አባዱላ ገመዳ ተነሱ፤ ግርማ ዋቄ ተሾሙ

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ግርማ ዋቄ የአየር መንገዱ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ አባዱላ ገመዳን በመተካት በቦርድ ሰብሳቢነት ተሾሙ።

አቶ ግርማ ዋቄ አየር መንገዱን ለሰባት ዓመታት በመምራት ለዕድገት እንዲበቃ መሰረት የጣሉ፣ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ልምድ ያላቸውና በዘርፉ ስኬታማ መሪ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
አቶ ግርማ ዋቄ የአየር መንገዱ የስራ አመራር ቦርድ ሆነው መሾማቸው አየር መንገዱን ለበለጠ ስኬት ሊያበቁ የሚችሉና ተቋሙ ወደፊት ከሚጠበቅበት የዕደገት ደረጃ ሊያደርሱት እንደሚችሉም የታመነ መሆኑንም አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም በሚሰጡት በሳል አመራርና ትክከለኛ ውሳኔ ሰጭነት በተግባር ያረጋገጡ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ibsa Ijjannoo Koree Giddugaleessaa Dhaabbata Dimokiraatawa Ummata Oromoorraa kanname.

Historic speech of PM Dr.Abiy Ahmed(english version)

Akkuma Kaleessaa Har’as Qormaatota Injifinnoon Ceenee, Harka Keenya Galataaf ni Bal’ifna