መልዕክት ለአዲስ አበባው ዳውድ ኢብሳ አድናቂዎች

ዳውድ ኢብሳ ማነው? ለምትሉ ወገኖች አቶ ዳውድ ኢብሳ ሌንጮ ለታ ሌላ ድርጅት መስርቶ ከተገለለ ወዲህ የኦነግ ሊቀመንበር ሆነው በመንቀሰቀስ ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች አለቃ ናቸው
የአዲስ አበባው ዳውድ ኢብሳ በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበርና የወቅቱ የመድረክ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር መረራ ጉዲና በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል።
ይህ ሰው ፊንፊኔ አዲስ አበባ  ውስጥ እየኖሩ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ቡድኖችና የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ያቀዱትን የብጥብጥና የሁከት ስልት ወይም ስትራቴጂ ለማሳካት ሌት ተቀን ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ስለመሆናቸው ቁልጭ ብሎ እንደሚታይ ተግባራቸው ምስክር ነው፤ሰውዬው በቁጥጥር ስር ውለው ከታሰሩ ወዲህ በደጋፊና አድናቂዎቻቸው ኢትዮጵዊው ማንዴላ ተብለው ሲንቆለጳጰሱ እየሰማን ነው
እረ እንዴት እንዴት? ዶክተር መረራ ጉዲና ባለፉት 25 አመታት አገራችን ውስጥ በተዘረጋው ዴሞክራሲዊ ስርዓት እጅግ በጣም ከተጠቀሙ ዜጎች ውስጥ በመጀመሪያ ረድፍ ላይ የሚጠቀሱ ሰው ናቸው።በኢህአዴግ የዘመናት ትግል ውጤት አማካኝነት አገሪቷ ውስጥ በተፈጠረው የብዙሃን ፓርቲ ስርዓት ተጠቅመው ከአንድም ሁለት ፓርቲ በመመስረት መንቀሳቀስ የቻሉት ይህ ሰው በአንድ የምርጫ ዘመን ባገኙት የደጋፊዎቻቸው ድምፅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል መሆን ችለዋል።በአምስት አመታት ቆይታቸውም ኢህአዴግን በአደባባይ ከመስደብና ከማብጠልጠል አልፈው ለወከሏቸው ዜጎች አንድም ጠብ የሚል ነገር ማስገኘት አልቻሉም።
ጊዜው ደርሶ ከምክር ቤት ውጭ ከሆኑ ወዲህም በሰላማዊ ትግል ስም ሕጋዊና ሕገ ወጥ አካሄድን ደባልቀው በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል
ዶክተር መረራ ለ40 ዓመታት ስለሽብርተኝነት መጥፎነት ሲያስተምሩ ኖረው በሽብር ተግባር ውስጥ ሊሳተፉ እንደማይችሉ መናገራቸው ተሰምቷል፤ይህ አባባል አሁን የቀረበባቸውን ክስ ለመከላከል ያቀረቡት የመከላከያ ነጥብ ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት ያለው አይመስለኝም።
ስለሽብርተኝነት መጥፎነት ሳስተምር ኖሬአለሁ የሚሉት ሰው በውጭ ከሚገኙ ሽብርተኛ ቡድኖች ጋር በተደጋጋሚነት መገናኘት ለምን አስፈለጋቸው?ዶክተር መረራ ባለፈው ክረምት አሜሪካ ሚኒሶታ ከሚኖሩ ጠባብ ኃይሎች ጋር የሰፊ ጊዜ ቆይታ እንደነበራቸው ይታወቃል ከእነ ጀዋር መሃመድ ጋርም ተገናኝተው ሞቅ ያለ አቀባበል የተደረገላቸው ስለመሆኑ ታይቷል፤ተሰምቷል እንደውም የጀግና አቀባበል እንደተደረገላቸው በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል።
ሰውዬው ከእነዚህ ኃይሎች ጋር በተደጋጋሚነት ሲገናኙ በሆደ ሰፊነት ዝም ሲል የቆየው የኢህአዴግ መንግስት በስተመጨረሻ የዶክተሩ አካሄድ ከጫፍ መድረሱን ሲረዳ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረጉና እንደማንኛውም ዜጋ ከሕግ በታች እንጂ ከሕግ በላይ መሆን እንደማይችሉ በተግባር ማሳየቱ ተገቢ ነው።
አሁን ዶክተር መረራ ከአንዳርጋው ፅጌ ጋር እየተነፃፀሩ የአንድነት ኃይሎችም ልክ ለአንዳርጋቸው ፅጌ እንጮሁት ለመረራም መጮህ አለባቸው የለባቸውም የሚል ክርክር እየተሰማ ነው፤ይህ ሁኔታ ባልተቀደሰ ጋብቻ የተገናኙትን ጠባብና ትምክህተኛ ኃይሎች ያቃቃረ መሆኑ ተስተውሏል።

እንግዲህ በ2007 ዓ.ም አገራዊ ምርጫ ቀድመው ካርድ ባለመውስደቸው በተወዳደሩት የምርጫ ክልል ድምፅ መስጠት ስላልቻሉት ዶክተር መረራ ጉዲና ሕገ ወጥ አካሄድ እጅግ በጣም ብዙ ነገር ማለት የሚቻል ቢሆንም በዚሁ ይብቃኝ።በአዲስቷ ኢትዮጵያ ማንኛውም ሰው ከሕግ በታች እንጂ ከሕግ በላይ መሆን አይችልም፤ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢሆኑ ከሕግ በታች ናቸው። ዋሸሁ እንዴ? አይደለም እንዴ?

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa