላይ ያለ ህዝብ ተሳትፎ ፀጥታ እና መረጋጋትን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፥ መላው የኦሮሚያ ህዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ የአካባቢውን ሰላም ለማስፈን ከፖሊስ ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

የክልሉ ፖሊስ አሁንም ፀጥታን ከማስከበር ባሻገር የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በውይይት እንዲፈቱ ጥረቱን ይቀጥላልም ብለዋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman