በፍጻሜው ጦርነት-ክብርና ፍቅር ለትግራይ ወገናችን
ትግራይን በደንብ ከሚያውቁ ‘’የመሀል አገር ሰዎች ‘’አንዱ ነኝ፡፡በዚህም ራሴን እንደ ዕድለኛነት እቆጥራለሁ፡፡ከማይጨው እስከ ዛላንበሳ፣ከአብይአዲ እስከ ሽረ እንዳስላሴ፣ከአክሱም አስከ አድዋ፣ከአዲግራት እስከ አዲዳዕሮ፣ ከመቀሌ እስከ እንዳባጉና….አብዛኞቹን የትግራይ ከተሞችና ገጠሮች አውቃለሁ-ከ30 ዓመታት በፊት!!የትግራይን ምድርና የህዝቡን አኗኗር በአካል ከማወቄ በፊትም በት/ቤት ደረጃ አብረውኝ የተማሩ የምወዳቸው ጓደኞችና የማከብራቸው አስተማሪዎች (የትግራይ ልጆች) ነበሩ፡፡ከልብ የምወደው የጥ/ቤትና የሰፈር ጓደኛየ ገብረኪዳን ስዩምንና የ7ኛ ክፍል አስተማረየን ጋሸ ይህደጎ ኃይሉን መቼም ቢሆን የምረሳቸው አይደሉም፡፡ጋሽ ይህደጎ እጅግ ጨዋ፣መካሪና ጎበዝ ተማሪን አበረታች ስለነበር ተማሪዎቹ በተለየ ሁኔታ ክብርና ፍቅር ነበረን፡፡በት/ቤት ጓደኞቸና አስተማሪዎቸ ጨዋነትና እውነተኛነት ምክንያት ለትግራይ ተወላጆች የተለየ ክብር ኖሮኝ እንዳደኩ አስታውሳለሁ፡፡በዚህ ዓይነት ስነልቦና ውስጥ እያለሁ ነበር ትግራይን በአካል የማወቅ ዕድል የገጠመኝ፡፡በእርግጥም የአብሮአደግ ጓደኞቸና አስተማሪዎቸ ጨዋ ባህሪና እውነተኛነት ከትግራይ ህዝብ ባህሪ የተቀዳ መሆኑን ተረዳሁ፡፡እውነት ነው የምላችሁ አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ጨዋና እውነት ነው ብሎ ለሚያምንበት ነገር ሟች ነው፡፡ጨዋነትና ለእውነት ሟችነት የትግራይ ህዝብ ሀብቶች ናቸው፡፡መዋሸት፣ማበል፣ማጭበርበር፣ በሰው ላይ ማሴርና ክፋት መስራት በትግራይ ህዝብ ዘንድ የተነወሩ ባህሪያት ናቸው፡፡የትግራይ ህዝብ ለሀገሩ ለኢትዮጵያ ያለው ፍቅርና ‘’ለመሀል አገር ሰው ‘’የሚያሳየው አክብሮት ልብ ይነካል፡፡የትግራይ ጎረምሳ እጅግ ከተቆጣብህና ከተናደደብህ ‘’በቴስታ ‘’ከመሬት ይደባልቅህ ይሆናል እንጂ እንደዋልጌው ጌታቸው ረዳ የምርጥ ስ...
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ