በአዲሱ የኦሮሚያ አመራር የጥገኞቹ ስጋት ለምን?
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በ2009 ዓ.ም መጀመሪያ ወራት ላይ ወደ ኃላፊነት ከመጡ ወዲህ በአጠቃላይ የኦሮሞ ሕዝብ በተለይም የኦሮሚያ ወጣቶች ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት ያለምንም ማቅማማት እንዲረጋገጥ ብርቱ ጥረት በማድረግ የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ገና በመጀመሪያው ዓመት የስልጣን ዘመናቸው በማስመዝገብ ላይ ያሉት ለውጥ ቀጣይና የሰፊውን የኦሮሞ ሕዝብ ድጋፍ በማግኘት ተጠናክሮ መቀጠል የሚችል መሆኑን ብዙዎች ከወዲሁ ገምተዋል፤ መገመት ብቻ ሳይሆን በርዕሰ መስተዳድሩ ቁርጠኛ አካሄድ በልበ ሙሉነት ተማምነዋል ማለትም ይቻላል። አቶ ለማ መገርሳ በክልሉ ይበል የሚያሰኝ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ የሚገኙት በሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ድጋፍና በአካባቢያቸው ካሉ አመራሮች በሚያገኙት እገዛ መሆኑ ግልፅ ነው የርዕሰ መስተዳድሩ ቁርጠኝነት ምንም ያህል ጠንካራ ቢሆን በኦሮሞ ሕዝብና በአካባቢያቸው ከሚገኙ አመራሮች የተሟላ ድጋፍ ስላላቸው እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፤ከሶስት ሚሊየን በላይ የሆነው ትክክለኛ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አባላትና ትክክለኛ የእህት ድርጅቶች አባላትም ከክቡር አቶ ለማ መገርሳ ጎን መሆናቸው ሊዘነጋ አይገባም! ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በክልሉ በየዘርፉ የሚታዩ ፖለቲካዊ፤ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች ደረጃ በደረጃ አስተማማኝ መፍትሄ እንዲያገኙ የሚሰሩ እንዲሁም የኦሮሚያን ሕዝብ በብቃት መምራት የሚችሉና የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ለአገር አንድነትና ዕድገት ሲያበረክት የኖረውን የማይተካ አስተዋፅኦ በማስተባበር ማስቀጠል የሚችሉ ብቁ አመራር ናቸው። ይህን ሃቅ በመካድ የክቡር አቶ ለማ መገርሳንና በአቅራቢያቸው የሚገኙ አመራሮችን መልካም ...