ልጥፎች

ከጁን, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

ምስል
ፊንፊኔ ግንቦት 28፣2011 (ቶለዋቅ ዋሪ) ዶክተር ንጉሴ ምትኩ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ፡፡ ዶክተር ንጉሴ የህዝብ ተወካች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ ነው በዋና ስራ አስፈፃሚነት የተሾሙት፡፡ የቀድሞው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ስዩም መኮንን በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው ሹመቱ የተካሄደው፡፡ ሹመቱ በምክር ቤቱ አባላት አስተያየት ተሰጥቶበት በአራት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡ ምንጭ:FBC

Ergaa Ayyaana Iid alfaxiir I/A/Pi/M/N/Oromiyaa

ምስል
Hawaasa musliimaa maraan baga ayyaana sooma hiikkaa/ id al faxiiriin nagayaan isin gahe. Idal fixriin guyyaa ga mmachuu guyyaa maatii ollaa fi firaa wajjiin akkasumaas guyyaa waan qabanirraa qoodanii hiyyeessaa waliin jaalalaaf gammachuun dabarsan, guyyaa kan rakkateef dhaqqaban,kan dhibameef aafiyaa, dhala namaa maraaf waan gaarii hawwuudhaan baga ittiin nu gahe waliin jedhaniidha. Ji’aan Ramadaanaa baranaa ammo Ji’aa Jaalalli diiniin islaamummaa itti dhugoome miidhaginni, rakkoon majilisaa hiikkatee karaa qabatee tokkummaa fi gamtaan obbolaa keenya itti mirkanaawe, islaamummaan nageenya, islaamummaan kan walitti muufale afooyitulellaah jadhee ittiin walitti araaramu, islaamummaan qabbanaa fi miidhagina, jaalalaa fi kabajni dhala namaaf qabnu, jaalalli obbolummaa firaa fi ollaa qabnu gochaan miidhagee itti mullatee darbeedha. Keessattuu Jaalalaa fi hammachuun obbolaa keenya naannoolee Ollaa waliin qabnu akkaataa diiniin islaamummaa ajajuun waliin hafxiraa tokkoon keenya isa

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ1440ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ወር ጾም ፍቺ፣ ዒድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት:

ምስል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ1440ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ወር ጾም ፍቺ፣ ዒድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ለ1440ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ወር ጾም ፍቺ፣ ዒድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ዒድ አል ፈጥር - የጾም ወር ማጠናቀቂያና መሸኛ በዓል ነው። በረመዳን ወር መጨረሻ እና በሸዋል ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ የሚውል በዓል ነው ዒድ-አልፈጥር። በቅዱሱ የረመዳን ወር ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ሙስሊሙ ራሱን ከመብልና መጠጥ ከማቀብ ባለፈ በመልካም እና በጎ ተግባርም መትጋት ይጠበቅበታል። በዚህ ረገድ፣ ነቢዩ መሐመድ (ሠለላ አለይህ ወሠለም) “አስከፊ ንግግር እና ተግባራትን ያልተወ ሠው ከምግብና ከመጠጥ መታቀቡ ብቻ በአላህ ዘንድ ከቁምነገር የሚገባ አይደለም” በማለት ትክክለኛውን መንገድ ማመላከታቸው በሐዲስ ሰፍሮ ይገኛል። በመሆኑም በጾምና ሰላቱ፣ በምስጋናና በልግስና ታጅቦ ሠላሳ ቀናትን የሚዘልቀው የረመዳን ወር ነፍስን አለምላሚ ሥጋን ግን ጎሳሚ፣ ከዚያም በተጨማሪ ፈታኞቹ ቀናት ካለፉ በኋላ የሚመጣው አዲስ ቀን፣ የኢድ በረከትን የታደለና ድካምንም የሚያስረሳ ተደርጎ ይወሰዳል። በእምነታችን የተነሳ ትዕዛዛቱን ለመፈፀም በጽናት የምንቀበለው መከራ ሁሉ ከባድ ቢሆንም ማለፉ ግን አይቀሬ ነው። ያልፋል። አስተላለፉ ግን ‹ሲምር ያስተምር› እንደሚባለው ምሕረትም ትምህርትም አግኝተንበት ነው። የረመዳን ወርና መሸኛው ኢድ አል ፈጥር በዓል ከመነሻ እስከመድረሻ ያለው ሥርዓት በእንዲህ ዓይነቱ በረከት የታደለ ነው። የረመዳን ወር የጾምና የመታዘዝ፣ የድካምና የመፈተንም ወቅት ነው። ነገር ግን ከሚበላባ