በእነ ጄኔራል ታደሰ ወረደ የክስ መዝገብ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

 

በእነ ጄኔራል ታደሰ ወረደ የክስ መዝገብ የተከሰሱ 74 ተከሳሾች ላይ የተመሰረተውን ክስ ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ
ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ጨምሮ በ74 ተከሳሾች ላይ የተመሰረተውን የዐቃቢ ሕግ ክስ ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡
በእነ ጄኔራል ታደሰ ወረደ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የህውሓት ወታደራዊ ቡድን አመራርና አባላት ናቸው የተባሉ አጠቃላይ 74 ተከሳሾች ሲሆኑ፥ ከእነዚህ ውስጥ 20 ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።
ተከሳሾቹ ከህውሓት የሽብር ቡድን ተልዕኮ ተቀብለው ወታደራዊ ቡድን በማደራጀት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በፌደራል ፖሊስ እንዲሁም በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ጥቃት ማድረስ ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ክስ አንደተመሰረተባቸው ይታወቃል ።
ትላንት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ-ሽብርና ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀረቡት ኮ/ል ገ/መስቀል ገ/ኪዳን እና ኮ/ል ዶክተር አለምብርሃንን ጨምሮ 19 ተከሳሾች ሲሆኑ፥ አንድ ተከሳሽ በህመም ምክንያት ከማረሚያ ቤት አለመቅረቡ ተገልጿል።
ፍርድ ቤቱ በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ከ1ኛ እሰከ 47ኛ ፣ 49ኛ፣ 50ኛ እና ከ52ኛ እስከ 56ኛ ያሉ በአጠቃላይ 54 ተከሳሾችን ፖሊስ ከመከላከያ ጋር በመተባበር እንዲያቀርባቸው በተሰጠው ተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ አለመቅረባቸውን ተከትሎ ፖሊስ ያላቀረበበትን ምክንያት እንዲያስረዳ ታዞ ነበር።
ይህን ትዕዛዝ ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተከሳሾቹ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደነበሩ በመጥቀስ÷ የትግራይ ልዩ ኃይል አባል በመሆን በጦርነቱ በመሳተፍ እና በመምራት ላይ የነበሩ መሆናቸውን ማብራራቱ ይታወሳል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ተከሳሾቹ የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ ድንጋጌ ከ12 አመት በላይ የሚያስቀጣ መሆኑን አብራርቶ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ተደርጎ የማይቀርቡ ከሆነ ያልቀረቡ ተከሳሾች ጉዳይ በሌሉበት እንዲቀጥል እንዲታዘዝ ፍርድ ቤቱን በመጠየቁ ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርአት ሕጉ መሰረት ያልተያዙ 54 ተከሳሾች በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ በመስጠቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የጋዜጣ ጥሪ ውጤት ለመጠባበቅ ለየካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል ።
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ለየካቲት 08 ቀን 2014 ዓ.ም በያዘው ቀጠሮ በቁጥጥር ስር ያልዋሉ 54 ተከሳሾች በጥር 16 ቀን 2014 ዓ.ም በታተመው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገፅ 21 ላይ የጋዜጣ ጥሪ የተደረገላቸው መሆኑን አረጋግጧል ።
በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ በቁጥጥር ስር ያልዋሉት 54ቱ ተከሳሾች በችሎት ባለመቅረባቸው መዝገቡ በሌሉበት እንዲታይ በመወሰን የዐቃቤ ሕግን ክስ ለመስማት ለየካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።
 
VIA: (ኤፍ ቢ ሲ)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman