የሕግ የበላይነት ይጠበቃል፤ይከበራል


ብዙዎች በከፈሉት መስዋዕትነት ለሁላችንም የሚበጅ ለውጥ ታየቷል ለውጡን አስተማማኝ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው ጥቂት አመራሮች የሚያሳዩት ቁርጠኝነት ብቻ ለውጡን ማስቀጠልና አስተማማኝ ማድረግ አይችልም
ስለዚህ ሁሉም በእኔነት ስሜት መስራት ይጠበቅበታል ሁሉም ተባብሮ ሲንቀሳቀስ የህግ የበላይነት ይጠበቃል ይከበራልም
ሁላችንም ኃላፊነታችንን በአግባቡ ከተወጣን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየው አግባብ ያልሆነ አካሄድ ይስተካከላል
የመንግስት የመጀመሪያ ስራ ሕግን ማስከበር ስለሆነ መንግስት ወዶ ሳይሆን በግዴታ የህግ የበላይነትን ያስከብራል ሁሉም ዜጋ ግን ለህግ ማስከበር ስራ መተባበርና ግዴታውን መወጣት ይጠበቅበታል
መንግስት ህግ ማስከበር አልቻለም ብሎ ማሰብ ስህተት ነው አንዳንድ የአገራችን ሚዲያዎች በዚህ አይነት መልኩ ሲሰሩ ይሰማል በተለይም አንዳንድ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎችና የቴሊቪዥን ጣቢያዎች ኃላፊነት የጎደለው ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ የብሮድካስት ባለስልጣን የሚባለው ተቋምማ አንቀላፍቷል ባለስልጣኑ ንቁ ሆኖ ቢከታተል ኖሮማ ማንም አንደፈለገ አይዘባርቅም ነበር
ሁሉም ሚዲያዎች ከመዘባረቅ ወጥተው ለህዝብና አገራችን ተስፋ ሰጪ የሆኑ ስራዎችን ጠንክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa