ልጥፎች

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አዲሱን ዓመት አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕት

ምስል
ክብርት የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ለአንድ እራት አምስት ሚሊዮን ብር የከፈላችሁ እውነተኛ የኢትዮጵያ ባለሃብቶች ዛሬ የዚህ በአል እውነተኛ ታዳሚ በመሆናችሁ ለእናንተም የሚገባችሁን ክብር ሰጥቼ መጀመር እፈልጋለሁ። ብዙ ተስፋ አስቆራጭ ነገር ባለበት ሀገር ውስጥ 16 ሰዓት እየሰራችሁ የቤተመንግስቱን ፕሮጀክት በስድስት ወር ጊዜ ማጠናቀቅ ለቻላችሁ የፕሮጀክት ኃላፊዎች እንደምንችል ለሕዝብ ልምድ ያሣዩና ለእኛም ተስፋ የሆኑ ሙያተኞች በእኛ መካከል አላችሁ። የሚገባችሁን ክብር ሰጥቼ ማለፍ እፈልጋለሁ። በለውጥ እርምጃዎቻችሁ ታጅቦ ላይመለስ በማለፍ ላይ ያለው አመት ከእድሜው ቁጥር በላይ ታላቅ ፈተና የደቀነብን ግን ደግሞ ኢትዮጵያ በፈተና የማትወድቅ መሆኗን ዳግም ያስመሰከረ ዘመን ነበር 2011 ዓ.ም። ያሳለፍነው አንድ አመት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ እንደሀገርና ሕዝብ ለዘመናት ተጭኖ የነበረው ድህነት፣ጉስቁልና የመብት ረገጣና አፈና ጦርነት የመበታተን አደጋ በዘላቂነት እንዲወገድ እንዲሁም የዘመናት ጸረ-ዴሞክራሲያዊ የቁልቁለት ጉዟችን እንዲገታ የጦርነት ታሪካችን ጦርነት ሆኖ እንዳይቀጥል ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከራሳቸው ጋር እንዲታረቁ ፤የዜጎች ክብርና ሀገራዊ አንድነት እንዲረጋገጥ የአንድ አመት ሳይሆን የአስር አመቱን ውዝፍ እዳ የተጋፈጥንበትም አመት ነበር። ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ከለውጥ በፊት የነበሩባቸው አያሌ ጭነቶቻቸው በለውጡ ከጭንቅላታቸው ላይ የተራገፈላቸው ቢሆንም በምትኩ ካረፉባቸው አዳዲስ ጭነቶች ገና አልተገላገሉም። በሕዝብ ትግል ከመጣው ለውጥ በፊት እንደነበሩት በርካታ አመታት በውስጥና በውጭ ግልጽ የሆነ ጦርነት በሀገር ደረጃ ባይኖርም ሰላሙ እረፍት ከሚሰጥበት ዴሞክራሲው ሙሉ በሙሉ ከአፈና የተላቀ...

ለሃይማኖታዊ ግጭት ጅማ የተመረጠችበት ምክንያት!

ምስል
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ያነበብኩት አንድ መረጃ በጅማ ከተማ በሃይማኖት ስም ብጥብጥ ለመፍጠር የተደረገው ጥረት በህዝብና የፀጥታ አካላት ጥረት ከሽፏል ይላል መክሸፉ ጥሩ ነው እንኳን ከሸፈ! የነገሩን ስረ መሰረት ግን ለወደፊት ጥንቃቄ ማድረግ በሚያስችል መልኩ ማየትና መረዳት ያስፈልጋል የሚል እምነት አለኝ በራሴ ግምት ብጥብጡ እንዲነሳ የተፈለገው “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር ሆነን በኦሮሚያ ክልል የራሳችን መዋወቅር ይኑረን” ብለው የጠየቁ አባቶችን በማሸማቀቅ የህዝብ ፍላጎትም ተዳፍኖ እንዲቀር ለማድረግ ነው በዚህ ጉዳይ ወስጥ የብዙ አካላት እጅ ሊኖር ይችላል ከውጭ እስከ አገር ውስጥ በገንዘብና በመሳሰሉት ጉዳዮች ድጋፍ እንደሚደረግ መገመት አይከብድም ከአመታት በፊት ጅማ ከተማና አካባቢዋ ላይ የሆነውን አረመኔያዊ ድርጊት እናስታውስ፤አሁን ጅማ የተመረጠችበትን ተጨባጭ ምክንያት ልንገራችሁ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ቤተክርስቲያን አቃጥለዋል ጉዳት አድርሰዋል በሚል ምክንያት ዘግኛኝ ድርጊት ተፈፅሞ አልፏል እንዲያውም በወቅቱ የደረሰው ጉዳት በምስል ተወስዶ በሲዲ አባዝተው በማሰራጨት ቸብችበው የተጠቀሙ ኃይሎች አሉ አሁንም “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ደርሷል” በሚል ሽፋን በመላ አገሪቱ ህዝቦች እንዲጋጩና አስከፊ ጉዳት እንዲደርስ ፅኑ ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች አሉ እነዚህ ኃይሎች ገንዘባቸውን መድበው በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አትጠራጠሩ!በዚህ ምክንያት ያጡትን ለማግኘት የሚጥሩ የሚፍጨረጨሩ ደፋ ቀና የሚሉ አሉና ልብ እንበል የለውጡ አደናቃፊዎችም በዚህ ዘመቻ ተጠቃሚ ሊሆኑ ስለሚችሉ እንደሚቀላቀሉ አትጠራጠሩ!በጅማ የከሸፈው ጥረት ሌሎች አካባቢዎች ላይም ቢሞከር በፍጥነት ...

ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ከተነሡ፤ ካሰቡት ሳይደርሱ አይመለሱ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

ምስል
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ፡- • ስለማይበገረው ጽናታችሁ እና ሁሉን ማድረግ ስለሚችለው አስደናቂ አቅማችን በተለየ አክብሮት እና ፍቅር እጅ እነሳለሁ፡ ፡ • በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነን እንኳን ሀገራችንን የሚመለከቱ አበይት ጉዳዮች ሲገጥሙን ከመቅጽበተ አይን ለሚያጋምደን- ያለምንም ልዩነት እንደ አንድ እናትና ልጅ ለሚያዛምደን እና ያለመለያየት ለሚያዋህደን ዘመን አይሽሬ ኢትዮጵያዊ መንፈሳችን ያለኝን የማይናወጥ ፍቅር በክብራችሁ ጥላ ስር ሆኜ በክብር እገልጻለሁ፡፡ • መቼም- ማንም የትኛውንም የክፋት ሴራ የሚሰራ የጥፋት አበጋዝ አብሮነታችንን ሊያጠለሽ ቢጥር እንኳን አብሮነታችን ከነፍሳችን ውስጥ የተሸመነ እንጂ ከስጋችን ላይ የተጎነጎነ አይደለምና አብሮነታችንን ላጸደለው የአረንጓዴ አሻራ ድላችሁ የተለየ ምስጋናዬን በፍቅሬ ሙዳይ ሞሽሬ እነሆ ልኬያለሁ፡፡ ሀገር ታመሰግናለች- እኔም አመሰግናለሁ፡፡! የኢትዮጵያን አረንጓዴ ጸጋ በመመለስ አረንጓዴ አሻራ እንድናሳርፍ ያቀረብኩትን ጥሪ በመቀበል ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በነቂስ ለችግኝ ተከላ ወጥቷል፡፡ ከጨቅላ ሕጻናት እስከ ዘጠና ዓመት አዛውንት፣ ከጎዳና ተዳዳሪዎች እስከ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ፣ ከታክሲ ተራ አስከባሪዎች እስከ ጸጥታ አስከባሪዎች፣ ከገበሬዎች እስከ ግብርና ባለሞያዎች፣ ከልማት ጣቢያ ሠራተኞች እስከ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች፣ ከተማሪዎች እስከ መንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከሀገር ቤት እስከ ዳያስፖራ፣ ከድምጻውያን አስከ ተዋንያን፣ ከአትሌቶች እስከ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች፣ ከጋዜጠኞች እስከ ፊልም ባለሞያዎች፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ - ያልተሳተፈ የኅብረተሰብ ክፍል አልነበረም፡፡ ይህ የተሳትፎ ማእበል እና የእ...

Gabaan yoo maraattu waliin maraachuu hin qabnu!

Finfinnee Adoolessa 15/2011(Tolawaaq waarii) ammaa shira hojjetamuun gatiin omisha adda addaa dabaleera. Gochi kun beekaa akka raawwatamu shakkiin jira Hundumaafuu yoo gabaan maraattu waliin maraachuu hin qabnu.Haa maraatan.Jireenya keenyaaf filmaata mijeeffachuun utuu callifnee ilaallee daldaalaan maraate hundi gara fayyummaatti deebi'uunsaa hin oolu.Waan isaan akka qaalawu taasisan yeroof yoo dhiifne hin duunu. Inuma jiraanna.Biddeen xaafii nyaanna yoo ta'e nyaata biraa jijjiiruun kanneen xaafii daldalan kasaarsuu dandeenya.Foon nyaanna yoo ta'e waan foon bakka bu'utti fayyadamuu dandeenya.Mee tarkaanfii kana fudhachuun warra nutti roorrisutti haa roorrifnu!

Hayyoonni har'a Magaalaa Dirree-Dhawaatti mari'atu

ምስል
Finfinnee Adoolessa 15/2011(Tolawaaq waarii) Waltajjiin marii dhimmoolee biyyaa irratti xiyyeeffatuufi hayyoota gara garaa hirmaachisu har'a Dirree-Dhawaatti adeemsifamaa oola Ministirri itti gaafatamaan pirees seektiriyaatii waajjira muummicha ministiraa Ob.Nugusuu Xilaahuun kaleessa galgala akka himanitti waltajjii marii moggaasa አዲስ ወግ jedhamuun kanaan dura eegalame har'a Dirree-Dhawaatti itti fufee oola. Hayyoonni biyyaa dhimma misoomaafi guddina biyyaafi yaadawwan haarawa qabatanii gara fuulduraatti akka dhufan taasisuun kaayyoo marichaa akka ta'edha Obbo Nugusuun kan himan. Waltajjichi dhimmoolee bu'uraa biyya keenyaa irratti waliigaltee biyyaalessaa uumuufi jijjiirama cimsuuf kan gargaaru akka ta'e himameera.

Hoj-maneen nutti baay’ifame gabrummaa waggaa 150 hin caalu!

ምስል
Finfinnee Adoolessa 10/2011(Tolawaaq Waarii) Har’a Oromootu Itiyoophiyaa bulchaa jira.Oromoon carraa kana kennaadhaan hin arganne.Qabsoo bara dheeraa lakkoofsiseen mirga abbaa biyyummaa argate.Wanti akkanumatti kennamu hin jiru.Ifaajiitu bu’aa barbaadamu argamsiisa.Oromoon ifaajiisaa bara hedduutiin rakkoo hedduu isarra gahaa ture dandamatee injifatee har’a irra ga’e. Amma imala injifannoorra jirra.Imalli injifannoo   Oromoo ammoo akka argaafi dhag’aa jirrutti gufuun itti heddummatus daran cimee itti fufa malee gonkumaa duubatti akka hin deebine beekamuu qaba!Numa keessaa dhugaa kana hubachuu kan dadhabetu oliif gadi raafamee diinni Oromoo akka wixiffatu taasisaa jira.Wixiffannaa diinaa kana kan dhabamsiifnu tokkummaa keenya yoo cimsinedha. Tokkummaa Oromoo akka sibiilaatti yoo jabeessine diinni nu sodaatti.Diinni duruu nu sodaatti.Diinni waan sodaattuuf sababa adda addaa uumtee akka nuti adda facaanuufi wal hin taane gooti.Kan Oromoo taatee dhalatte hundi dh...

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ምስል
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የሲዳማ ዞን መስተዳደር ምክር ቤት ውሳኔን መሰረት በማድረግ በህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ለመወሰን ህዝበ ውሳኔ እንዲደራጅለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንደ አዲስ የማደራጀት፣ የምርጫ ቦርድ ስልጣንና ተግባር የሚወስነውን ህግ የማርቀቅ እና በተወካዮች ምክር ቤት የማጸደቅ፣ የምርጫ ህጎችን የማሻሻል፣ ተቋማዊ ለውጦችን የማከናወን እንቅስቃቄ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ከነዚህ ተቋማዊ ለውጦች መካከል የቦርዱን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት አድርጎ የተከናወነው የምርጫ ቦርድ አባላት መረጣ ዋነኛው ነው ፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ የቦርድ አባለት መረጣ ሰፊ ምክክርና ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጐበት ከተለየ በኋላ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 06 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ተጨማሪ አራት የቦርድ አባላት ሹመት ተከናውኖ ቦርዱ አባላት ተሟልተውለት ስራውን ጀምሯል፡፡ ቦርዱ ተሟልቶ ስራ በጀመረበት ባለፈው አንድ ወር በእንጥልጥል የሚገኙ እና አስቸኳይ ናቸው ያላቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በቦርዱ አለመሟላት ምክንያት በእንጥልጥል ከቆዮት ጉዳዮች አንዱ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለቦርዱ የቀረበው የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ህዝበ ውሳኔ ማደራጀት ነው፡፡ ቦርዱ ስራ ከጀመረ አንስቶ የሲዳማ ዞን ክልልነትን የሚመለከቱ በተለያዩ ጊዚያት የቀረቡትን ጥያቄዎች ከመመልከቱም በላይ ከክልሉና የዞን መስተዳድር አመራሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡ እንደሚታወቀው የሲዳማ ዞን የክልልነት ህዝበ ውሳኔ የማደራጀት ጥያቄ ...