የኮሮና ሪፖርትና ቆሻሻው ልምምድ

የኢትዮጵያ ከተገለጸ በኋላ በትግራይ ክልል የሚለው ሌላ መግለጫ ችግሩ የማንም ይሁን ያልተገባ ልምምድ ነው፡፡ ሀገር ነን፤ ለህዝብ ክብር ስትሉ ተቀናጁ፡፡
የኮሮና ጉዳይ ሀገራዊ ብቻ አይደለም እንደውም በዓለም ደረጃ የዓለም የጤና ድርጅት ምድርን የተመለከተ አቃፊ ሀሳቦች መረጃዎችና ጉዳዮችን እውን የሚያደርግበት የምድር ቀውስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ መረጃዎችን ብሔራዊ በሆኑ ተቋማት በኩል ስትሰጥ ቆይታለች፡፡ ዘግይተውም ቢሆን ክልሎች የጀመሩት የምርመራ ስራ ውጤቱ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ተቀናጅቶ በጤና ሚኒስትር በኩል ሲነገር ቆይቷል፡፡
አሁንም ቢሆን የሁሉም ክልሎች ውጤትና የኮሮና ወቅታዊ ሁኔታ በማዕከላዊነት በጤና ሚኒስትር በኩል እየተገለጸ ነው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ግን የኢትዮጵያ የሃያ አራት ሰዓት መረጃ ይፋ ከሆነ በኋላ የትግራይ በሚል ሌላ ቁጥር ተነግሯል፡፡
ይሄ ፖለቲካ አይደለም፤ የሰው ህይወትና የሀገር ትርጉም ነው፡፡ ችግሩ ከየቱም ወገን ሊፈጠር ይችላል፡፡ እንዲህ ያለ ቆሻሻ ልምምድ ግን በኢትዮጵያ ምድር ሊኖር አይገባም፡፡ ይሄንን እንደ ህዝብ ልንቆጣው ይገባናል ምክንያቱም ትግራይ ኢትዮጵያ ናት፡፡
ውጤቱ ሳይደርስ የትግራይ ሪፖርት የሚዘገይበት አግባብ ካለ የፌዴራሉን ሪፖርት አዘግይቶ የሃያ አራት ሰዓቱን ሪፖርት አንድ ላይ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ አሊያ ደግሞ ሁሉም ክልሎች በራሳቸው ሚዲያና አግባብ መረጃውን እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡ ኢትዮጵያና ትግራይ ማለት ምን አገባኝ ባይነት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው፡፡ ነውርም ጭምር፤
ትግራይ ኢትዮጵያ ናት፡፡ እንዲህ ያሉ ልምምዶች ፖለቲከኞችን ያሰክራሉ፤ ክፉና ስውር ደባ ያላቸው ሰዎች ልምምዱን ወደ መጥፎ ልዩነት ይዘውት ይጓዛሉ፡፡ በትግራይ የሚደረገው የማዕከላዊ መንግስቱ ኮሮናን የመከላከል እንቅስቃሴ ሊሽኮረመም አይገባውም፡፡ እንደሌላው አካባቢ ሁሉ በትግራይም ኮሮናን ለመከላከል የሚሰራው ስራ በፌዴራል መንግስቱ በአግባቡ ሊታገዝ ይገባዋል፡፡ ከዚያ ውጪ የቱም ወገን አሳስቆ የጥፋት ቢያቆም መልካም ይመስለኛል፡፡ህዝቡ ይከበር፡፡ #Ethiopia
Source:Dire Tube

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa