መንግስት የህግ የበላይነትን በማስፈን ህገወጥ ተግባራትን ሊያስቆም ይገባል

መንግስት የህግ የበላይነትን በማስፈን ህገወጥ ተግባራትን ሊያስቆም ይገባል – አስተያየት ሰጭዎች
መንግስት የህግ የበላይነትን በማስፈን በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ህገወጥ ተግባራትን ሊያስቆም እንደሚገባ አስተያየት ሰጭዎች ተናገሩ።
ያለፉት ሶስት እና አራት ወራት ብዙ መልካም ዜና ተሰምቶባቸዋል ኢትዮጵያውያንም ትልቅ ተስፋን ሰንቀው ቆይተዋል።
ይሁን እንጅ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈፀሙ ሁከትና ግርግሮች ይህን ተስፋ ማደብዘዝ መጀመራቸውን አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ።
እነዚህን ስጋቶች የፈጠሩት ሁከትና ግርግሮች የበርካቶችን ህይወት አሳጥተዋል፤ በንብረት ላይም ከባድ ውድመት አድርሰዋል።
ጣቢያችን ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎችም በቅርቡ በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጸሙት ተግባራት ሰብዓዊነት የጎደላቸው አሳፋሪና ሊደገሙም የማይገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች ስርዓት አልበኝነት ነግሷል የሚሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፥ የሰው ህይዎት በአሰቃቂ ሁኔታ ማጥፋት፣ ንብረት ማውደም፣ ተሽከርካሪ አስቁሞ መፈተሽ እና ሌሎች ህገወጥ ድርጊቶች በመንጋ ይፈፀማሉ ብለዋል።
ይህ ደግሞ ስርዓት አልበኝት መሆኑን ጠቅሰው፥ ድርጊቱ ለውጡን ያልደገፉ ጥቂት አካላት የሚመሩት መሆኑንም አንስተዋል።
እንደ አስተያየት ሰጭዎቹ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ሀይሎች በፍጥነት አለመግባትና ከገቡ በኋላም ዝምታን መምረጥ እንዲሁም አጥፊዎችን የመቅጣቱ ነገርም ተቀዛቅዞ ታይቷል።
በአጀብ የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችም አጥፊ የሚሏቸውን አካላት በህግ አግባብ እንዲቀጡ ከማድረግ ይልቅ ራሳቸው የመቅጣት ያልተገባ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባታቸውም ተገቢ አይደለም ነው የሚሉት።
በመሆኑም መንግስት ይህን ፈር የለቀቀ ድርጊት በማጤን የህግ የበላይነትን ሊያሰፍን እንደሚገባው ጠቅሰው፥ አጥፊዎቹን ወደ መቅጣት ሊሸጋገር እንደሚገባውም አስረድተዋል።
ህብረተሰቡም አጥፊዎቹን በማጋለጥ አሁን የተገኘውን ለውጥ ለማጣጣም ነገሮችን በሰከነ መንገድ ማየት እንደሚገባውም ጠቁመዋል።
የፀጥታ አካላት ሚናቸውን በአግባቡ እና በፍጥነት አለመወጣትም ወጣቶች በሀሰተኛ መረጃ ተነሳስተው ያልተገባ ተግባር እንዲፈጽሙ እና ፍትህ የመስጠት ስራ ላይ እንዲሰማሩ ማድረጉን ገልፀዋል።
በመሆኑም የፀጥታ እና የፍትህ አካላት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተስፋፉ የመጡ ህገወጥ ድርጊቶችን የህግ የበላይነትን በማስፈን ስርአት እንዲይዙ ማድረግ አለባቸው ነው ያሉት።
ምንጭ:FBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa