ጥቂት ሃሳቦች ስለ ሞልቃቃው አሸባሪ ቡድን
የህወሃት አሸባሪ ቡድን የመንግስትን የተናጥል የተኩስ አቁም አዋጅ በሌለ አቅሙ በመናቅ ላይ እንደሚገኝ እየተስተዋለ ነው ይህ ሞልቃቃ አሸባሪ ቡድን የመሞላቀቁን ልክ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን ዘርዝሮ አቅርቧል
ሞልቃቃው አሸባሪ ካቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ መሰረታዊ አገልግሎቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቀድ የሚለው ይገኝበታል
ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ የኤሌክትሪክ የቴሌኮሙኒኬሽን የባንክና የህክምና አገልግሎቶች የሚጠቀሱ ናቸው
እነዚህ አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ እንዲደርሱ አሸባሪው ቡድን የበጣጠሳቸው የኤሌክትሪክና የተሌኮሙኒኬሽን መስመሮች እንዲጠገኑ እንዲሁም ቡድኑ በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ያፈራሳቸው ድልድዮች የአስፓልት መንገዶችና የአውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲጠገኑ አገር ከመቶ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጋለች
የተጠቀሱ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚቻለው ገንዘብ ሲኖር መሆኑ ይታወቃል ገንዘብ ከሌለ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት እንደማይቻል ግልፅ ነው
ስለዚህ ሞልቃቃው አሸባሪ የወያኔ ቡድን መሞላቀቁን አቁሞ በስልጣን ዘመኑ ከኢትዮጵያ ህዝብ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች ያስቀመጠውን በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ በማድረግ የጠየቃቸውን አገልግሎቶች ማግኘት ይችላል የአገር ሃብት ተዘርፎ በውጭ ባንኮች እንዲቀመጥ የተደረገው ለዚህ ክፉ ጊዜ ካልዋለ ለመቼ ሊሆን ነው?
ሌላው አስቂኝ የአሸባሪው ቅድመ ሁኔታ በማንነታቸው የታሰሩ ይፈቱ የሚል ነው በሞልቃቃው አሸባሪ ቡድን እሳቤ እነ አቶ ስብሃት ነጋ በማንነት ችግር ምክንያት ነው የታሰሩት፤ ግሩም እይታ ነው
እውነትም ሞልቃቃ አሸባሪ ቡድን!!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ