በአዳማ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ከ11 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ተያዘ

በአዳማ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ እጅ ሲዘዋወር የነበረ ከ11 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ ዋና ሳጅን ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት፥ ገንዘቡ ዛሬ ጧት የተያዘው በአንድ ገልሰብ እጅ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ነው።

ግለሰቡ ማለዳ 2 ሰዓት ከ30 ላይ በአዳማ ከተማ ወረዳ አንድ ቀበሌ 09 ልዩ ስሙ አዳማ ራስ ሆቴል አካባቢ፥ 11 ሺህ 500 የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ ሕብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆነው እና ገብረመድህን ይርጋው ገብረጊዮርጊስ የተባለው ይኸው ግለሰብ፥ እጅ ከፍንጅ የተያዘው ገንዘቡን ወደ ቶጎ-ውጫሌ ከተማ ለመጓጓዝ ሲዘጋጅ በነበረበት ወቅት ነው።
በአሁኑ ወቅት ግለሰቡን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማካሄድ መጀመሩንም፥ ዋና ሳጅን ወርቅነሽ ገልሜቻ ገልፀዋል።
መንግስት ህገወጦችን ለማጥራት የጀመረው ዘመቻ ከዳር እንዲደርስ ሕብረተሰቡ እያሳየ ያለውን ትብብርና ርብርብ አጠናክሮ እንዲቀጥል፥ ዋና ሳጅን መጠየቃቸውን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman