ልጥፎች

የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ጃፓንና ሜክሲኮ አምባሳደሮች የሕዳሴውን ግድብ ጎበኙ

ምስል
ጥቅምት 21  2010 ዓ.ም(ቶለዋቅ ዋሪ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ጃፓንና ሜክሲኮ አምበሳደሮች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጎበኙ። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሀገሪቱ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትስስር የሚያሳድግ መሆኑን፥ አምባሳደሮቹ ገልፀዋል። የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ እንዲሁም የተፋሰሱ ሀገራትን ምክንያታዊና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከግምት ያስገባ መሆኑን አምባሳደሮቹ ከጉብኝቱ በኋላ ተናግረዋል። የአራቱም የበለፀጉ ሀገራት አምባሳደሮች በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ቁርጠኝነት ሀገሪቱን በቀጠናው የኤሌትሪክ ኃይል ማዕከል ወደ መሆን እያሸጋገራት ነው በማለት አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ለህብረተሰቡ ኑሮ መለወጥ ኤሌክትሪክ ኃይል ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የገለጹት አምበሳደሮቹ፥ የህዳሴው ግድብ በዚሁ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ፊሊፕ ቤከር ላለፉት ዓመታት በሀገሪቱ ህዝብ ተሳትፎ እየተገነባ ያለውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለመጎብኘት ሲመኙ መቆየታቸውንና በጉብኝቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደነቅ የምህንድና ጥበብ እና ሀገራዊ ስሜት የሚታይበት መሆኑን የተናገሩት ደግም፥ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምበሳደር ሚካኤል ራይኖር ናቸው። የኃይል ዕጥረት መሰረታዊ የልማት ፈተና መሆኑን የተናገሩት አምባሳደሩ "ግድቡ ሀገሪቷን ከጎረቤት አገሮች ጋር የሚያስተሳር ነው" ሲሉም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር ቪክቶር ትሬቪኖ፥ የህዳሴ ግድቡ ኃይል ከማመንጨት ባሻገር በአካባቢው ትልቅ የቱሪዝም ማዕከል እንደሚሆን ጠቁመው፥ በቱሪዝም ዘርፍ ሀገራቸው ልምድ ለማካፈልና ለመተባበር...

በነቀምቴ ከተማ ተቀስቅሶ ስለነበረው ግጭት የሚወጡት ዘገባዎች እውነታውን የሚያሳዩ አይደሉም- የከተማዋ ፖሊስ

ምስል
ሰሞኑን በነቀምቴ ከተማ ተቀስቅሶ የነበረውን ግጭት በተመለከተ በተለያዩ የማህብራዊ ሚዲያዎች ላይ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እውነታውን የሚያሳዩ አይደሉም አለ የከተማዋ ፖሊስ። በከተማዋ የሚስተዋለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተለቀቁ የሚገኙ መረጃዎች ከእውነታው የራቁ እና ሆነ ተብሎ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማስመሰል የሚያቀርቡ መሆናቸውን ነው ፖሊስ የገለፀው። የከተማዋ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ይታና በተለይ ለነቀምቴ ፋና ኤፍ ኤፍ ኤም 96 ነጥብ 1 በሰጡት መግለጫ፥ ለግጭቱ መንስኤ ነው የተባለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በግለሰቦች ቤት ተከማችቶ ተገኘ የሚለው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል። እስካሁን ድረስ ከአንደ ፈቃድ ያለው ሽጉጥ ውጭ ተከማችቶ የተገኘ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ የለም ነው ያሉት። ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በተከሰተው ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉንም ኮማንደር ጌታቸው አረጋግጠዋል። በግጭቱ 10 ሰዎች ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው፥ በከተማዋ በሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል። አንዳንድ ግለሰቦች ግጭቱን መነሻ በማድረግ የግለሰቦችን ሱቅ እና መጋዘኖች መዝረፋቸውንም ነው የጠቆሙት። ድብቅ አላማቸውን ሊያሳኩ መሰረተ ቢስ በሆነ ወሬ የከተማዋን ህዝብን ሲያሸብሩ እና ሰላም ሲነሱ የተገኙ 16 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርምር እየተደረገባቸው እንደሚገኙ ኮማንደሩ ገልፀዋል። ኮማንደር ጌታቸው እንደተናገሩት በግጭት ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ አምስቱ የኦሮሞ፣ ሶስት ጉራጌዎች እና ሁለት የትግራይ ብሄሮች ተወላጆች ናቸው። ትናንት እና ከትናንተ በፊት የሞቱት ደግሞ አንድ የኦሮሞ እና ሁለት የአማራ ብሄር ተወላጆች...

ከአምባሳደር ትአትር ህንፃ ላይ ለሚንደቀደቁ ድምፆች!

አሁን በጣም መረን የለቀቃችሁ መሆናችሁን ኣሳይታችኋል ለከትም እንደሌላችሁ ታውቋል፤ሴትዮዋ ስቱዲዮ የምትገባው ከቃመች በኋላ ይመስላል እርስዋ ቀድማ በምታነሳቸው ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያወሩ ብሎገር ተብዬዎችም ለበሉበት የሚጮሁ መሆናቸውን እያሳዩ ነው እውነት ነውር ነው! ድፍረት ነው! ባለፈው ሳምንት በተካሄደ ዘለፋዊ ውይይት ላይ ባልና ሚስት በአልጋቸው ላይ ተወያይተው ያፀደቁትን የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ ይዘው ስቱዲዮ ገቡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አመራሮችንም ጥበት ውስጥ የተሸሸጉ ሲሉ ወነጀሉ ሰዎቹ በሚጠብቁት ልክ የማስታወቂያ ገቢ ባይኖራቸውም የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል በጩኸት ላንቃው የሚሰነጠቅበት ድምፅ ገቢ ምንጭ ኪራይ ሰብሳቢዎች እንደሆኑ ግልጽ ነው እነዚህ ሰዎች የሚደመጡበት አካባቢ ውስን በመሆኑ ነው እንጂ እንደፍላጎታቸውማ ቢሆንነ ኖሮ አገር ተቃጥላ ብን ብላለች እግዚአብሔር “እባብን የልቡን አውቆ እግር ነሳው” አለ ያገሬ ሰው

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያካሄደውን ስብሰባ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀቀ

ምስል
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያካሄደውን ስብሰባ የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀቀ። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከጥቅምት 18 እስከ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ የደረሰበት ደረጃ እና ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን በዝርዝር የገመገመበትን ስብሰባ አካሂዷል። በአሁኑ ወቅት በተወሰኑ የአገሪቱ አካባቢ የተከሰቱ ችግሮችና ግጭቶች ባህሪያቸውና ምክንያታቸው ምን እንደሆነም በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ በመስከረም ወር መጀመሪያ በምስራቁ የሀገሪቱ አካባቢ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱት ግጭቶች በዜጎች ህይወት እና በንብረት ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ከማስከተላቸውም አልፎ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸውና ከኑሮአቸው ተፈናቅለው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ነው የገመገመው። ይህ ድርጊት በምንም መልኩ መከሰት ያልነበረበት እንደሆነ በማንሳት የኪራይ ሰብሳቢነትን ችግሮች መድፈቅ ባለመቻሉ የተፈጠረ እንደሆነ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ለግጭቶቹ መፈጠር ምክንያት የሆኑ የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የሙስናና የብልሹ አሰራሮች ከዚህ ጋር ተያይዞ ህገ ወጥነት እንዲስፋፋ እያደረጉ ያሉ የኮንትሮባንድ ትስስሮች በዝርዝር ተፈትሸው በአፋጣኝ እንዲቀረፉ የኢህአዴግ ምክር ቤት በወሰነው መሰረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል። ከእነዚህ ችግሮች ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ህገ ወጥነቶች በምንም መልኩ እንዲቀጥሉ እንደማይፈቅድላቸው እና የህግ የበላይነት መረጋገጥ እንደሚገባ በአፅንኦት አስምሮበታል። ለሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ለመምህራን፣ ለሴቶችና ወጣቶች እንዲሁም ችግሩ በተከሰተባቸው...

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ወጣቶች የክልሉን ሰላም እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ

ምስል
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ወጣቶች ከሁከት እና ብጥብጥ አካላት ቅስቀሳ በመራቅ የክልሉን ሰላም እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ። የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በአምቦ ከተማ የተከሰተው ግጭት ክልሉን የሁከት አውድማ ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ባሰራጩት የሀሰት መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት በአምቦ ከተማ በተፈጠረ ግጭት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ከአምቦ ከተማ አስተዳደር ባገኘነው መረጃ መሰረትበግጭቱ ምክንያት የስምንት ሰዎች ህይወት አልፏል። ሶስት ተሽከርካሪዎችም ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ነው የተገለፀው። የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፥ የክልሉ መንግስት በግጭቱ ምክንያት በደረሰው ሰብኣዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገልፅዋል። ግጭቱ "ከፊንጫ ወደ አዲስ አበባ ህገ ወጥ ስኳር እየተጓጓዘ ነው” በሚል የሀሰት መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል። የክልሉ መንግስት ግጭቱን ከመጠንሰስ እስከ መተግበር ድረስ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ እንድሚያቀርብም አረጋግጠዋል። አቶ አዲሱ ባለፈው ሳምንት በቡኖ በደሌ ዞን የተፈጠረውን ጨምሮ ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በአምቦ ከተማ የታየው ክስተት የኦሮሚያ ክልልን የሁከት እና ነውጥ ማእከል ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ያቀነባበሩት ሴራ ውጤት ነው ብለዋል። አዲሱ የክልሉ መንግስት አመራር ከክልሉ ህዝብ ጋር ካደረጋቸው ምክክሮች በመነሳት የኪራይ ሰብሳቢነት መገለጫ በሆነ ሙስና፣ ምዝበራ፣ ህገ ወጥ ንግድ (ኮንትሮባንድ) እና በህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ላይ ጠንካራ እርምጃ መወስድ መጀመሩን ሃላፊው ገልፀዋ...

የብሮድካስት ባለሥልጣን ሚዲያው አደገኛ አዝማሚያዎች ይታዩበታል አለ

ምስል
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም በብሮድካስት ሚዲያው የሚታይ አሳሳቢ ሁኔታ አለ አሉ፡፡  ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ያሉት በአገሪቱ እየታየ ያሉ ግጭቶችን ሚዲያው የሚዘግብብትን መንገድ በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡ ሚዲያዎች ጠንካራ ባለመሆናቸው ለማኅበራዊ ሚዲ ያው የተጋለጡ ናቸው ብለው፣ ከግሉም ሆነ ከሕዝብ ሚዲያው የሚታዩ አደገኛ የሆኑ አዝማሚያዎች እየተስተዋሉ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ ሰሞኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ የተሳሳተ ዘገባ ያቀረቡ የሚዲያ ተቋማትን በሕግ ለመጠየቅ እንቅስቃሴ ይጀመራል ያሉት የግል አስተያየታቸው ነው ያሉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር፣ አንድ ሚዲያ እንዲህ አይነት ጥፋት ከተገኘበት እንዴት፣ በማንና ምን ይቀጣል የሚለው የሚወሰነው በፍርድ ቤት እንጂ በሌላ የመንግሥት ተቋም አይደለም ብለዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ኢኤንኤን የቴሌቪዥን ጣቢያንና ዛሚ ሬድዮ ጣቢያን የተሳሳተ ዘገባ በማስተላለፍ እንደወቀሷቸው ይታወሳል፡፡

Manni marichaa yaada mooshinii boru dhaggeeffata

ምስል
Onkololeessa 15,2010(Tolawaaq Waarii) Muummichi ministiraa Ob.Hayilamaariyaam Dassaalany kamisa boru mana maree bakka bu'oota ummataatti argamuudhaan mooshinii haasawaa pireezidaant Dr.Mulaatuu Tashooma irratti ejjennoo mootummaa ibsu. Pireezidaantiin Itiyoophiyaa Dr.Mulaatuu Tashooma haasawa miseensoota mana maree bakka bu'oota ummataafi mana maree federeeshiniitiif dhageessisaniin hojiiwwan siyaasaafi hawaas-diinagdee biyya keenyatti bara bajataa haarawaatti hojjetaman irratti akka xiyyeef fatan ni beekama. Dhimma qabiyyee haasawa pireezidaantichaa irratti hooggantoonni paartilee mormitootaa adda addaa yaada sab-quunnamtiilee adda addaa irratti kennaniin haasaan pireezidaantichaa haala qabatamaa biyyattiin irratti argamtu jiddu galeessa kan taasifate miti jechuudhaan qeeqaa akka turan ni beekama Turtiin muummichi ministiraa mana mareetti taasisan sab-quunnamtiileedhaan kallattiidhaan tamsa'a jedhamee eegama.hordofaa.