ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ!

 

😢 ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ!
#Ethiopia | ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ መሪዎች ተጎድተውም ቢሆን ኢትዮጵያን እንድ እንዲያደርጉ በእንባ ተማፀነች።
ኮማንደር ደራርቱ ተማፅኖዋን ያሰማችው በቤልግሬድ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ላይ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ላጠናቀቀው የአትሌቶች እና አሰልጣኞች ቡድን በተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ላይ ነው።
" የሀገራችን ጉዳይ ሁላችንንም ያመናል " ያለችው ደራርቱ " የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን አባቶቻችን ናቸው በእርግጠኝነት ደግሞ ነገ ሌላ ቀን ነው ኢትዮጵያ ታርቃ አንድ ሆና ትቆማለች " ስትል ተናግራለች።
ኮማንደር ደራርቱ ፤ ከትግራይ ክልል የተገኙ ድንቅ አትሌቶችን ክብር ይገባችኃል ያለች ሲሆን " በብዙ ፈተናዎች አልፈው በብዙ ተፅእኖ አልፈው የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ስላደረጉ ምስጋና አቅርባለች።
" በእርግጠኝነት ቤተሰቦቻችሁ የት እንዳሉ ታውቃላችሁ " ያለችው ደራርቱ " ግድ የላችሁም እንወዳችኃለን እናከብራችኃለን ፤ እንደልጆቻችን ነው አሁንም የምናያችሁ ስለሆነም ትግራይ ዛሬ ብቻዋን አይደለችም ከኢትዮጵያ ጋር ነች፤ ነገም ከኢትዮጵያ ጋር ትሆናለች " ስትል ተናግራለች።
ኮማንደር ደራርቱ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት መሪዎች ተጎድተውም ቢሆን ለኢትዮጵያ ህዝብ ብላችሁ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓት ስትል በእንባ የተማፀነች ሲሆን " ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ። እናተ አንድ ካደረጋችሁ ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች። " ብላለች።
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ አሜሪካ ፤ በ " H.R. 6600 " ኢትዮጵያንም ሆነ ትግራይን ለመጥቀም ሳይሆን ለመበተን እንደሆነ ተናግራ መሪዎች ከተስማሙ የሚፀድቅበት ምክንያት ስለሌለ ለወደፊት ኢትዮጵያ ሲሉ እዲስማሙ ተማፅናለች።
ህዝቡም በመተባበር #ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርባለች።
TWO LOVELY DOVES WITH OLIVE BRANCH - PEACE SYMBOL
PEACE + LOVE + UNITY + RESPECT

 
Source: Geexuu Tamasgan

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa