ልጥፎች

ከኦገስት, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

መንግስት የህግ የበላይነትን በማስፈን ህገወጥ ተግባራትን ሊያስቆም ይገባል

መንግስት የህግ የበላይነትን በማስፈን ህገወጥ ተግባራትን ሊያስቆም ይገባል – አስተያየት ሰጭዎች መንግስት የህግ የበላይነትን በማስፈን በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ህገወጥ ተግባራትን ሊያስቆም እንደሚገባ አስተያየት ሰጭዎች ተናገሩ። ያለፉት ሶስት እና አራት ወራት ብዙ መልካም ዜና ተሰምቶባቸዋል ኢትዮጵያውያንም ትልቅ ተስፋን ሰንቀው ቆይተዋል። ይሁን እንጅ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈፀሙ ሁከትና ግርግሮች ይህን ተስፋ ማደብዘዝ መጀመራቸውን አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ። እነዚህን ስጋቶች የፈጠሩት ሁከትና ግርግሮች የበርካቶችን ህይወት አሳጥተዋል፤ በንብረት ላይም ከባድ ውድመት አድርሰዋል። ጣቢያችን ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎችም በቅርቡ በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጸሙት ተግባራት ሰብዓዊነት የጎደላቸው አሳፋሪና ሊደገሙም የማይገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች ስርዓት አልበኝነት ነግሷል የሚሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፥ የሰው ህይዎት በአሰቃቂ ሁኔታ ማጥፋት፣ ንብረት ማውደም፣ ተሽከርካሪ አስቁሞ መፈተሽ እና ሌሎች ህገወጥ ድርጊቶች በመንጋ ይፈፀማሉ ብለዋል። ይህ ደግሞ ስርዓት አልበኝት መሆኑን ጠቅሰው፥ ድርጊቱ ለውጡን ያልደገፉ ጥቂት አካላት የሚመሩት መሆኑንም አንስተዋል። እንደ አስተያየት ሰጭዎቹ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ሀይሎች በፍጥነት አለመግባትና ከገቡ በኋላም ዝምታን መምረጥ እንዲሁም አጥፊዎችን የመቅጣቱ ነገርም ተቀዛቅዞ ታይቷል። በአጀብ የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችም አጥፊ የሚሏቸውን አካላት በህግ አግባብ እንዲቀጡ ከማድረግ ይልቅ ራሳቸው የመቅጣት ያልተገባ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባታቸውም ተገቢ አይደለም ነው የሚሉት። በመሆኑም መንግስት ይህን ፈር የለቀቀ ድርጊት

በስሜታዊነት የሚለወጥ ነገር የለም

ኢሕአዴግ ለሶስት አስርት አመታት ለሚጠጋ ጊዜ ሀገርን የመምራት ሃላፊነት ተረክቦ በሁሉም መስክ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት ሲሰራ መቆየቱና በዚህም ሀገራችን ለዘመናት ስትታወቅበት የነበረውን ረሃብ፣ ጦርነትና ኋላ ቀርነት ከመሰረቱ ለመለወጥ የሚያስችሉ ስኬቶችን አስመዝግቧል፡፡ ይሁንና የመጡ ለውጦች ሁሉን አቀፍ አለመሆናቸውና የህዝቡን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ፍላጎት ማርካት ያለመቻላቸው፤ ብሎም ከራሱ ከድርጅቱ ውስጥ በመነጩ ፀረ ዴሞክራሲያዊ ባህሪዎች የተነሳ ካለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ወዲህ በሀገራችን ከፍተኛ አለመረጋጋቶች ሲከሰቱና ያልተገባ ዋጋ ሲያስከፍሉን ቆይተዋል፡፡ኢህአዴግ የመሪነት ሚናው በከፍተኛ ሁኔታ እየተጓደለና መርህ ወደ መልቀቅ እየተጓዘ መሆኑን በጥልቅ ተሃድሶ በሚገባ ገምግሜያለሁ ብሎ በአዲስ የመደመር አስተሳሰብ መመራት ከጀመረ ደግሞ ግና መንፈቅ እንኳን ያልሞላው መሆኑም ይታወቃል፡፡ በግምገማው የተለዩ ችግሮችን ግዝፈትና አስከፊነት በመረዳትም ሰፊ የማስተካካያ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ በሀገራችን የተጀመረውን ልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማሳለጥ ብሎም ረጅሙን የህዳሴ ጉዞ ለማሳካት የአመራር ለውጥ በማድረግ ወደ ተጨባጭ ስራ ገብቷል፡፡ አዲሱ አመራር የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚና የኢሕአዴግ ምክር ቤት ባስቀመጡት አቅጣጫ ብሎም ባደገና በጎለበተ አስተሳሰብ በመመራት ተፈጥሮ የነበረውን የሰላም እጦትና ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በጥቂት ጊዜያት በመቅረፍ በአንድነት፣ በፍቅርና በመደመር እሳቤ