ጠ/ሚ ኃይለማርያም ለቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ዢንፒንግ የደስታ መግለጫ ላኩ

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ሆነው በድጋሚ በመመረጣቸው የደስታ መግለጫ ደብዳቤ ላኩ።
ከሰሞኑ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ 19ኛውን ድርጅታዊ ጉባኤ በማካሄድ ሺ ዢንፒንግን የፓርቲው ዋና ፀሀፊ አድርጎ ዳግም መርጧል።

የፕሬዚዳንት ሺ ድጋሚ መመረጥን እና የ19ኛው የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ መካሄድን አስመልክቶ የደስታ መግለጫ የላኩት አቶ ኃይለማርያም፥ በኢትዮጵያ መንግስትና በድርጅታቸው እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ለቻይና ህዝብ ሰላምና ብልፅግናን ለተመራጩ የፓርቲው ዋና ፀሃፊ ደግሞ ጤናና መልካም የስራ ዘመንን ተመኝተዋል።
በፕሬዝዳንት ሺ ዢንፒንግ አመራር ቻይና ዘርፈ ብዙ አስደናቂ እድገት ማስመዝገቧን ጠቅሰው፥ ሀገሪቱ ለዓለም ብልፅግና እና ሰላም ሚናዋን እየተወጣች መሆኗን በደብዳቤያቸው ገልፀዋል።
ቻይና በዓለም አቀፍ መድረኮች የምታቀርባቸውን ዘመናዊ አስተሳሰቦች ኢትዮጵያ ስትደግፍ መቆየቷን የገለፁት የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም፥ የ19ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ውሳኔዎችም በዓለም ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ የሚያግዙ እንደሚሆኑ እምነታቸውን ተናግረዋል።
አቶ ኃይለማርያም እንዳሉት የሁለቱ መሪ ድርጅቶች እና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መልካም ፍሬዎችን ሲያፈራ ቆይቶ አሁን ላይ ወደ ስትራቴጂያዊ የትብብር አጋርነት አድጓል።
ይህ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች የበለጠ እንዲጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ለሺ በላኩት ደብዳቤ አረጋግጠዋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman