የፒኮክ ፖለቲካ ምንጭ የአጀንዳ እጦት ነው!


“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” ይላል ያገሬ ሰው።ግራ የገባቸው አንዳንድ የፖለቲካ ሐይሎች የፒኮክን ምስል ከቤተመንግስት ለማስነሳት ፊርማ እየሰበሰብን ነው ሲሉ ሰማን፤ጉድ ነው!
እነርሱስ አጀንዳ በማጣት ግራ ገብቶአቸው ነው።ገራሚዎቹ እሺ ብለው የሚፈርሙላቸው ናቸው።ቤተ መንግስት የተገነባውን የፒኮክ ወፍ ምስል ልናስፈርስ ነው ይፈርሙሉን ተብሎ ሲጠየቅ ይገርማል።
መታወቂያችን አንበሳ ነው!(የንጉሳዊያን ነው)።ስልጣን በዘር የሚተላለፍበት።የፒኮክ ፖለቲካን በማራማድ ላይ የሚገኙ ሐይሎች ምን እያሉን እንደሆነ ግልፅ ነው።
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ይህን ያረጀና ያፈጀ የበሰበሰ የገለማ አስተሳሰብ በፍፁም እንደማይቀበሉት መረዳት አለመቻል ድንቁርና ነው።
ለማንኛውም የፒኮክ ፖለቲካ ምንጭ የአጀንዳ እጦት ነው! ለማለት ያህል ነው።በኮቪድ 19 ጊዜ ይህን የፒኮክ ፖለቲካ በመቀበል የሚነጉድ ወገን ካለ እርሱ አልገባውም።ፒኮክዬ እምር ብለሽ ለዘላለም ኑሪ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

invastimantii Oromiyaa caalmatti cimsuuf qajeelfamni dambii haaraan ba'ee hojiirra ooluu eegaleera

Nuu jiraadhu Oromiyaa!!

ቤተ መንግሥት ድረስ ገብተው ጉድ ሊሰሩን የነበሩ የሠራዊቱ አባላት መኖራቸውን ካሰብን......