ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ከተነሡ፤ ካሰቡት ሳይደርሱ አይመለሱ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ፡- • ስለማይበገረው ጽናታችሁ እና ሁሉን ማድረግ ስለሚችለው አስደናቂ አቅማችን በተለየ አክብሮት እና ፍቅር እጅ እነሳለሁ፡ ፡ • በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነን እንኳን ሀገራችንን የሚመለከቱ አበይት ጉዳዮች ሲገጥሙን ከመቅጽበተ አይን ለሚያጋምደን- ያለምንም ልዩነት እንደ አንድ እናትና ልጅ ለሚያዛምደን እና ያለመለያየት ለሚያዋህደን ዘመን አይሽሬ ኢትዮጵያዊ መንፈሳችን ያለኝን የማይናወጥ ፍቅር በክብራችሁ ጥላ ስር ሆኜ በክብር እገልጻለሁ፡፡ • መቼም- ማንም የትኛውንም የክፋት ሴራ የሚሰራ የጥፋት አበጋዝ አብሮነታችንን ሊያጠለሽ ቢጥር እንኳን አብሮነታችን ከነፍሳችን ውስጥ የተሸመነ እንጂ ከስጋችን ላይ የተጎነጎነ አይደለምና አብሮነታችንን ላጸደለው የአረንጓዴ አሻራ ድላችሁ የተለየ ምስጋናዬን በፍቅሬ ሙዳይ ሞሽሬ እነሆ ልኬያለሁ፡፡ ሀገር ታመሰግናለች- እኔም አመሰግናለሁ፡፡! የኢትዮጵያን አረንጓዴ ጸጋ በመመለስ አረንጓዴ አሻራ እንድናሳርፍ ያቀረብኩትን ጥሪ በመቀበል ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በነቂስ ለችግኝ ተከላ ወጥቷል፡፡ ከጨቅላ ሕጻናት እስከ ዘጠና ዓመት አዛውንት፣ ከጎዳና ተዳዳሪዎች እስከ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ፣ ከታክሲ ተራ አስከባሪዎች እስከ ጸጥታ አስከባሪዎች፣ ከገበሬዎች እስከ ግብርና ባለሞያዎች፣ ከልማት ጣቢያ ሠራተኞች እስከ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች፣ ከተማሪዎች እስከ መንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከሀገር ቤት እስከ ዳያስፖራ፣ ከድምጻውያን አስከ ተዋንያን፣ ከአትሌቶች እስከ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች፣ ከጋዜጠኞች እስከ ፊልም ባለሞያዎች፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ - ያልተሳተፈ የኅብረተሰብ ክፍል አልነበረም፡፡ ይህ የተሳትፎ ማእበል እና የእ