" እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

 ዋነኛዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ካንሰር የሆነዉ አብን ትላንት ባህር ዳር ላይ "ኦሮሞነት ይዉደም" ሲል ፎክሯል! በግልፅ አማርኛ "ኦሮሞ ይጥፋ" ብሏል! ግን ዛሬ ላይ ኦሮሞንም ሆነ ሌላዉን ብሔር ማጥፋት ፈፅሞ እንደማይቻል አብን እራሱ ጠንቅቆ ያዉቃል! መፈክሩ ከሁለት ዓላማዎች አንዱን ለማሳካታ ተዘጋጅቷል። ከተሳካለት ኦሮሞን በስሜት አነሳስቶ አማራ ወንድሙን እንዲያጠቃ በማድረግ በደም ላይ ተረማምዶ የስልጣን ኮርቻ ይቆናጠጣል! ይህ ካልሆነለት ደግሞ ወንድማማቾችን በማባላት አጥፍቶ በመጥፋት ኢትዮጵያን በታትኖ የነአልሲሲን ፍላጎት ያሟላል!

ይህ አደገኛ ሴራ ነዉ! አብን የጁንታዉ የመንፈስ ልጅ ነዉ የምንለዉ ከዚህ ሴረኝነቱ ይነሳል! ታላቁ የኦሮሞ ህዝብ ደግሞ ትላንት የጁንታዉን ሴራ እንዳከሸፈዉ ሁሉ ዛሬም የጫጩቶቹን አደገኛ ሴራ በማክሸፍ የሀገርን አንድነት ያፀናል! ለዚሀም ባያለበት ሁሉ አማራ ወንድሙን ሊያከብርና ሊያንከባክብ ይገባል! በኦሮሚያ ደግሞ አብን ለወጠነዉ እኩይ ዓላማ በራሱ ማፍያዎች ወይም በወንድሙ ኦነግ ሸኔ አማራ ወንድሞቻችንን ሊያጠቃ ይችላል! ስለዚህ እያንዳንዱ ኦሮሞ በተለይ ወጣቱ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን በጎረቤቱ የሚኖረዉን አማራ ህይወትና ንብረት በአንክሮ መጠበቅ ዋነኛዉ ትኩረቱ ሊያደርግ ይገባል! ታላቅነት የራስን ወንድም በማዉደም ሳይሆን በመዉደድና በመጠበቅ ይገለፃል! ለማንኛዉም የደም ነጋዴዎች ሴራ ይከሽፋል! በህብረ-ብሔራዊነትና በወንድማማችነት ታጅቦ የኢትዮጵያ ሁሉ-አቀፍ ብልፅግና ይረጋገጣል! እያንዳንዳችን የወንድማችን ጠባቂ ነን! #Ethiopia #Oromia

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa