ልጥፎች

ከጃንዋሪ, 2017 ልጥፎች በማሳየት ላይ

“Harka hanna bare dooluutu socho’a”

ምስል
Gantuun ummata ofii gante garaa ofiitiif kaachuu malee wanti beektu hinjiru.Gantoonni aanaalee gara garaa godina Shawaa bahaa tokko tokkos hanna baran Ummata irratti utuu raawwachaa jiranuu nidursina jedhanii socho’anis tibbana durfamaniiru.Dhimmichi akkana: Daandiin saffisaa Mojoo irraa hanga Hawaasaatti ijaaramu hanga tokko lafa qonnaan bulaa tuquun isaa akka hinoolle beekamaadha.Mootummaan ammoo kanaaf fala kaa’uudhaan qonnaan bulaan keenya akka hinmiidhamneef haala mijeesse. Falli mootummaan kaa’e beenyaa kaffaluudha,akkaataa murtee mootummaatiin qonnaan bulaan sababa ijaarsa daandii saffisaa kanaan lafasaa dhabu hektaara tokkoon birrii miliyoona 2 akka argatuuf murteeffameera.Akkaataa shallaggii kanaatiin qonnaan bulaan naannichaa kamiyyuu hammeentaa lafti qonnaa jalaa tuqameen beenyaa kan argatu ta’a.Waraabeessi kana beekuufi ummata keessa oolee bulu ammoo kana dhageenyaan mala malate. Qonnaan bultoota Naannawa Mojoo,Alam xeenaafi Maqii sababa hojii daandii saffisaa ka

የሾላ በድፍኑ አካሄድ ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም

ምስል
ከሰሞኑ በርካታ ሰዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰምተናል፤በሙስና የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተነግሯል መልካም ነው።አገራችን ከገባችበት አሳሳቢ ችግር አንፃር በማን አለብኝነት ወደ ጥፋት አረንቋ የተዘፈቁ ግለሰቦችን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ነው ሕዝብም ይደግፈዋል። ነገር ግን በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚውሉ ሰዎች ለፍርድ ሂደቱ እንቅፋት ይፈጥራል ካልተባለ በስተቀር ልክ ቀደም ሲል በቁጥጥር የዋሉ ግለሰቦች ጉዳይ ያለምንም መሸፋፈን ሲነገር እንደነበረው ሁሉ ከ130 በላይ ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች ማንነትና የተጠረጠሩበትም ጉዳይ በወቅቱ ለሕዝብ ይፋ መደረግ አለበት። እነ ማን ናቸው ስልጣናቸውን ተጠቅመው ፋብሪካዎችን ያቋቋሙት? እነ ማን ናቸው በሕንፃ ላይ ሕንፃ በሕዝብና መንግስት ገንዘብ የገነቡት? እነ ማን ናቸው ስልጣናቸውን ተጠቅመው የባለጉት?ወዘተ..ሕዝብ ይጠይቃል የኢህአዴግ አባላትም ይጠይቃሉ የሕዝብ የማወቅ መብት መከበር አለበት! የተጠርጣዎቹን ስም ዝርዝር በወቅቱ ይፋ ማድረግ የሕዝብን የፀረ ሙስና ትግል ያጠናክራል፤የሕዝብ አጋርነትንም ይጨምራል።የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እያለ ጉዳዩን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የገለፀበት ምክንያትም ለእኔ ግልፅ አይደለም፤ምናልባት አገሪቷ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በመተዳደር ላይ ስለሆነች ይሆን?እንጃ።ጎበዝ “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” እንዳይሆን ጠንቀቅ ይበጃል

መልዕክት ለአዲስ አበባው ዳውድ ኢብሳ አድናቂዎች

ምስል
ዳውድ ኢብሳ ማነው? ለምትሉ ወገኖች አቶ ዳውድ ኢብሳ ሌንጮ ለታ ሌላ ድርጅት መስርቶ ከተገለለ ወዲህ የኦነግ ሊቀመንበር ሆነው በመንቀሰቀስ ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች አለቃ ናቸው ። የአዲስ አበባው ዳውድ ኢብሳ በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበርና የወቅቱ የመድረክ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር መረራ ጉዲና በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል። ይህ ሰው ፊንፊኔ አዲስ አበባ  ውስጥ እየኖሩ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ቡድኖችና የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ያቀዱትን የብጥብጥና የሁከት ስልት ወይም ስትራቴጂ ለማሳካት ሌት ተቀን ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ስለመሆናቸው ቁልጭ ብሎ እንደሚታይ ተግባራቸው ምስክር ነው፤ሰውዬው በቁጥጥር ስር ውለው ከታሰሩ ወዲህ በደጋፊና አድናቂዎቻቸው ኢትዮጵዊው ማንዴላ ተብለው ሲንቆለጳጰሱ እየሰማን ነው እረ እንዴት እንዴት? ዶክተር መረራ ጉዲና ባለፉት 25 አመታት አገራችን ውስጥ በተዘረጋው ዴሞክራሲዊ ስርዓት እጅግ በጣም ከተጠቀሙ ዜጎች ውስጥ በመጀመሪያ ረድፍ ላይ የሚጠቀሱ ሰው ናቸው።በኢህአዴግ የዘመናት ትግል ውጤት አማካኝነት አገሪቷ ውስጥ በተፈጠረው የብዙሃን ፓርቲ ስርዓት ተጠቅመው ከአንድም ሁለት ፓርቲ በመመስረት መንቀሳቀስ የቻሉት ይህ ሰው በአንድ የምርጫ ዘመን ባገኙት የደጋፊዎቻቸው ድምፅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል መሆን ችለዋል።በአምስት አመታት ቆይታቸውም ኢህአዴግን በአደባባይ ከመስደብና ከማብጠልጠል አልፈው ለወከሏቸው ዜጎች አንድም ጠብ የሚል ነገር ማስገኘት አልቻሉም። ጊዜው ደርሶ ከምክር ቤት ውጭ ከሆኑ ወዲህም በሰላማዊ ትግል ስም ሕጋዊና ሕገ ወጥ አካሄድን ደባልቀው በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው አገር ያወቀ