የሾላ በድፍኑ አካሄድ ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም

ከሰሞኑ በርካታ ሰዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰምተናል፤በሙስና የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተነግሯል መልካም ነው።አገራችን ከገባችበት አሳሳቢ ችግር አንፃር በማን አለብኝነት ወደ ጥፋት አረንቋ የተዘፈቁ ግለሰቦችን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ነው ሕዝብም ይደግፈዋል።

ነገር ግን በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚውሉ ሰዎች ለፍርድ ሂደቱ እንቅፋት ይፈጥራል ካልተባለ በስተቀር ልክ ቀደም ሲል በቁጥጥር የዋሉ ግለሰቦች ጉዳይ ያለምንም መሸፋፈን ሲነገር እንደነበረው ሁሉ ከ130 በላይ ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች ማንነትና የተጠረጠሩበትም ጉዳይ በወቅቱ ለሕዝብ ይፋ መደረግ አለበት።
እነ ማን ናቸው ስልጣናቸውን ተጠቅመው ፋብሪካዎችን ያቋቋሙት? እነ ማን ናቸው በሕንፃ ላይ ሕንፃ በሕዝብና መንግስት ገንዘብ የገነቡት? እነ ማን ናቸው ስልጣናቸውን ተጠቅመው የባለጉት?ወዘተ..ሕዝብ ይጠይቃል የኢህአዴግ አባላትም ይጠይቃሉ የሕዝብ የማወቅ መብት መከበር አለበት!

የተጠርጣዎቹን ስም ዝርዝር በወቅቱ ይፋ ማድረግ የሕዝብን የፀረ ሙስና ትግል ያጠናክራል፤የሕዝብ አጋርነትንም ይጨምራል።የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እያለ ጉዳዩን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የገለፀበት ምክንያትም ለእኔ ግልፅ አይደለም፤ምናልባት አገሪቷ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በመተዳደር ላይ ስለሆነች ይሆን?እንጃ።ጎበዝ “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” እንዳይሆን ጠንቀቅ ይበጃል

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa