ማበዳቸው ትክክልና ምክንያታዊ ነው!

 ኦሮሞ አገርን የማስተዳደር ስልጣን ያዘ ብለው አብደው ጨርቃቸውን የጣሉ እንዳሉ እየተመለከትን ነውⵆረግጠውና ዘርፈው ሲያስተዳድሩ የነበሩትን ባልጠበቁት ሁኔታ ሲያጡ ማበድ ሲያንሳቸው ነው

ከ8 ወራት በፊት ከምሁራን ጋር በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተነገረ ተብሎ አንደ አዲስ በየማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ ያለው ንግግር ምንም አዲስ ነገር የለውምⵆአይ አጀንዳ ፈጠራ!ድንቄም አጀንዳ
አቶ ሽመልስ ስለ ፊንፊኔ፤ስለ አፋን አሮሞ፤ስለ ብልፅግና ፓርቲ የተናገሩት እውነት እውነቱን ዕንቅጩን ነውⵆእውነቱ የተነገራቸው ኃይሎች የተነገረውን እውነት ቢያውቁም መቀበል ስለማይፈልጉ ነገርዬውን ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ለመጠምዘዝ አጀንዳ ለመፍጠር ጥረት አደረጉ፤ለዚህም ይረዳናል ብለው ያሰቡትን የአቶ ሽመልስ የአንድ መድረክ ንግግር ከማህደራቸው በርብረው በማውት ማራገብ ጀመሩⵆየሚዲዎቻቸውንም ቅንጅት አየንበት
መሰሪዎቹ እነርሱ መላ ነው ብለው በወሰዱት በዚህ ቀሽም አካሄዳቸው ኦሮሞና አማራ ግጭት ውስጥ ይገባልናል ብለው አሰቡ፤ያሰቡት አልተሳካም!ወደፊትም ሊሳካ አይችልም
ከስልጣን የተባረሩቱ የህወሃት ቡድን ሽማግሌዎች የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ከፊንፊኔ/አዲስ አበባ ተባርረው መቀሌ ከመሸጉ ወዲህ የሚችሉትን ሁሉ ቢያደርጉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ከስልጣን ለማውረድ አልቻሉም፤ለወደፊትም የትኛውንም ሙከራ ቢያደርጉ ኦሮሞን ከስልጣን መንበር ማውረድ የሚችሉበት ሁኔታ የለምⵆ
ኦሮሞ የኢትዮጵያ ምሰሶ ነው! ምሰሶው ከወደቀ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ልትኖር አትችልምⵆይህ እውነት “ህወሃት እኔ ከሌለሁ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” እንደሚለው ተረት ተረት አይነት ነገር እንዳይመስለን ጥንቃቄ ያስፈልጋልⵆአገር ለማፍረስ በመፍጨርጨር ላይ የሚገኙ ኃይሎች ኦሮሞና ኦሮሚያ ላይ የሚረባረቡበትን ምክንያት ከዚህ አንፃር መገንዘብ ተገቢ ነው!እነርሱ ይህቺን ሃቅ በደንብ አብጠርጠረው ያውቃሉⵆ
ኦሮሞ የአቃፊነት ቱባ ባህሉን ጠብቆና አክብሮ ከብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር በሰላም ሲኖር እጅግ በጣም የሚሸክካቸው የህወሃት ሽማግሌ ቡድንና ጀሌዎቹ እነ ኦነግ ሸኔ እና የአማራ አክራሪ ቡድኖች በሰበብ አስባቡ የስልጣን መውጫ ቀዳዳ ቢፈልጉም ምንም ሊያገኙ አይችሉም!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman