የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር መስዋዕትነት የከፈለው ለህግ ልዕልና መረጋገጥ ነው…የክልሉ መንግስት

የትግራይ ህዝብ ለዓመታት የከፈለው መስዋዕትነት በሃገሪቱ የህግ የበላይነት እንዲከበርና በማንኛውም ወቅት ተጠያቂነት እንዲኖር መሆኑን የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ መንግስት ዛሬ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው መንግስት አሁን የጀመረው የህግ የበላይነትን የማስከበር ሂደት በተገቢው ጥንቃቄ ሊከናወን የሚገባው ነው።
ሰብአዊ ጥሰትና ሙስና በፈጸሙ ሰዎች ላይ በመንግስት ሰሞኑን እየተወሰደ ያለው እርምጃ የህግ ልዕልና ሳይሸራረፍ ከተጽዕኖ በጸዳ መልኩ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት መግለጫው አመልክቷል።
የትግራይ ህዝብ ለዓመታት የከፈለው መስዋዕትነት የህግ የበላይነት እንዲከበርና በማንኛውም ወቅት ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው መንግስት እየወሰደ ያለውን በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ እንዲያተኩር ጠቁሟል።

የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የሙስና ችግርና ህገ-መንግስታዊ ጥሰት እጃቸው ያለበት አመራሮችና ተቋማት ችግር መሆኑን ቀደም ሲል በተካሔዱ የኢህአዴግ የስብሰባ መድረኮች ላይ በግልጽ ውይይት መደረጉንም አመልክቷል።
ችግሩ በእኩል እንዲስተናገድ ከማድረግ ባለፈ እርቅና ይቅር ባይነትን መሰረት አድርጎ የተጀመረው ሂደት ወደ ኋላ እንዳይመለስ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል መግለጫው።
“የህግ የበላይነትም ሳይሸራረፍ እንዲተገበር ከፍተኛ ጥንቃቄና ጥናት የሚጥይቅ መሆኑንም የክልሉ መንግስት ያምናል” ሲልም አስታውቋል፡፡

የትግራይ ክልል ህዝብ ከሌሎች ብሔሮችና ብሔረሰቦች ጋር በመሆን የከፈለው መስዋዕትነት የዜጎች እኩልነትና ሰብአዊ መብት እንዲከበር እንጂ በማንም አካል እንዲጣስ እንዳልሆነ መግለጫው አመልክቷል።
ባለፉት ዓመታት ይታዩ የነበሩት የፍትህና የዲሞክራሲ መጓደሎች እንዲስተካከሉ ህዝቡ በፅናት እየታገለ መምጣቱንም መግለጫው አስታውሶ በጥልቅ ተሀድሶ ወቅት ህዝቡ ያሳየው ተሳትፎ አንዱ ማሳያ መሆኑን አስረድቷል።
ከሰብአዊ መብት አያያዝና ከሙስና ጉዳዮች ጋር በተያያዘ እየታየ ላለው ሁኔታ ተጠያቂዎቹ እጃቸው ያለበት አመራሮችና ተቋማት መሆናቸውንም መግለጫው አመልክቷል።
መቀሌ ህዳር 5/2011 (ኢዜአ)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman