በአዲሱ የኦሮሚያ አመራር የጥገኞቹ ስጋት ለምን?

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በ2009 ዓ.ም መጀመሪያ ወራት ላይ ወደ ኃላፊነት ከመጡ ወዲህ በአጠቃላይ የኦሮሞ ሕዝብ በተለይም የኦሮሚያ ወጣቶች ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት ያለምንም ማቅማማት እንዲረጋገጥ ብርቱ ጥረት በማድረግ የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ
ርዕሰ መስተዳድሩ  ገና በመጀመሪያው ዓመት የስልጣን ዘመናቸው በማስመዝገብ ላይ ያሉት ለውጥ ቀጣይና የሰፊውን የኦሮሞ ሕዝብ ድጋፍ በማግኘት ተጠናክሮ መቀጠል የሚችል መሆኑን ብዙዎች ከወዲሁ ገምተዋል፤ መገመት ብቻ  ሳይሆን በርዕሰ መስተዳድሩ ቁርጠኛ አካሄድ በልበ ሙሉነት ተማምነዋል ማለትም ይቻላል።

አቶ ለማ መገርሳ በክልሉ ይበል የሚያሰኝ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ የሚገኙት በሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ድጋፍና በአካባቢያቸው ካሉ አመራሮች በሚያገኙት እገዛ መሆኑ ግልፅ ነው የርዕሰ መስተዳድሩ ቁርጠኝነት ምንም ያህል ጠንካራ ቢሆን በኦሮሞ ሕዝብና በአካባቢያቸው ከሚገኙ አመራሮች የተሟላ ድጋፍ ስላላቸው እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፤ከሶስት ሚሊየን በላይ የሆነው ትክክለኛ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አባላትና ትክክለኛ የእህት ድርጅቶች አባላትም ከክቡር አቶ ለማ መገርሳ ጎን መሆናቸው ሊዘነጋ አይገባም!
ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በክልሉ በየዘርፉ የሚታዩ ፖለቲካዊ፤ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች ደረጃ በደረጃ አስተማማኝ መፍትሄ እንዲያገኙ የሚሰሩ እንዲሁም የኦሮሚያን ሕዝብ  በብቃት መምራት የሚችሉና የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ለአገር አንድነትና ዕድገት ሲያበረክት የኖረውን የማይተካ አስተዋፅኦ በማስተባበር ማስቀጠል የሚችሉ ብቁ አመራር ናቸው።
ይህን ሃቅ በመካድ የክቡር አቶ ለማ መገርሳንና በአቅራቢያቸው የሚገኙ አመራሮችን መልካም ጥረት ለማጉደፍ ከቻሉም ለማኮላሸት የተለያዩ ስያሜዎችን ለመስጠት በመሯሯጥ ላይ የሚገኙ ኃይሎች እየተስዋሉ ነው የእነዚህ ኃይሎች አሉባልታዎችን መንዛትና መንፈራገጥ ከግልፅ ጠላትነት ተለይቶ ሊታይ አይችልም ይህ የጠላትነት አካሄድ ደግሞ ለአቶ ለማ ብቻ ሳይሆን ለሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ጭምር መሆኑን የስም አጥፊ ኃይሎችን እኩይ አካሄድ መነሻ በማድረግ መተርጎም ይቻላል
ርዕሰ መስተዳድሩ በመርህ ላይ ተመስርተው የክልሉን ሕዝብና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም ረገድ ተጠቃሚ ለማድረግ በመስራት ላይ ይገኛሉ፤ይህን እውነታ በቅንነት የሚያስብ ዜጋ ሁሉ መገንዘብ የሚችል መሆኑ ግልፅ ነው
በርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳ ላይ ከሚወሩ መሰረተ ቢስ አሉባልታዎችና ክሶች ውስጥ በጥቂቱ ለማየት ከኢንቬስትመንት ስራና የክልሉ ወጣቶች ተጠቃሚነት ጋር አያይዘው የተናገሩትን ብቻ ለማሳያነት ስለሚረዳ ላንሳ፤አቶ ለማ በተለያዩ መድረኮች ላይ በሚያሰሟቸው ንግግሮች የሕዝብን ፍላጎትና ስሜት መኮርኮርና መያዝ የሚችሉ ንግግሮችን ማድረግ እንደሚችሉ በተግባር አረጋግጠዋል በደረቅ የካድሬ ጩኸት ሕዝብን የሚሸነግሉ እንዳልሆኑም ተናግረው በተግባር ባሳዩት ስራቸው አረጋግጠዋል።
ለምሳሌ አቶ ለማ “የኦሮሞን ወጣቶች ተጠቃሚ ማድረግ የማይችልና የኦሮሚያን ወጣቶች ያገለለ የኢንቬስትመንት ስራ አያስፈልገንም ይቅርብን” ብለዋል አልተሳሳቱም ትክክል ናቸው።ከኢትዮጵያ ሶማሌና የኦሮሚያ ክልል የድንበር ላይ ግጭት ጋር በተያያዘም “የችግሩ ምንጭ ለዘመናት አብሮ የኖረው የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ሳይሆኑ የአካባቢው ኪራይ ሰብሳቢ አመራሮች ናቸው፤ከአስር አመት በፊት የተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ሳይተገበር መቆየቱም ሌላው ምክንት ነው” ሰሉ ተናግረዋል በዚህ ላይም አቶ ለማ ምንም የተሳሳቱት ነገር የለም ትክክል ናቸው።
መሰረተ ቢስ አሉባልታዎቹ ደግሞ “በህጋዊ የንግድ አሰራር ስም የሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ነጋዴዎች በክልሉ እንዳይሰሩ አድርገዋል፤በወጣቶች ተጠቃሚነት ስም በግል ባለሃብቶች ላይ ተፅዕኖ እያደረሱ ነው፤ለኢትዮጵያ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልል የድንበር ግጭት በቀድሞው አመራር ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል፤በክልሉ የኢኮኖሚ አብዮት ስም ሌሎች ላይ ስጋት እንዲፈጠር አድርገዋል” የሚል ነው።
የርዕሰ መስተዳድሩ ቁርጠኛ አመራር ኪራይ ሰብሳቢውን ለምን አሳሰበ?
ቀደም ባሉ አመታት ኦሮሚያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶች(አሸዋ፤እነ ፑሚስ የኖራ ድንጋይ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ግብአት፤ጠጠርና በመሳሰሉት) ተጠቃሚ በመሆን የተንደላቀቀ ኑሮ መኖር የቻሉት በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ግለሰቦች ነበሩ እነዚህ ግለሰቦች ምንም ጉልበት ባላፈሰሱበት ተጨማሪ ግብአት ባልጨመሩበት የተፈጥሮ ሃብት ለራሳቸው የተሻለ ኑሮ መኖር ቢችሉም በአካባቢያቸው ለሚገኙ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር ሳይችሉ የቆዩ ናቸው ወጣቶቹን ከነመፈጠራቸውም ረሷቸው ማለት ይቀላል
አዲሱ የኦሮሚያ አመራር ቡድን ለዚህ ጉዳይ ጊዜ መድቦ በጥሞና  ተወያይቶ ትክክለኛ አቅጣጫ ካስቀመጠ በኋላ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገባ ካደረገ ወዲህ ተጨባጭ ለውጦች በመታየት ላይ ናቸው፤በዚህም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ስራ አጥ የነበሩ ወጣቶች ገቢ በማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ማዳበር ጀምረዋል፤በአጭር ጊዜ ውስጥ በመታየት ላይ በላው ለውጥ ብግን ያለው ኪራይ ሰብሳቢ በተለያዩ ስልቶች የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶ በመንፈራገጥ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል ነገሩ ግን እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል ስለሆነባቸው ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ሲረዱ በመንፈራገጥ ላይ ይገኛሉ
በአዲሱ የኦሮሚያ አመራር የጠባቡ  ኃይል ስጋት ለምን?
በአሁኑ ወቅት ኦሮሚያን ለመምራት ዕድል ያገኘው የአመራር ስብስብ የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ በህገ መንግስታችን ዋስትና ባገኙ መብቶች ሁሉ ተጠቃሚ መሆን እንዲችል ወስኖ በመስራት ተጨባጭ ለውጦችን በማስገኘት ላይ የሚገኝ ስመ ጥር አመራር ነው።በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ጠባብ ኃይሎች በአሁኑ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ቁርጠኛ አመራር ውሳኔዎችና አጠቃላይ እንቅስቀሴዎች ደስተኛ እንደማይሆን በግልፅ ይታወቃል።
እዚህም እዚያም ያለው ጠባብ ኃይል የአዲሱን አመራር አካሄድ በቅንነት ማየት የማይችልባቸው በርካታ ምክንያቶች አንዳሉ መገመት ይቻላል።የመጀመሪያውና ዋነኛው ምክንያት የግዙፍ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ምንጭ የሆነው ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ እንቅስቀሴ ከእጃችን እንዲያመልጥ እያደረጉ ነው የሚል ሲሆን፤የክልሉ ሕዝብ ለመብቶቹ መከበር በፅኑ አቋም እንዲከራከርና መብቱን ለማስከበር እንዲቆም በማድረግ ላይ ናቸው የሚል ነው
በአሁኑ ወቅት ኦሮሚያ ውስጥ ባለው ለውጥ በውጭ አገር የሚገኘው የኦነግ ርዝራዥና የአገር ውስጥ ጠባብ ኃይሎች ስጋት ውስጥ ገብተው ቢንፈራገጡ ምንም አይገርምም፤ምክንያቱም ለመብቱ መከበር የቆመና በሃሰት ፕሮፓጋንዳ የማይነዳ ይልቁንም በምክንያት የሚከራከር፤የቀድሞና የአሁን ተጠቃሚነቱን በማነፃፀር አይቶ በማመዛዘን የሚረዳ ህብረተሰብ ተፈጥሯልና
ይህን የነቃና ለመብቶቹ መከበርና ለተጠቃሚነቱ መቆም የቻለን ሰፊ ሕዝብ በትክክለኛ መስመር መምራት የሚችል አመራርም መፈጠር መቻሉ ጠባቡን ኃይል በሁሉም ረገድ ስጋት ውስጥ ማስገባቱ ግድ የሆነበት ወቅት ላይ እንገኛለን።እኛ ኦሮሞዎች ይህን ጉዳይ “ምቀኛ አታሳጣኝ በሚል ብሂል አልፈነዋል;ለክልላችን ሰላም ልማትና ዴሞክራሲ መረጋገጥ እንዲሁም ለአገራችን ኢትዮጵያ ዕድገትና ብልፅግና እውን መሆን በቁርጠኝነት በመስራት ላይ እንገኛለን! ሰላም።









አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa