በነቀምቴ ከተማ ተቀስቅሶ ስለነበረው ግጭት የሚወጡት ዘገባዎች እውነታውን የሚያሳዩ አይደሉም- የከተማዋ ፖሊስ

ሰሞኑን በነቀምቴ ከተማ ተቀስቅሶ የነበረውን ግጭት በተመለከተ በተለያዩ የማህብራዊ ሚዲያዎች ላይ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እውነታውን የሚያሳዩ አይደሉም አለ የከተማዋ ፖሊስ።
በከተማዋ የሚስተዋለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተለቀቁ የሚገኙ መረጃዎች ከእውነታው የራቁ እና ሆነ ተብሎ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማስመሰል የሚያቀርቡ መሆናቸውን ነው ፖሊስ የገለፀው።
የከተማዋ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ይታና በተለይ ለነቀምቴ ፋና ኤፍ ኤፍ ኤም 96 ነጥብ 1 በሰጡት መግለጫ፥ ለግጭቱ መንስኤ ነው የተባለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በግለሰቦች ቤት ተከማችቶ ተገኘ የሚለው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል።
እስካሁን ድረስ ከአንደ ፈቃድ ያለው ሽጉጥ ውጭ ተከማችቶ የተገኘ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ የለም ነው ያሉት።
ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በተከሰተው ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉንም ኮማንደር ጌታቸው አረጋግጠዋል።
በግጭቱ 10 ሰዎች ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው፥ በከተማዋ በሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
አንዳንድ ግለሰቦች ግጭቱን መነሻ በማድረግ የግለሰቦችን ሱቅ እና መጋዘኖች መዝረፋቸውንም ነው የጠቆሙት።
ድብቅ አላማቸውን ሊያሳኩ መሰረተ ቢስ በሆነ ወሬ የከተማዋን ህዝብን ሲያሸብሩ እና ሰላም ሲነሱ የተገኙ 16 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርምር እየተደረገባቸው እንደሚገኙ ኮማንደሩ ገልፀዋል።
ኮማንደር ጌታቸው እንደተናገሩት በግጭት ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ አምስቱ የኦሮሞ፣ ሶስት ጉራጌዎች እና ሁለት የትግራይ ብሄሮች ተወላጆች ናቸው።
ትናንት እና ከትናንተ በፊት የሞቱት ደግሞ አንድ የኦሮሞ እና ሁለት የአማራ ብሄር ተወላጆች መሆናቸውን ተናግረዋል።

አሁን ላይ የፀጥታ አካሉ ከህብርተሰቡ ጋር ተባብሮ በወሰደው እርምጃ ከተዋማ የተረገጋች እና ወደ ሰላማዊ እንቅሰቃሰዋ መመለሷ ተገልጿል። 

Maddi:Faanaa Biroodkaastiing Korporeet(FBC)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman