ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለረመዳን ጾም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ



ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ የሚጀመረው የረመዳን ጾምን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዚህ ዓመት የረመዳን ወር የሚውለው ዓለም በኮሮና በተጠቃችበትና ወረርሽኙን ለመከላከል አለመጨባበጥ፣ መራራቅና በቤት መወሰን ዋና የመከላከያ መንገዶች ሆነው በመላው ዓለም በሚተገበሩት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡
ነብዩ መሐመድ የወረርሽን መስፋፋት ለመከላከል ካስተማሩት አንዱ የሰዎችን እንቅስቃሴዎች መገደብ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
“ንጽሕና የእምነት ክፍል ነው በማለት ነብዩ እንዳስተማሩት የራሳችንን፣ የቤተሰባችንን፣ የአካባቢያችንን ንጽሕና በመጠበቅ ኮሮናን በእምነትም በምግባርም እንከላከለው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
“የረመዳን ወር አንዱ ትልቅ እሴት ዘካና ሰደቃ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለሌሎች ማካፈል፣ ለሌሎች መትረፍ መቻል ነው፣ ለሌሎች የሚሰጥ በጎ ነገር ለሰጪው ደስታን፣ ለተቀባዩ ደግሞ የኑሮ ድጋፍን የሚያስገኝ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
የዚህ ዓመት ዘካችንና ሰደቃችን ንግዳቸው የተቀዛቀዘባቸው፣ የቤት ክራይ የሚከፍሉትን ላጡ፣ የትምህርት ቤት ክፍያን ለመክፈል የተቸገሩ፣ ልጀቻቸውን ለመመገብ የከበዳቸውን እንዲያስባቸው እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡
ረመዳን የመጣው በሚያስፈልገን ጊዜ ነውና ለወቅታዊ ችግራችን መፍቻነት እንጠቀምበት፤ ለመልካም ስራ ተሽቀዳደሙ በማለት ቁርዓን እንዳስተማረን እገዛችንን ከሚፈልጉ ወገኖቻችን ጎን ለመቆም እንሽቀዳደም፣ የገንዘብ አቅም የሌለን ሰዎች ሁሉ በመልካም ተግህባር ሁሉ እንሰማራ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
ረመዳን የመሰባሰቢያ ወቅት መሆኑን ሁላችንም የሚንገነዘብ ቢሆንም ያለንበት ወቅት ይህን እንዲንከውን አልፈቀደልንም፤ በአካል ለመሰብሰብ ብንቸገርም በተግባርና በመንፈስ አብረን መሆናችንን ማሳየት ይቻላል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
“የኮሮና ወረርሽኝ ለብዙ ነገሮቻችን ተቃራኒ ሆኖ የመጣ ነው፤ መሰባሰብን፣ መቀራረብን፣ መጨባበጥን፣ ለወረርሽኙ መስፋፈያ እየተጠቀመበት ነው፤ በዚህ ምክንያት ከእንደዚህ ነባር ልማዶቻችን ለጊዜው እንዲንለይ ተገደናል፤ ስለዚህ የዘንድሮን ረመዳን በየቤታችን ሆነን በቤተሰብ ደረጃ ብቻ አካላዊ ርቀታችን ጠብቀን እንዲናከብረው ተገደናል፤ ይህንን የችግር ወቅት በፈጣሪ እርዳታና በጋራ ጥረታችን አልፈን ረመዳንን እንደ ጥንቱ እሴቶቻችን ጠብቀን እንደምናከብረው ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፡፡
በዚህ የተቀደሰ የረመዳን ወር ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ የነባር እምነቶች ተከታዮችና ሁሉም ኢትዮጵያውያኖች ሁሉ በዚህ ወረርሽኝ ላይ በጋራ እንዲረባረቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
VIA:EBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa