የአሸባሪዎቹን ቡድኖች ወያኔና ኦነግ ሸኔን ለሚናፍቁቱ

መሃል አገር ተቀምጣችሁ ወያኔ ተመልሶ ይመጣል ብላችሁ ተስፋ በማድረግ ላይ ያላችሁ ወገኖች ተስፋችሁን ቁረጡ

አሸባሪዋ ወያኔ የምዕራባዊያን ድጋፍ ቢኖራትም ተመልሳ በመምጣት ኢትዮጵያን የማስተዳደር አቅም በፍፁም የላትም፤አሁን ባዶ ፉከራዋን ብቻ ነው በፕሮፓጋዳ ማሽኖቿ በማሰማት ላይ ያለችው

የወያኔ ታጣቂዎች ወደ መሃል አገር እየገሰገሱ ነው የሚል የሃሰት መረጃ ስታገኙ ፊታችሁ በተስፋ ሲፈካ፤የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ወሰደ የሚል መረጃ ስታገኙ ደግሞ ፊታችሁ የሚጨፈግግ እንዳላችሁ እየተስተዋለ ነው

በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ውስጥ ዕድል ገጥሟችሁ በመስራት ላይ የምትገኙ የአሸባሪ ቡድን ደጋፊዎች የሚሻላችሁና የሚበጃችሁ በተመደባችሁበት የስራ ዘርፍ ላይ በማትኮር ውጤታማ መሆን ብቻ ነው

ከዚህ ውጭ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥም ሆነ በግል ተቋማት ውስጥ ቦታ ይዘህ/ሽ ወያኔ ተመልሶ ይመጣል ብለህ/ሽ ስትናፍቂ ብትውይ ምንም ጠብ የሚል ነገር ሊኖር አይችልም

ይልቅ የሚሻለው በተመደባችሁበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን መትጋት ነው፤አለበለዚያ ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ብዙ ስራ አጥ ወገኖች ስላሉ ያገኛችሁት ዕድል የጊዜ ጉዳይ  ነው እንጂ ሊነጠቅ ይችላል ነገ ሌላ ቀን ነው!በመሃል አገር የአሸባሪውን የሃሰት ፕሮፓጋዳ በመቀበል ስትንቶሶቶሱ ብትውሉ ምንም የሚመጣ ለውጥ የለም ተጠንቀቁ!

አንዳንዶቻችሁ ልክ እንደ ቀድሞ ተሰብስባችሁ ወያኔ በምትሰጠው ተልዕኮ ላይ በመወያየት ተልዕኮ ለመፈፀም ያምራችኋል፤እንግዲህ ሲያምራችሁ ይቅር፤አንዳንዶች ደግሞ ባላችሁበት የስራ ዘርፍ ስራን በማጓተት ተፅዕኖ ለመፍጠር ትጥራላችሁ ይህም የአይና አውጣነታችሁን ልክ ያሳያል

ኦነግ ሸኔን በመናፈቅ ላይ ያላችሁ ወገኖችም ምንም ተስፋ የምታደርጉት ነገር የለም፤ ኦነግ ሸኔ በተለይም የወያኔ ተላላኪነቱን ካወጀ ወዲህ በሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ታንቅሮ የተተፋ አሸባሪ ቡድን ነው

በተለያዩ አካባቢዎች ተደብቆና ሁኔታዎችን አይቶ በሚፈፅመው ጥቃት ለወያኔ ድጋፍ ሆኖ መምጣት ይችላል ብላችሁ በማሰብ ተስፋ ካደረጋችሁ እጅግ በጣም የዋህ ናችሁ ማለት ነውስለዚህ ለእናንተም የሚበጀው ተስፋ በመቁረጥ የግል ኑሮአችሁን ማሻሻል በምትችሉበት ሁኔታ ላይ በማትኮር የሚጠበቅባችሁን ግዴታ እየተወጣችሁ መኖር ብቻ ነውአንተ ማን ነህ ይህን ምክር ሰጪ ለምትሉኝ ሁሉ እኔ ባለ ተራው ነኝ! በሰላም ወሉ!


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman