ሙያ በልብ ነው ይሏል እንዲህ ነው
አበው
ቀድሞውኑም እንዲህ ጨርሰውታል ሙያ በልብ ነው በማለት፤ከሰሞኑ የሰማነው አዳስ ነገር አሁንም እያነጋገረ መሆኑ ይታወቃል።ሰውዬው
ሞላ አስገዶም እነ ሻቢያን ጉድ ሰራቸው።እነርሱ አሁን ለፕሮፓጋንዳቸው
ማሳመሪያ ወታደሮቹን ሸውዶ ነው፤አመት በኣል እናከብራለን ብሎ በማታለል ወደ አገር ቤት ወሰዳቸው፤ስልጣን ስለ አጣ ነው ምናምን
በማለት ቢወሸክቱም ጉድ ተሰርተዋል።እውነት ነው ቅስማቸው እንክትክት ብሎ ተሰባብሯል።
በሞላ
ቁርጠኛ አቋም እነ ግንቦት ሰባት ወገባቸው ጉምድ ብሎ ተቆርጧል።እንዲህ ነው እንጂ ሙያ በልብ ነው።
የትግራይ
ሕዝብ ዴሚክራሲያዊ ንቅናቄ(ትሕዴን) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስገዶም በእውነት ለአገራቸው የቆሙ እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጅ መሆናቸውን
በተግባር አሳይተዋል።
ሰውዬው
ለሆዳቸው ያላደሩ ከአስመሳይነት የራቁ፤አድርባይነትን አሽቀንጥረው የጣሉ መሆናቸውን በሰሩት የጀግና ስራ አስመስክረዋል።የሞላ አስገዶም
ታሪካዊ እርምጃና የመንግስታችን ጥበባዊ አካሄድ በእውነት ወደር አይገኝለትም።
ሻዕቢያና
ተላላኪዎቹ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሸረቡት ሴራ ከንቱ ሆኖ ቀርቷል።በታሪካዊው የሞላ አስገዶም ቆራጥ እርምጃ የግንቦት ሰባት፤የአብነግና
ኦነግ ሰዎች ወሽመጥ ቍርጥ ብሏል።
ለኢትዮጵያችን
የተደገሰው የእልቂት ድግስ ውሃ ሲበላው እጅግ በጣም ደስ ይላል።ለአገሩ ሰላምና ልማት እንዲሁም ብልፅግናን የሚመኝ ዜጋ ከዚህ በላይ
የሚያስደስተው ነገር ይኖር ይሆን?
አዎ
በስም ዜጋ፤ነገር ግን ተስፈኛና ምንም ነገር የማይሰማው ብዙ ደነዝ እንዳለ ይታወቃል።በአገር ውስጥም ሆነ ውጭ ሆኖ በዚህ ታሪካዊ
እርምጃ እርር ድብን ያለ ኢትዮጵያ ዜጋ የለም ማለትም አይቻልም።ዋናው ነገር ግን እነርሱ የሚፈልጉቱ ነገር መሆን አለመቻሉ
ነው ለእኛ ትልቁ ድል።ወደፊትም እናቸንፋለን፤ለማንም አንበገርም!
አቶ ሞላ መስከረም 05 2008 ዓም በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በአዳማ ከተማ አቀባበል የተደረገላቸው ከምንም በመነሳት ሳይሆን ጀግንነታቸውን በማድነቅ ነው።
የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ አብረሃም አዱላ በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉን መንግስት ወክለው ባሰሙት ንግግር አቶ ሞላ ለኢትዮጵያ በመቆርቆር ለፈፀሙት ታላቅ ተግባር እናመሰግናለን ብለዋል
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የአዳማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።ሌሎች የኢትዮጵያ ክልልሎችም ተመሳሳይ አቀባበል ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ