የክልሉ መንግስት የሪፖረተር ጋዜጣን ዘገባ ሀሰተኛ ነው በማለት ኮነነ በህግም እጠይቃለሁ ብሏል
የክልሉ መንግስት የሪፖረተር ጋዜጣን ዘገባ ሀሰተኛ ነው በማለት ኮነነ በህግም
እጠይቃለሁ ብሏል
በአቶ አማረ አረጋዊ ባለቤትነት የተያዘው የሪፖረተር ጋዜጣ ሚያዝያ 6/2009
ባወጣው ዕትም “የማዕድን ቦታ እንዲያስረክቡ የታዘዙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከኦሮሚያ ጋር በመደራደር ይዞታቸውን አስከበሩ” በሚል ርዕስ ያወጣውን ዘገባ የክልሉ መንግስት የኮሙኒክሽን ጉዳዮች ቢሮ በአፅንኦት
ኮነነ
ጋዜጣው
በሃሰት ያወጣውን ዘገባ አስተባብሎ የክልሉን መንግስት ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ በሕግ ለመጠየቅ እንደሚገደድም ቢሮው አስታቋል
የኦሮሚያ
ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ወጣቶች በሚጎዳ መልኩ ከየትኛውም አካል ጋር እንዳልተወያየና ወደፊትም ለመወያየት ፍላጎትና
እምነት እንደሌለው ጠቁሟል
ከሲሚንቶ
ፋብሪካዎች ጋር በተያያዘ የክልሉን ወጣቶች ተጠቃሚነት አስመልክቶ ህብረተሰቡ የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖረው በቀጣይ በኦሮሚያ ቴሌቪዥንና
ሬዲዮ ድርጅት ተከታታይ ዘገባዎች እንደሚቀርቡም ተነሯል
የሪፖርተር
ጋዜጣ አሳትሞ አሰራጭቷል የተባለው ዘገባ ቀጥሎ ያለው ነው ያንብቡ፡http://ethiopianreporter.com/content/%E1%8B%A8%E1%88%9B%E1%8B%95%E1%8B%B5%E1%8A%95-%E1%89%A6%E1%89%B3-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B2%E1%8B%AB%E1%88%B5%E1%88%A8%E1%8A%AD%E1%89%A1-%E1%8B%A8%E1%89%B3%E1%8B%98%E1%8B%99-%E1%8B%A8%E1%88%B2%E1%88%9A%E1%8A%95%E1%89%B6-%E1%8D%8B%E1%89%A5%E1%88%AA%E1%8A%AB%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%8A%A8%E1%8A%A6%E1%88%AE%E1%88%9A%E1%8B%AB-%E1%8C%8B%E1%88%AD-%E1%89%A0%E1%88%98%E1%8B%B0%E1%88%AB%E1%8B%B0%E1%88%AD-%E1%8B%AD%E1%8B%9E%E1%89%B3%E1%89%B8%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%8A%A8%E1%89%A0%E1%88%A9
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ