ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ27 አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ
ጽህፈት ቤቱ እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንቷ የሰጡት 16 ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም 11 የአምባሳደርነት ሹመት ነው፡፡
በዚሁ መሰረት፦
አቶ ተፈራ ደርበው፣
አቶ ደሴ ዳልኬ ፣
ዶክተር ስለሺ በቀለ ፣
ጀነራል ባጫ ደበሌ ፣
ጀነራል ሀሰን ኢብራሒም ፣
ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ ፣
ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ ፣
አቶ ረሻድ መሀመድ ፣
አምባሳደር ጀማል በከር ፣
አቶ ፈይሰል አሊይ ፣
አቶ ኢሳያስ ጎታ ፣
አቶ ጸገአብ ክበበው ፣
አቶ ጣፋ ቱሉ ፣
ዶክተር ገነት ተሾመ ፣
አቶ ዳባ ደበሌ እና
አቶ ፈቃዱ በየነ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡
በተጨማሪም :-
አቶ አሳዬ አለማየሁ፣
አቶ ሃይላይ ብርሃነ፣
አቶ አወል ወግሪስ፣
ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት፣
አቶ አንተነህ ታሪኩ፣
አቶ አክሊሉ ከበደ፣
አቶ ሰይድ መሐመድ፣
አቶ ዮሴፍ ካሳዬ፣
አቶ ዘላለም ብርሃን፣
ወይዘሮ ፍርቱና ዲባኮ እና
አቶ ወርቃለማሁ ደስታ በአምባሳደርነት መሾማቸውንም የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ ሹመቱን የሰጡት በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት መሆኑን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤተ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ