የኦሮሚያ ክልል መንግስት አደነቀ

የፌዴራል መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ የኦሮሚያ ክልል መንግስት አደነቀ
የፌዴራል መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አደነቀ።
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫው፥ የኢፌዴሪ መንግስት በሰው ልጅ ላይ አሰቃቂ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ እና በሀገሪቱ ላይ ከባድ የሙስና የወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል የህግ የበላይነት አንዲከበር እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ ነው ብሏል።
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፤ የኢፌዴሪ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ በከፍተኛ ሁኔታ ያደንቃል ያለው መግለጫው፤ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።
በህግ በምትተዳደር ሀገር ውስጥ በሰው ልጅ ላይ ለመፈፀም ይቅርና ለማሰብ የሚከድብ ተግባር በመፈፀም እንዲሁም የህዝብን ሀብት ለግል ጥቅም ማዋል ከሀገር ክህደት ተለይቶ እንደማይታይም መግለጫው አትቷል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት መንግስት እየወሰደ ያለው እርምጃ ማንኛውም ሰው ከህግ ማምለጥ አንደማይችል እና ከሀገሪቱ ህገ መንግስት በላይ እንዳልሆነ እንዲሁም የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ጠንካራ መሰረት የሚጥል መሆኑንም ገልጿል።
ተግባሩ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለህግ የበላይነት መከበር በቁርጠኝነት እንዲሰራ የሚያነሳሳ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል።
ሌባ መቼም ቢሆን ከህዝብ አይን እና ጆሮ ማምለጥ አይችለም ያለው መግለጫው፥ የክልሉ ህዝብም በማንኛውም ህገ ወጥ ተግባርን መከላከል ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጠል ጥሪ አቅርቧል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman