ይፋዊ ጉብኝቶችን አስመልክቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቃባይ አቶ መለስ አለም የተሰጠ ማብራሪያ



በክቡር ጠቅላይ / ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና በውጭ ጉዳይ / ክቡር / ወርቅነህ ገበየሁ የተደረጉ ይፋዊ ጉብኝቶችን አስመልክቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቃባይ አቶ መለስ አለም የተሰጠ ማብራሪያ


መግቢያ
በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙትና አገራችን በረጅም ጊዜ ታሪክ የተሳሰረቻቸው ጎረቤት አገሮች ማለትም ኬንያ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኤርትራ እንዲሁም እንደ ዩጋንዳ ያሉ አገራት ለአገራችን ሰላም፣ ዲሞክራሲና ዘላቂ ልማት መረጋገጥ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳላቸው የማይካድ እውነታ ነው፡፡ አገራችን ከሌሎች አገሮች ጋር ስለሚኖራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ስናነሳ ጎረቤት አገሮችን በቀዳሚነት ማንሳት እንዳለብን በውጭ ጉዳይና አገራዊ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ በግልፅ የተቀመጠ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህም፡-
1. ኢትዮጵያ ከነዚህ አገራት ጋር ተመሳሳይ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክና የተፈጥሮ ሀብት የሚጋሩ ህዝቦች ያሏት መሆኑ አገራቱ ከሌሎች አካባቢዎች በተለየ ከአገራችን ጋር ቀጥተኛ የሆነ ትስስር እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡
2. በእነዚህ አገሮች የሚኖር ሰላም እና ፀጥታ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በአገራችን ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ አለው፡፡ ከዚህም በመነሳት አገራችን ከጎረቤት አገራት ጋር ባላት ግንኙነት ዙሪያ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ነው፡፡ በአንድ በኩል ከብዙዎቹ ጋር ስትራቴጂክ አጋርነት መፈራረም ተችሏል፡ በሌላ በኩል ሰላም እና መረጋጋት የራቃቸው ጎረቤቶቻችንን ለማረጋጋት ህይወትም ገንዘብም እየገበርን ነው፡፡ ይህም በአፍሪካ ቀንድ ለሚገኙ አገራት በአገራችን በኩል ለተሰጠው ትኩረት እንደ ማረጋገጫ ነው፡፡
3. በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት በኋላም የአፍሪካ ህብረት ላይ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ተባብራ ስትሰራ መቆየቷ ይታወቃል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ አገራችን ባለፉት አስር አመታት ያስመዘገበችው ኢኮኖሚያዊ ለውጥ በብዙዎች ዘንድ ከአገራችን ልምድ የመማር ፍላጎትን አጭሯል፡፡
በያዝነውም አመት (... 2017) የውጭ ጉዳይ በህግ በተሰጠው ሀላፊነት መሰረት የተከናወኑ ተግባራትን ብናይ፡-
/ሚኒስትር /ማርያም ደሳለኝ በዩጋንዳ፣ በታንዛንያ እና በዛምቢያ ይፋዊ ጉብኝት (Official Visit ) አድርገዋል እንዲሁም በሶማሊያ በአለ ሹመት ላይ ተገኝተዋል፡፡
የደቡብ ሱዳን፣ የጅቡቲ፣ የላይቤሪያ፣ የሱዳን ፕሬዝዳንቶች በአገራችን በመገኘት ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር / ወርቅነህ ገበየሁ በተመሳሳይ በኬንያ፣ በጅቡቲ፣ በሱዳን ወዘተ በመገኘት ከአገሪቱ መሪዎች እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረዋል፡፡
በመሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደረጃ በተካሄዱት ይፋዊ ጉብኝቶች ምን ውጤት ተገኘ?
1. 20 በላይ ስምምነቶች ከደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ላይቤሪያ፣ ዛምቢያ፣ ዩጋንዳ ጋር ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቶቹ በጸጥታ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የተመሩ ነበሩ፡፡
ምሳሌ፡- በመንገድ ግንባታ የኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ጋር የንግድ እና ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት፣
- በመንገድ ግንባታ የኢትዮ-ደቡብ ሱዳን የወዳጅነት መንገድ ግንባታ ዕቅድ ይፋ ሆኗል፣
- ከታንዛኒያ ጋር በስትራቴጂካዊ አጋርነት መስክ ለመተባበር የተፈረሙት ስምምነቶች ይጠቀሳሉ፡፡
2. ጉብኝቶቹን ተከትሎ የደቡብ ሱዳን መንግስት በናይል ላይ የተፈረመውን Comprehensive Frame work Agreement (CFA) ለመቀበል ካቢኔ ስብስቦ ውሳኔውን አሳውቋል፡፡ በታንዛኒያ መንግስት በኩል የናይልን ውሃ በተመለከተ ... 1929/59 የተደረሰው የቅኝ ግዛት ስምምነት ተቀባይነት እንደሌላው በማያወላዳ ቋንቋ አስቀምጧል፡፡ CFA ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዕልባት ለማበጀት መሪዎቹ ተስማምተዋል፡፡
3. የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብን (EACC) ለማቋቋም መሪዎቹ በድጋሜ ቁርጠኝነታቸውን የሚያረጋግጡበት ዕድል ፈጥሯል፡፡
4. ዛምቢያ እና ታንዛኒያ ውስጥ በህገወጥ ገብተው በቁጥጥር ስር የነበሩ በመቶዎቹ (600) የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተፈተው አገራቸው እንዲመለሱ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
5. የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት ኢጋድ እንዲጠናከር፣ ለሶማሊያ ዳግም ግንባታ ድጋፍ እንዲደረግ፣ ለደቡብ ሱዳን ሰላም የተፈራረመው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ የቀረበበትና በምስራቅ አፍሪካ ያለውን የድርቅ ችግር በጋራ ለመፍታት እንዲሁም ለጋሾች የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
I. ጅቡቲ
ኢትዮጵያና ጅቡቲ ለረጅም ዘመናት የቆየና የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው አገራት ናቸው፡፡ በሁለቱ አገራት ህዝቦች መካከልም ከፍተኛ የሆነ ግንኙነት መኖሩ የበለጠ የተሳሰሩ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ በአገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮች ዙሪያ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡ እስካሁንም የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ማለትም የባቡር መስመር ዝርጋታ፣ የመንገድ ግንባታ፣ የውሀ መስመር፣ የስልክ መስመር እንዲሁም የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የመሳሰሉት መገንባታቸው በሁለቱ እህትማማች አገራት መካከል ያለውን ትስስር የበለጠ ለማጠናከር መንገድ ከፋች ነው፡፡ የክልሉን ሰላምና ፀጥታም አስመልክቶ በሁለቱ አገራት መካከል እየተሰራ ያለው ስራ ቀላል የማይባል ነው፡፡ ሁለቱ አገራት በሚገናኙባቸው እንደ ኢጋድ፣ ኮሜሳ፣ አፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ላይ እያሳዩ ያሉት ትብብር የሁለቱን አገራት ወዳጅነት ማሳያ ነው፡፡
የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር እስማኤል ኦማር ጌሌ ከመጋቢት 07-09 ቀን 2009 . በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ፕሬዝዳንቱ ፓርላማ በመገኘት ንግግር አድርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በጉብኝቱ ወቅት አራት ስምምነቶችን መፈራረም ተችሏል፡-
ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት (Agreement on Extradition)
በወንጀል መከላከል ጉዳዮች ላይ የጋራ የህግ ስምምነት(Agreement on Mutual Legal Assistance on Criminal Matters)
በፍትህና የህግ ስልጠና ዘርፎች ለመተባበር የጋራ መግባቢያ ሰነድ (Memorandum of Understanding on Cooperation in the Fields of Justice and Legal Training) እና
• (የንግድ ስምምነት) Agreement on Trade
በአጠቃላይ የሁለትዮሽ ውይይቱ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ የሚገኘውን የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ውህደት ለማፋጠን መሪዎቹ ቁርጠኝነታቸውን ያሳዩበት መድረክ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ውይይቱ የቀጠናውን የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ላይ አገራቱ በጋራ በመመካከር ለመስራት መግባባት ላይ የተደረሰበት ነበር።
II. ሱዳን
አገራችን ከሱዳን ጋር የቆየና የጠበቀ ግንኙነት አላት፡፡ ሁለቱ አገራት ረጅም ድንበር የሚጋሩ ከመሆናቸውም ባሻገር በአገራቱ መሪዎች መካከል የጠበቀ ግንኙነት ያለ መሆኑ በሁለቱ አገራት መካከል ላለው ትስስር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ሁለቱ አገራት በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በቅርበት እየሰሩ ያሉ ከመሆናቸውም ባሻገር በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያም በጋራ በተለይ በድንበር አካባቢ ባሉ ህዝቦች ላይ በማተኮር እየሰሩ ነው፡፡ ሁለቱ አገራት በመንገድ፣ በኤሌክትሪክ እንዲሁም በባቡር የተገናኙ ሲሆን በያዝነው አመትም (... 2017) የየብስ ህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት (passenger road transport) መጀመሩ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ጠንካራ እንዲሆን አድርጓል፡፡
... ከአፕሪል 04-06, 2017 ባሉት ቀናት የሱዳን ፕሬዝዳንት ክቡር ኦማር ሀሰን አልበሽር አገራችንን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት መሪዎቹ የሁለቱ አገራት ግንኙነቶች የበለጠ በሚጠናክሩባቸው አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ ከነዚህም በአገራቱ መካከል ያለውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ ከዚህ በፊት በአገራቱ መካከል ከዚህ ቀደም የተፈረሙ ስምምነቶችን ማጠናከር፣ በናይል ዙሪያ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማስኬድ እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ሰላም ለማስፈን በአገራቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የበለጠ ማጠናከር ላይ በስፋት መወያየታቸው የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
III. ደቡብ ሱዳን
በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት የተለየ ግንኙነት ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡ ሁለቱ አገራት ድንበር ከመጋራታቸውም ባሻገር የሚጋሩት ተመሳሳይ ህዝብ ያላቸው አገራት ናቸው፡፡ ደቡብ ሱዳኖች ለነፃነት ካደረጉት ትግል አንስቶ ነፃ እስከወጡበት ጊዜ ድረስ በአገራችን በኩል ከፍተኛ እገዛ ሲደረግላቸው የቆየ ሲሆን ከነፃነት በኋላም በደቡብ ሱዳን በተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት አገራችን በግልም ሆነ እንደ ኢጋድ ዋና ሊቀ መንበርነቷ ከፍተኛ የሆነ ሚና ተጫውታለች፡፡ ጦርነቱን ሸሽተው ወደ አገራችን ለተሰደዱ ደቡብ ሱዳናውያን የተደረገው አቀባበልና መስተንግዶ በሁለቱ አገራት መካከል ላለው ከፍተኛ ትስስር ምስክር ነው፡፡
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ክቡር ጄኔራል ሳልቫ ኪር ... ከየካቲት 23-25, 2017 ባሉት ቀናት በአገራችን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ጉብኝቱ በአገራቱ መካከል የዘለቀውን ወዳጅነትና ትብብር የበለጠ እንዲጠናከር አድርጓል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ስምንት ስምምነቶች የተፈረሙ ሲሆን እነዚህም፡
በመንገድና በድልድይ ለማገናኘት የሚያስችል የትብብር ስምምነት(Agreement on Cooperation on Roads and Bridges);
በመንገድ ግንባታ የጋራ ትብበር ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ(MoU on Bilateral cooperation on the Construction of Roads);
በነዳጅ ማስተላለፍ ሂደት የመግባቢያ ስምምነት(Memorandum of Understanding on Diesel Off-take Arrangement);
በሀይል ዘርፍ የመግባቢያ ስምምነት(Memorandum of Understanding in the Field of Energy);
የድንበር ንግድ ፕሮቶኮል(Border Trade Protocol);
የተመረጠ የንግድ ስምምነት(Preferential Trade Agreement);
በጤና ዘርፍ ለመተባበር የመግባቢያ ስምምነት(MoU on cooperation in the field of Health); እና
በኮሚኒኬሽን፣ በመረጃ ልውውጥ በመገናኛ ብዙሀን ተጨማሪ ስምምነቶች(An Additional Agreement on Communication, Information and Media)
ከተፈረሙት ስምምነቶች በተጨማሪ መሪዎቹ የአገራቱን የኢኮኖሚ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የእቃዎችና የሰዎች ነፃ ዝውውር አስፈላጊ በመሆኑ በአስቸኳይ Gambella – Pagak – Palouge እንዲሁም Dima - Raad – Boma – Bor መንገዶች ግንባታ እንዲጀመር ወስነዋል፡፡ ይህም ከዚህ በፊት የነበረውን የአገራቱን ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያሳድግ ታምኖበታል፡፡
IV. ዩጋንዳ
አገራችን ኢትዮጵያና ዩጋንዳ ጠንካራና የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ከመሆናቸው ባሻገር በክልላዊ እንዲሁም በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ አጋርነታቸውን ያሳዩ አገራት ናቸው፡፡ በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚከናወኑ ስራዎች ላይ በተለይም በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን ሰላም የማስፈን ጥረቶች ሁለቱ አገራት በተናጠልም ሆነ በጋራ በኢጋድ ማዕቀፍ ውስጥ ያበረከቱት ቀላል የማይባል አስተዋፅኦ አገራቱ ከፍተኛ የሚባል አጋርነት ያላቸው ለመሆኑ ምስክር ነው፡፡ በአገራቱ በመሪዎች ደረጃም ጭምር ያለው ጠንካራ ትስስር በየጊዜው እየተገናኙ በክልላዊ እንዲሁም በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ስለሚኖራቸው ሚናና የጋራ ጥቅም ሀሳብ እንዲለዋወጡና የጋራ አቋም እንዲያራምዱ አስችሏቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ... በተቀላቀለችው Northorn Corridor Development Projects ስር ባሉት ፕሮጀክቶች ዩጋንዳ የምታስተባብረውን Standard Guage Railway ዘርፍ መቀላቀሏ ከዩጋንዳ ጋር የበለጠ ለመስራት እድሉን ይከፍታል፡፡
የኢ... ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በዩጋንዳ ሪፐብሊክ ከየካቲት 23-25 /2009 ያደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝትም በአገራቱ መካከል የነበረውን ትስስር ይበልጥ ያጠናከረ እንደነበር እሙን ነው፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የሁለቱ አገራት መሪዎች በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡-
በናይል ተፋሰስ አገሮች ስምምነት (Comprehensive Framework Agreement (CFA)) ዙሪያ ዩጋንዳ ስምምነቱን አለመፈረሟን በማንሳት የተወያዩ ሲሆን በዩጋንዳ በኩል የናይል ተፋሰስ አገራት የናይልን ውሃ በጋራ እና በተመጣጠነ መልኩ (Equitable) የመጠቀም መብት ስላላቸው የጋራ መግባባት ፈጥረው ሁሉም አገራት ስምምነት ላይ እንዲደርሱና ስምምነቱ እንዲፈረም እየሰሩ እንደሆነ ስለገለፁ ስለ CFA ጉዳይ በመሪዎች ደረጃ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ለማበጀት ተስማምተዋል፡፡
በአገራቱ አስተፅኦ አማካኝነት በሶማሊያ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላምም በማስቀጠል ዙሪያ ተወያይተው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ የሶማሊያን ወታደራዊ ሀይል የማጠናከር ስራ እንዲሁም ለአገሪቱ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ድጋፍ በማድረግ አገሪቱ እንድትቆም የማስቻል ስራ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በኢጋድ አደራዳሪነት የተፈረመው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት እንዲተገበርና national dialogue እንዲሳካ እንዲሁም Regional protection force (RPF) በአገሪቱ በአስቸኳይ እንዲሰማራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በንግድ መስክ ሁለቱ አገሮች ተባብረው መስራት እንዲቻል በመሰረተ ልማት መስክ የማገናኘት ስራ ስለመስራት ተወያይተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ሁለት ስምምነቶች ተፈርመዋል እነዚህም፡
በሴቶችና ህፃናት እንዲሁም በወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ስምምነቶች
V. ታንዛኒያ
ኢትዮጵያና ታንዛኒያ የቆየ ወዳጅነት ያላቸው አገራት ናቸው፡፡ ሁለቱ አገራት ግንኙነት በተለይም ከአፍሪካ ህብረት ምስረታ በኋላ በፖለቲዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እየተጠናከረ የመጣ ነው፡፡ ሁለቱ አገራት በሚገናኙባቸው አለም አቀፍም ሆነ አህራዊ መድረኮች ላይ የጋራ አቋም በመያዝ አጋርነታቸውን ጠብቀው የቆዩ አገራት ናቸው፡፡
ክቡር /ሚንስትር /ማርያም ደሳለኝ ... ከማርች 31 እስከ ኤፕሪል 1 2017 .. ድረስ በታንዛኒያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትሩ ታንዛኒያው መሪ ጆን ማጉፉሊ ጋር ባደረጉት ቆይታ 15 ነጥቦች ላይ ከመግባባት ደርሰዋል፡፡ መግባባት ከተደረሰባቸው ነጥቦች መካከል በማእድን ቁፋሮ፣ በገቢዎችና ጉምሩክ፣ በግብርና፣ በቴሌኮም እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፎች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ፣ የቪዛ ጥያቄን የማስቀረት፣ ኤምባሲ የመክፈት፣ የዳሬሰላምን ወደብ የመጠቀም እንዲሁም 400 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ለታንዛኒያ መላክ ... የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 3 ስምምነቶች ተፈርመዋል እነዚህም፡-
ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምስረታ(Establishment of strategic partnership)
የሚንስትሮች የጋራ ኮሚሽን ማቋቋም (Establishment of Joint ministerial commission)
በቱሪዝም ዘርፍ የመግባቢያ ስምምነት(MOU on cooperation on Field of tourism)
VI. ዛምቢያ
ኢትዮጵያና ዛምቢያ የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው፡፡ ዛምቢያ ነጻነቷን ለመቀዳጀት ላደረገችው ጥረት የዲፕሎማቲክ ድጋፍ ከሰጡት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት።የሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የሚገኝ ሲሆን በአህጉራዊ እና በአለም አቀፋዊ መድረኮች የጋራ አቋም በመያዝ እየሰሩ ይገኛሉ።ኢትዮጵያና ዛምቢያ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ አህጉር ሰላም እንዲሰፍንና በአገሮች መካከል የኢኮኖሚ ግንኙነት እንዲጠናከር ተቀራርበው እየሰሩ ከመሆናቸውም ባሻገር ይህ የፖለቲካ ግንኙነት ስር እንዲሰድ በኢኮኖሚው ዘርፍ መተሳሰር እና መጎልበት እንደሚገባው በማመን የሁለቱ ሀገሮች ባለስልጣናት የጋራ ቋሚ ኮሚሽን ትብብር እንዲቋቋም በመወሰናቸዉ .. 2015 . የማቋቋሚያ ስምምነት ተፈርሟል።
ክቡር /ሚንስትር /ማርያም ደሳለኝ ... ከማርች 29-31 ቀን 2017 .. በዛምቢያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ሁለት ስምምነቶች ተፈርመዋል፡
በኮሚኒኬሽን፣ በመረጃ ልውውጥ በመገናኛ ብዙሀን (Communication, Information and Media) እና በውሃ ሀብት አጠቃቀም መስኖና ሀይል ዘርፎች ትብብር(Cooperation in the Fields of Water Resource Management, Irrigation and Energy)
VII. ላይቤሪያ
የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ቀደምት ነው፡፡ ኢትዮጵያና ላይቤሪያ በአፍሪካ በቅኝ ያልተያዙ፣ ከአጉሪቱ ፖለቲካዊ ነፃነታቸውን ያላስደፈሩ አገሮች በመሆናቸው ብቸኛ ያደርጋቸዋል፡፡ በመሆኑም ከአፍሪካ አገራት ውስጥ ቀዳሚ የተባበሩት መንግስታት አባል አገራት ናቸው ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ታሪካዊ መሆኑን እንረዳለን፡፡ 250 በላይ ዜጎቿን በእርስበርስ ጦርነት ያጣችውን ላይቤሪያ ለመታደግ የመከላከያ ሰራዊታችን ወደዚያው አቅንቶ ታሪክ የማይረሳው ውለታ የሰራበት ክስተት ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በዚህም ከፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚንስትር ኃለማርያም ደሳለኝ ጋር በጋራ አገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ሁለቱ አገራት አራት ስምምነቶችንም ተፈራርመዋል፡፡
በትምህርት
በእንስሳት ሃብት፣
በጤና እና ህክምና ሳይንስ እና
በኢንዱስትሪ ልማት ስምምነቶቹን ተፈራርመዋል ፡፡
VIII. ኬንያ
ኢትዮጵያና ኬንያ ለዘመናት የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው፡፡ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ኬንያ ነፃነቷን ካገኘችበት ጊዜ አንስቶ በየትኛውም የመንግስት ስርአት ለውጥ ያልተፈተነ ነው፡፡ ሁለቱ አገራት ባህልና ቋንቋ የሚጋራ ህዝብ ያላቸው ናቸው፡፡ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ትስስር ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ መሆን የሚችል ነው፡፡ ሁለቱ አገራት የህዝብ እንቅስቃሴን በተመለከተ ዜጎቻቸው ያለምንም ቪዛ መዘዋወር እንዲችሉ ስምምነት አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ያላቸው አስተዋፅኦ በተለይም በሶማሊያና ደቡብ ሱዳን ላይ ከፍተኛ መሆኑ ሁለቱ አገራት የበለጠ ተቀራርበው እንዲሰሩ አግዟቸዋል፡፡ Northern Corridor Development Projects በሚገነቡ ፕሮጀክቶች ስር ኬንያ የምታስተባብረውን የሀይል ማመንጨት፣ ማስተላለፍና ትስስር (Power Generation, Transmission and interconnectivity) ዘርፍ አገራችን ኢኒሽየቲቩን መቀላቀሏ ሁለቱ አገራት ከዚህ ቀደም ከጀመሯቸው የኢኮኖሚ ትስስርን ከሚያፋጥኑ ስራዎች በተጨማሪ የአገራቱን አብሮነት የበለጠ ያጠናክራል፡፡
ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር / ወርቅነህ ገበየሁ .. ከማርች 8-10 ቀን 2017 . በኬንያ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። በቆይታቸው ከክብርት አምባሳደር አሚና ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ እነዚህም፡
በአገራቱ ሁለትዮሽ ግንኙነቶች በተለያዩ ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የበለጠ ስለማጠናከርና በሃገራችን እና በኬንያ መካከል .. 2012 . የተፈረመው የልዩ ደረጃ (Special Status) ስምምነት አፈፃፀም ዙሪያ ስለ መስራት፣
በአዲስ አበባ .. በኦገስት 2015 . የተፈረመውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ስለ መስጠት፣
ሶማሊያ ራሷን ችላ እንድትቆም የተጠናከረ እገዛ እንደሚያደርጉ፣ እንዲሁም በድርቅ ምክንያት ለተከሰተው ረሃብ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እርዳታ እንዲያደርግ ጥሪ ማድረግ እና ሌሎች ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ከባህረ ሰላጤው አገሮች ጋር የተደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች
IX. ኳታር
የኳታርና የኢትዮጵያ ግንኙነት ከነበረበት ደረጃ አንጻር ይመዘናል፡፡ ግንኙነቱ የተመሰረተው ... 1995 በመሆኑ ገና ልጅ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከግንኙነቱ እድሜ አንጻር ሲመዘን አሁን ያለው ግንኙነት የላቀ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡።
የኳታሩ ኢሚር Sheikh Tamim Bin Hamad Al-Thani ሚያዚያ 2 ቀን 2009 . ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ኢሚሩ ከኢፌዲሪ ክቡር ፕሬዝዳንት / ሙላቱ ተሾመ እና ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በአካባቢያዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ግንኙነቱ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የመተማመን መንፈስ እየጎለበተ መምጣቱን ያመላክታል፡፡ ጉብኝቱ ሁለቱ አገሮች በመጪዎቹ አመታት በትብብር ሊሰሩ የሚገቡ የትብብር መስኮችን ለይቷል፡፡
ባለፈው ታህሳስ በኳታሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር Sheikh Mohamed Abdulrahman Jassim Al-Thani የሚመራ ቡድን በአገራችን ጉብኝት እንዳደረገ የሚታወስ ሲሆን በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ የተደረጉት ተደጋጋሚ ጉብኝቶች ሁለቱ አገሮች በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡
X. ሳውዲ አረቢያ
ኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ ለዘመናት የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው፡፡ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ የተጀመረው ... 1948 እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በያዝነው አመት በህዳር ወር ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝቱም አካባቢያዊ፣ አህጉራዊና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም የአገራችን ልማታዊ ጉዳዮች ተዳሰዋል፡፡
የሳውዲ ዓረቢያው ንጉሳዊ ችሎት ልዩ አማካሪና የልማት ፈንድ ሊቀመንበር Ahmed Al khateeb የሚመራ የልዑካን ቡድን ... በዲሴምበር 15/2016 . አገራችንን ጎብኝቷል፡፡ Mr. Ahmed Al Khateeb በሀይል ምርትና አቅርቦት, በመንገድ ኮንስትራክሽን, እና በግብርና መስኮች ሀብታቸውን ኢንቨስት ሊያደርጉ የሚችሉ ባለሀብቶችን በመምራት ነው አገራችንን የጎበኙት፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ከክቡር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር በመገናኘት በኢኮኖሚያዊ አና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያሉ ውይይቶችን አካሂደዋል፣ የልዑካን ቡድኑ የታላቁ ህዳሴ ግድብንም ጎብኝቷል ለግድቡ ያለውንም አድናቆት ገልጿል፡፡
የሳውዲ አረቢያው የግብርናው ሚኒስቴር Abdul Rahman bin Abdul Mohsen al-Fadhli በዚያው ወር
አስተያየት
በአጠቃላይ የተደረጉት ጉብኝቶች ሙሉ በሙሉ የተሳኩ በሚባል ደረጃ የሚቀመጡ ናቸው፡፡ አገራችን በውጭ ጉዳይና አገራዊ ደህንነት ፓሊሲና ስትራቴጂ ላይ እንደተቀመጠው አገራችን ለአፍሪካ እንደ አህጉር ለአፍሪካ ቀንድ አገራት እንዲሁም ለባህረ ሰላጤው አገሮች የተለየ ትኩረት ትሰጣለች፡፡ በመሆኑም ከአገራቱ ጋር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ የአገራችንን ጥቅም ከማስጠበቁም ባሻገር አገራችን ለያዘችው የልማት ጉዞ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ በእነዚህ ጉብኝቶች ኢትዮጵያ ለአህጉሩ ብሎም ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም ልማት ያላትን ቁርጠኝነት የአሳየችበት ነው ብሎ መግለጽ ይቻላል፡፡


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman