ሰውዬውን የያዘው ጋኔን አሁንም አለበት!
ለውጡ መጣሁ መጣሁ ሲል በነበረበት ወቅት ከሶስት አመታት በፊት በነበረው የስልጣን ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ በሚሰጠው መግለጫ ከአንደበቱ የሚወጡ ቃላት ለከት አልነበራቸውም።
የኦሮሞ ወጣቶች(ቄሮዎች) ሲያደርጉት የነበረውን ትግል ሲያንቋሽሽ ነበር፤እንዲያውም "የያዛቸው ጋኔን ሲለቃቸው ተቃውሞው ይቆማል" ብሎ በምፀት ተናግሯል።
ተቃውሞው ሲበረታበት ለከት በሌለው አንደበቱ በአደባባይ ያለውን ለማስተባበልና ይቅርታ ለመጠየቅም ተገድዶ እንደነበር ይታወሳል።
ጌታቸው ረዳ አሁንም በጋኔን ተይዞ ተጠፍንጎ እንዳለ ከአንደበቱ የሚወጡ ቃላት ማረጋገጫ ናቸው።
ይህ ሰው የጥላቻ ንግግር ህግን በመጣስ ላይ ይገኛል።በአደባባይ ባለስልጣናትን በስም እየጠራ" ወፈፌ" እያለ ሲሳደብ ታይቷል፤ተሰምቷል።
ለነገሩ ተስፋ ከቆረጠ ሰው የሚጠበቀውን ነው በማድረግ ላይ የሚገኘው።ጌተቸው ረዳን ጨምሮ ሸሽተው መቀሌ የገቡ የቀድሞ ባለስልጣናት(ይህን አገላለፅ አምርረው ይጠሉታል) በሚሰጧቸው የሚዲያ ቃለ መጠይቅ ውስጥ የሚነበብ ቁጭትና መንገብገብ ይታያል።እንግዲህ ምንም ማድረግ አይቻልም!
ለኦሮሚያ መሬት ዘረፋ ተጠያቂው የኦሮሞ ባለስልጣናት ናቸው ብሎ እንደ ገደል ማሚቱ ለአመታት የተባለውን በመደጋገም ላይ የሚገኘው ጌታቸው ረዳ እርሱና መሰሎቹ በኦሮሚያም ሆነ በሌሎቹ የአገራችን ክፍሎች የተሰራው ወንጀል ሁሉ አዘጋጅና አሰተባባሪ አቀናባሪ ራሳቸው መሆናቸውን ዘንግተዋል።"የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ