ስኬታማው የኦሮሚያ ክልል ጥልቅ የተሃድሶ ንቅናቄ

ስድስት ወራትን አስቆጥሯል፤ከላይ እስከ ታች ሁሉም ተፈትሽዋል በአመለካከትም ሆነ በድርጊት ችግሮች የት እንዳሉ ለማየት ተሞክሯል ሁሉም ነገር ምልዑ ነው ባይባልም ጥፋተኞች ጥጋቸውን እንዲይዙ፤በትክክለኛ አካሄድ የክልሉን ሕዝብ መምራት ይችላሉ ተብለው የታመነባቸው አመራሮችም ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ ኃላፊነት እንዲሰጣቸው ተደርጓል።
ለኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ይህ እጅግ በጣም ትልቅ ስኬት ነው፤ሰላም ደፍርሶ፤ወጥቶ መግባት አሳሳቢ ከሆነበት ሁኔታ በመውጣት ለዚህ ድል መብቃት መቻል ሊደነቅ ይገባል
ይህ ስኬት በአስተማማኝ ሁኔታ ሊመዘገብ የቻለው በሰላም ፈላጊው ታላቁና ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ሙሉ ተሳትፎና ቁርጠኛ በሆኑ ልጆቹ አመራር ነው።ይህን ሃቅ የሚክድና ለማጣጣል የሚሞክር ማንኛውም ኃይል በአጠቃላይ የአገራችን ኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላትና የሰፊው ኦሮሞ ሕዝብ ደመኛ ብቻ ነው፤አሁን በጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ በኦሮሚያ ክልል የተመዘገበውን ተጨባጭ ውጤት ማንቆለጳጰስና ማድነቅ የማይችል አዕምሮም በሽተኛ ነው!
ዛሬ በ38 የህዝባዊ ወይይት ማዕከሎች በአሮሚያ ክልል 20 ዞኖችና በ10 ዋና ዋና ከተሞች የህዝብ ተወካዮችን ያሳተፈ ኮንፍረንስ ተካሂዶ በሰላም ተጠናቅቋል፣የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ይህንኑ አረጋግጠዋል።
ዛሬ በተካሄደው ሕዝባዊ ኮንፍራንስ መፍትሄ ባላገኙ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፤በተጓተቱ የልማት ፕሮጀክቶችና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎች ቀርበው ከፌዴራልና ከክልሉ መንግስት ከተውጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ምላሽ ተሰጥቷል፤በየመድረኮቹ በባለስልጣናቱ የተሰጠው ምላሽ የመጨረሻ መፍትሄ ነው ማለት አይቻልም ገና በተግባር የሚፈተሹ ነገሮች ብዙ አሉ፤ሁሉም ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ መላው ህዝብና በየደረጃው የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው።


በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም በኦሮሚያ ክልልም ሆነ በመላ አገራችን የተመዘገበውን የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ ስኬት ዘላቂ ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል።በተለይም የአገራችን መገኛና ብዙሃን የተሃድሶውን ንቅናቄ ውጤትና ቀጣይነት በንቃት ተከታትለው መላው ሕዝብ የተሟላ ግንዛቤ መያዝ እንዲችል ሌት ተቀን መስራት ይጠበቅባቸዋል።የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን መንግስትን ብቻ ማንቆጳጰስና ከባለስልጣናት ጋር መሞዳሞድ የትም ማድረስ እንደማይችል በተግባር ታይቷል የግል መገኛኛ ብዙሃንም ከወዲያኛው ፅንፍ መቆማቸው እንደማይጠቅማቸው ሊገነዘቡት ይገባል፤የተቋማቱ ባላቤቶችም በሚዲያ ስራ ተሳክቶላቸው ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት የኢትዮጵያ ሰላም ልማትና ዴሞክራሲ ቀጣይ መሆን ሲችል ብቻ እንደሆነ በቅጡ ሊገነዘቡ ይገባል!ሁሉም ለሰላም ልማትና ዴሞክራሲ ቀጣይነት ይትጋ የበኩሉን የማይተካ ሚና ይወጣ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa