ዶክተር አብይ አህመድ ዓሊ ማን ናቸው?

ሙሉ ስም፡ ዶ/ር አብይ አህመድ ዓሊ
ትውልድ ቦታ፡ አጋሮ ኢትዮጵያ
የትውልድ ዘመን፡ 15/08/1975 (እ.ኤ.አ)

የትምህርት ዝግጅት (እ.ኤ.አ.)
2017 በሰላምና በደህንነት ጥናት ፒ.ኤች.ዲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከሰላምና ደህንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የዶክትሬታቸው ጥናት ርዕስና ይዘት፤ የሶሻል ካፒታል ሚና በተለምዶ ግጭት አፈታት ውስጥ፣

2013
ማስትሬት ዲግሪ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ከአሽላንድ ሊድ ስታር ዩኒቨርስቲ፣
2011
ማስትሬት ዲግሪ በትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ ከግሪኒውች ዩኒቨርስቲ ሎንዶን (ተባባሪ ተቋም ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት አዲስ አበባ) የማስትሬት ጥናታቸው ርዕስና ይዘት፤ ‘Perception and Practice of Servant Leadership in the Oromiya Region of Ethiopia’ ለጥናታቸው የናሙና ጥናት አድርገው የወሰዱት የኦሮሚያ ክልል አመራሮችን ነው። የጥናታቸው ጭብጥ፤ በአመራሩ ዘንድ ያለ ሕዝቡን የማገልገል ብቃትና አረዳድ እና በሕዝቡ በበኩል አመራሩ ላይ ያለ የመምራትና የአፈጻጸም ብቃት የግንዛቤ ልዩነት ላይ የተደረገ ጥናት ነው።
2005
ፖስት ግራጁዌት አድቫንስድ ዲፕሎማ በክሪፐቶሎጂ ከፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ አግኝተዋል፡፡
2001
በኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ ዲግሪ ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ኮሌጅ የመመረቂያ ፕሮጀክት፤ “A control system based on microprocessor” ለአበባ ኢንዱስትሪ በሪሞት ሙቀቱን መቆጣጠር የሚያስችል ሲስተም ነው። በአመቱ ከተመረጡ ፕሮጀክቶች አንዱ ነበር።
የሥራ ልምድ
2017
የኦሕዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ በም/ፕሬዚደንት ማዕረግ
2016 - 2017
የክልሉ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ የቢሮ ኃላፊ በም/ፕሬዚደንት ማዕረግ
2015
የኢፌዴሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
ከ2015 እስከ አሁን
የኦሕዴድ ሥራ አስፈፃሚ አባል
08/2010
የኦሕዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ
ከ08/2013
እስከ አሁን የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ
06/2010
እስከ አሁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል (ውክልና፤ ከኦሮሚያ ክልል ከጅማ ዞን ከአጋሮ ከተማ) መልካም የሥራ አፈፃፀም የሕዝብ ውክልና ለሰጣቸው የአጋሮ ከተማ ሕዝብ ያቀረባቸውን ቁልፍ ፍላጎቶች ለመመለስ ተንቀሳቅሰዋል። ከሚጠቀሱላቸው የሥራ ውጤቶች መካከል፣ ለከተማው መሰረተ ልማት ግንባታ የሚውል ያልተቋረጠ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ ፈጥረዋል። በውጤቱም፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሁሉን አቀፍ አቅርቦት ፈጽመዋል፤ በከተማው አጠቃላይ ሆስፒታል ተገንብቷል፤ የጋዝ ማደያ ጣቢያዎች ተስፋፍተዋል፤ የወጣቶች ማዕከል ተቋቁሟል። በተለይ በጅማ ዞን ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ ግጭቶች በርካታ ናቸው። ዶክተር አብይ ከበርካታ የሃይማኖት ተቋማት እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በጥምረት በዞኑ እርቅ እንዲወርድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በተለይ በግጭት አፈታቱ ዙሪያ ሁሉንም ወገን ያቀፈ ከአድልዎ የጸዳ የአደራዳሪነት ክህሎታቸውን ከግምት በማስገባት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰላም አምባሳደርነት እውቅና ሰጥቷቸዋል።
09/2013 - እስካሁን
የብሔራዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በአስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣
06/2007 - 08/2010
የሥራ አፈፃጸም፤ የኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ሴኪሪቲ ኤጀንሲ ዳሬክተርና መስራች
05/1991 - 07/2007
ራስን የማብቃት ልምምድ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ አመራሩ ድረስ ምሳሌ በመሆን ጭምር አስተዋውቀዋል። ኤጀንሲውን በማነሳሳትና በማንቀሳቀስ ውጤታማና ሊለኩ የሚችሉ ውጤቶችን አስመዝግበዋል። ከሚጠቀስላቸው መካከል የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የላቀ የምርምር ክንውን በመፍጠር ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት አጋዥ የሚሆኑ ሥራዎችን ሰርተዋል።
1994 - 1995
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ሌ/ኮሎኔል በመሆን አገልግለዋል። በሩዋንዳ ኪጋሊ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አባል ሆነው ሰርተዋል። ተጨማሪ ኃላፊነቶች
2014 - እስካሁን
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ቦርድ ሰብሳቢ
2015 - እስካሁን
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ፣
2013 - 2016
የኦሮሚያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ቦርድ ሰብሳቢ
2008 - 2010
የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ኮርፖሬሽን አማካሪ ቦርድ አባል
2009 - 2010
የኢትዮ-ቴሌኮም አማካሪ ቦርድ አባል የብሔራዊ ኤሌክትሮኒክ አይዲ አማካሪ ቦርድ አባል
2008 - 2010
ኃላፊ በመሆን በተለያዩ ምርምርና ፕሮጀክቶች አገልግለዋል። ከሚጠቀሱት መካከል፣ በኢትዮጵያ ሚዲያ ማስፋፊያ፤ በብሔራዊ ኤሌክትሮኒክስ የመታወቂያ ሲስተም፤ ኮምፒውተር ቤዝድ ኮሚኒኬሽን ሲስተምስ በተለያዩ ድርጅቶች እና በኢትዮጵያ የኦቶሜሽን ባንኪንግ ሲስተም አገልግለዋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa