መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከዛሬ ጀምሮ የተኩስ ማቆም ውሳኔ አሳልፈዋል
መንግስትና ኦነግ ከዛሬ ጀምሮ ተኩስ በማቆም የኦነግ ሰራዊት በጥቂት ቀናት ወደ ካምፕ እንዲገባ ውሳኔ አሳለፉ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከዛሬ ጀምሮ የተኩስ ማቆም ውሳኔ አሳልፈዋል። ከዚህ በተጨማሪም የኦነግ ሰራዊት በጥቂት ቀናት ውስጥ ካለበት ጫካ ወጥቶ ወደ ካምፕ እንዲገባም ውሳኔ አሳልፈዋል። መንግስት እና ኦነግ ውሳኔዎችን ያሳለፉት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት በዛሬው እለት በአምቦ ከተማ ባዘጋጀው የእርቅ ስነ ስርአት ላይ ነው። በዛሬው እለት በተዘጋጀው የእርቅ ስነ ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ወጣቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች እና የአምቦ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በመድረኩ ላይም መንግስት እና ኦነግ በኦሮሞ ባህል መሰረት ኮርማ በሬ በማረድ በይፋ የእርቅ ስነ ስርአት ፈጽመዋል። ሁለቱም አካላት ከዚህ በኋላ ወደ ደም መፋሰስ እንደማይገቡ እንዲሁም ያለፈውን ነገር በመተው ስለወደፊቱ ብቻ በጋራ ለመስራት በእርቅ ስነ ስርዓቱ ቃል ገብተዋል። በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከስምምነት የደረሱባቸው ዝርዝር የውሳኔ ነጥቦች ይፋ ተደርጓል። ዝርዝር ስምምነቱንም የቴክኒክ ኮሚቴውን በመወከል የፖለቲካ ተንታኝ እና አክቲቪስት አቶ ጀዋር መሃመድ ያቀረቡ ሲሆን፥ ሁለቱንም አካላት በማነጋገር በዝርዝር ውሳኔው ላይ መደረሱን አስታውቀዋል። በዚሀም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር መካከል ጦርነት መቆሙን አስታውቀዋል። ወደ ግጭት የሚያስገቡ ትንኮሳዎችን ሙሉ በሙሉ መከልከሉን እ