የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ተዋህደው......

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ተዋህደው መቀጠል የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የኦዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ለማ መገርሳና የኦዴግ ሊቀ መንበር አቶ ሌንጮ ለታ ተፈራርመዋል።
የአሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ለማ መገርሳ ሁለቱ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የራሳቸው ታሪክና አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች በመለያየት ህዝብን ከመበታተን ወደ አንድነት በመምጣት የተጀመረውን ለውጥ እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማጠናከር እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።
ተበታትኖ መጓዙ ለህዝቡም ሆነ ለፖለቲካ ፓርቲዎቹ አድካሚ በመሆኑም እንደየፓርቲዎቹ የአስተሳሰብ ቀረቤታ በመጣመርና በመዋሃድ ለሃገር ግንባታ መረባረብ እንደሚያስፈልግም ነው የተናገሩት።
የፓርቲዎቹን ውህደት ህዝቡ ሲጠይቅ እንደነበር ያነሱት አቶ ለማ፥ ፓርቲዎቹም ተወያይተው ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አውስተዋል።
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ሌንጮ ለታ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያን ፌዴሬሽን ዴሞክራሲያዊ በማድረግ የተረጋጋና ሰላማዊ የአፍሪካ ቀንድን መገንባት እንደሚቻል ገልጸዋል።
አቶ ሌንጮ አያይዘውም የኦሮሞ አንድ መሆን ለሃገር ግንባታም ቢሆን ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ነው ያሉት።
ከዚህ ባለፈም የህዝቡን አንድነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመበታተን አንድ መሆን ወሳኝ ነው ብለዋል።
ከዛሬው ውህደት ባለፈ ግን ሌሎች ፓርቲዎችም ተመሳሳይ መንገድ እንዲከተሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የኦዴፓ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ስምምነቱን አስመልከቶ በሰጡት መግለጫ፥ ሁለቱ ፓርቲዎች የኦሮሞ ህዝብ አንድ እንዲሆኑ ባቀረበላቸው ጥሪ መሰረት በዛሬው እለት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የውህደት የመግባቢያ ስምምነት እንደተፈራረሙ አንስተዋል።
አያይዘውም ኦዴፓ ከኦዴግ ጋር የህገ ደንብ፣ የስትራቴጅ እና የፕሮግራም ልዩነት የሌለው በመሆኑ በጋራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።
በቀጣይም ከሁለቱ ፓርቲዎች ቴክኒካል ኮሚቴ ተቋቁሞ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል ብለዋል።
በጋራ ለመስራት የሚደረገው የውህደት ሂደት እንደሚቀጥል ያነሱት አቶ አዲሱ፥ አሁን ላይም ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተጀመሩ ውይይቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

ምንጭ፤ FBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman