መንግስት በደምቢ ዶሎ በታገቱ ተማሪዎች ዙሪያ የደረሰበትን መረጃ በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገለጸ
Finfinnee Caamsaa 18/2012(TW) ታግተው የነበሩ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ መረጃ በቅረቡ ለህዝቡ ይፋ እንደሚደረግ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ የነበሩ ተማሪዎች መታገታቸው ይታወሳል። እነዚህን ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ የሚገመግም በፌዴራል ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየሰራ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከአሃዱ ቲቬ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልነው ነው ያሉት ሃላፊው፤ ጉዳዩን አስመልክቶ ለህብረተሰቡ መረጃውን ደረጃ በደረጃ መስጠት በሚገባ መልኩ ለመስጠት ቃል ብንገባም ሁኔታው ውስብስብ በመሆኑ ጊዜ ሊወስድ ችሏል ብለዋል። ጉዳዩ ውስብስብ ከመሆኑም በላይ በጉዳዩ ዘንድ ቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በርካታ ሰዎች የተሳተፉበት በመሆኑ ጊዜ ሊወስድ ችሏል ብለዋል አቶ ንግሱ። ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው 28 ሰዎች መያዛቸውንም በመግለጽ። ለዚህም በማህበራዊ ድረ ገጽ የተሳሳተና ያልሆነ መረጃ ለህብረተሰቡ እየደረሰው ነው ያሉት አቶ ንጉሱ፤ “ታግቼ ነበር ተማሪ ነበርኩ ”ብለው በተለያየ መልኩ የቀረቡ ወደ 4 ያህል ተማሪዎች እንደተያዙ ጠቁመዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጉዳዩን ለማድበስበስ የሞከሩም ተይዘዋል ብለዋል። በፌዴራል ደረጃ እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተቋቋመው ግብረ ሃይል ስራውን ሌት ተቀን እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ዝርዝርና የተሟላ መረጃውን በቅርቡ ለህዝቡ ይፋ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ንጉሱ በማከልም “እገታው እንዲከሰት ያቀዱ፣